Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ታሕሳስ ፩


✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ታኅሣሥ ፩ (1) ❖

✞✞✞✝ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይ "ቅዱስ ኤልያስ" :
"ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ" እና "ቅድስት ቤርሳቤህ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ታላቁ ቅዱስ ኤልያስ "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ቀጥላ ቅዱስ ኤልያስን ታከብራለች:: "ርዕሰ ነቢያት - የነቢያት ራስም" ትለዋለች:: እርሱ ሰማይን የለጐመ: እሳትን ያዘነመ: ፍጥረትንም በቃሉ ያዘዘ አባት ነውና:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ቅዱሱ ትውልዱ (ነገዱ) ኢዮርብዓም ነጥሎ ከወሰዳቸው እሥራኤል (10ሩ ነገድ) ሲሆን አባቱ "ኢያስኑዩ" : እናቱ ደግሞ "ቶና (ቶናህ)" ይባላሉ:: በጐ
አምልኮ ነበራቸውና እግዚአብሔር ማሕጸነ ቶናህን ቀድሶ ይህንን ቅዱስ ፍሬ ፈጠረ::

+ቅዱስ ኤልያስ በተወለደ ቀን በቤታቸው ብርሃን ተሞልቶ ታይቷል:: ብርሃን የለበሱ 4 ሰዎች (መላእክት) መጥተውም በእሳት ሰፋድል (መጐናጸፊያ) ሲጠቀልሉት ወላጆቹ በማየታቸው ደንግጠው ለነቢያትና ለካህናት ነገሯቸው::

+ካህናቱ ግን ነገሩ ቢረቅባቸው "ምን ዓይነት ፍጥረት ይሆን? በእሥራኤል ይነግሥ ይሆን! ወይስ ነቢይ ይሆን?" ብለውም አድንቀዋል:: ቅዱስ ኤልያስ ከልጅነቱ ጀምሮ ኮስታራ: ቁም ነገረኛ: ንጽሕናንም የሚወድ እሥራኤላዊ ነው::

+ወቅቱ (ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት) ሕዝቡና ነገሥታቱ የከፉበት: እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት የሚመለክበት ነበር:: ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት
ጣዖታት (ዳጐንና ቤል) በዚያ ዘመን ወደ እሥራኤል ገብተው ነበር::

+ቅዱስ ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ: የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር::

+በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው:: እርሱም "እሺ" ብሎ ታዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ ተቀበለ::

ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል: ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር አደረገ::

+በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር:: በዚህ ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ:-

1.ለድንግልና (ድንግል ነበርና)
2.ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና)
3.ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን
የጣለ ነቢይ ይባላል::

+መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን: በዘመነ ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን: በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ
የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ አልነበረም:: በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ
ክፉ ባልና ሚስት በእሥራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን ጣዖት አስመለኩት::

+ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሃሰት ምስክር ደሙን አፈሰሱት:: ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም:
አልለውጥም::" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::

+ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ አክአብና ኤልዛቤል ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም:: የአንቺንም
ደም ውሻ ይልሰዋል" አላቸው:: በዚህ ምክንያትም ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም::

+በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች:: 900ው ሲታረዱ አንድ መቶውን ግን ቅዱስ አብድዩ በዋሻ ውስጥ ደብቆ
እየመገበ አተረፋቸው:: በእሥራኤል ውስጥ ግን ዓመጻና ኃጢአት እየተስፋፋ ሔደ:: የእግዚአብሔርን ስጦታ
እየተመገበ ሕዝቡ ለቤል (ለበዓል) ሰገደ::

+ይህን ጊዜ ግን ቅዱስ ኤልያስ እንዲህ አለ:- "ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ በቃለ አፉየ::" ብሎ ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ ከለከለ::

ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት ተከለከለ::

+ሕዝቡ በኃጢአቱ ምክንያት ተጐዳ:: እርሱን ቁራ ይመግበው: ምንጭ ፈልቆለት ይጠጣ ነበር:: ይሔው
ቢቀርበት ጸለየ:: እግዚአብሔርም ከፈለገ ኮራት ወደ ሰራፕታ እንዲወርድ አዘዘው:: በዚያም የነቢዩ ዮናስ እናት እንጐቻ ጋግራ ብታበላው ቤቷ በበረከት ተሞላ::

+ልጇ ሕጻኑ ዮናስ ቢሞትም በጸሎቱ አስነሳላት:: ቀጥሎም 7 ጊዜ በትጋት ጸልዮ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የዘጋውን ሰማይ ከፍቶታል:: ሕዝቡም ዕለቱኑ ከበረከቱ ቀምሰዋል::

+ከዚያ አስቀድሞ ግን ከኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖት ጋር ተወዳድሮ አሸንፏቸዋል:: መስዋዕት
ሰውተው የእርሱን ብቻ እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታለታለችና ሕዝቡ 850ውን ሐሰተኛ ነቢያት በወንዝ ዳር በሰይፍ መትተዋቸዋል::

+ይሕንን የሰማች ኤልዛቤልም ትገድለው ዘንድ አሳደደችው:: "አቤቱ ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ! ብቻየን ቀርቻለሁና" ብሎ ቢጸልይ እግዚአብሔር ለጣዖት ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን እንዳተረፈ: እርሱንም ወደ ብሔረ ሕያዋን እንደሚወስደው ብሥራትን ነገረው::

+ደክሞት ተኝቶ ሳለም ቅዱስ መልአክ (ሚካኤል) ቀስቅሶ ታየው:: እንጐቻ ባገልግል: ውሃ በመንቀል አቅርቦ "ብላ! ጠጣ!" አለው:: በላ: ጠጣ: ተኛ:: እንደ
ገና ቀስቅሶ አበላው:: በ3ኛው ግን "ብላዕ እስከ ትጸግብ እስመ ርሑቅ ፍኖትከ - ጐዳናህ ሩቅ ነውና እስክትጠግብ ብላ" አለው::

+ኤልያስም ለ40 ቀናት ያለ ምግብ ተጉዟል:: ከዚያ በሁዋላም ምድራዊ ሕብስትን አልተመገበም:: እግዚአብሔር አክአብና ኤልዛቤልን ከተበቀላቸው
በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስ በክፋተኞች ላይ 2 ጊዜ እሳትን አዝንሟል::

+የሚያርግበት ጊዜ ሲደርስም ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን "የምትሻውን ለምነኝ" ቢለው "እጥፍ መንፈስህን"
አለው:: 3 ጊዜ ሊያስመልሰው ሞከረ:: ቅዱስ ኤልሳዕ ግን በብርታት ተከተለው:: ዮርዳኖስን ከፍለው ከተሻገሩ በሁዋላ ግን ቅዱስ ኤልያስን ሠረገላ እሳት ወርዶ
ነጠቀው:: ለኤልሳዕም እኩሉን ግምጃውን ጣለለት::

+ዛሬ ቅዱስ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለ ሲሆን በዘመነ ሐሳዌ መሲሕ መጥቶ በሰማዕትነት ከቅዱስ ሔኖክ ጋር ያርፋል:: (ራዕይ)¤ለተጨማሪ ንባብ ( ከ1ነገ. 17-2ነገ. 2, እና ዕርገተ ኤልያስን ያንብቡ::)

<<ነቢዩ ኤልያስ በእውነት ታላቅ ነው!>>

+"+ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ +"+

=>ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በታናሽ እስያ አካባቢ የተወለደ ሲሆን የክቡራኑ የመሣፍንት ልጅ ነው::
በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ ትንሹ ቴዎዶስዮስ ወደ ቤተ መንግስቱ ወሰደው::

+በዚያም "አገረ ገዥ ላድርግህ" ብሎ ቢጠይቀው "ትንሽ ቆየኝማ" ብሎት ጠፍቶ በርሃ ገብቶ መነኮሰ::
ቅዱስ ዼጥሮስ በምንኩስና ሲጋደል: ካለበት በርሃ መጥተው በግድ ወስደው: የጋዛ (አሁን የፍልስጤምና
እሥራኤል ደንበር) ዻዻስ አደረጉት::

+ከደግነቱ የተነሳም በቅዳሴ ጊዜ ሥጋ ወደሙ ሲለወጥ ያየው ነበር:: መላእክትም ያጫውቱት ነበር:: ሕዝቡ
ሲያጠፉ በየዋሕነት ዝም ቢላቸውም ቅዱስ መልአክ ገሥጾታል::

+የፋርስ ነገሥታት አጽመ ሰማዕታትን ሲያቃጥሉም እርሱ የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን አጽም ይዞ ተሰዷል:: ለብዙ
ዘመናት በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ቅድስት ቤርሳቤህ +"+

=>ይህቺ እናት አስቀድማ የኦርዮ ሚስት: ቀጥሎ ደግሞ የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሚስትና የሰሎሞን እናት
ለመሆን በቅታለች:: ቁጥሯ ከደጋግ እናቶቻችን ሲሆን የድንግል ማርያም ቅድመ አያትም ናት:: አንዳንድ
ሊቃውንት ደግሞ ስሟን "ቤትስባ (ቤተ ሳባ)" : ትውልዷንም ከኢትዮዽያ ያደርጉታል::=>አምላከ ኤልያስ በምልጃው ለሃገራችንና ለሕዝቧ
ርሕራሔውን ይላክልን:: ከቅዱሳኑም በረከትን ይክፈለን::

=>ታሕሳስ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኤልያስ ርዕሰ ነቢያት
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ
3.ቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ)
4.ናቡቴ ኢይዝራኤላዊ
5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
5.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት

=>+"+ ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝኩትን: የባሪያየን የሙሴን ሕግ አስቡ:: እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላቹሃለሁ:: መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ
ልጆች: የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል:: +"+ (ሚል. 4:4)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!። 

  "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethe
llettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments