Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

በእንተ ስማ ለማርያም ማህበር ህግና ደንብ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

በእንተ ስማ ለማርያም ማህበር ህግና ደንብ

 አንቀፅ 1

1.የማህበሩ መጠሪያ ስም በእንተ ስማ ለማህበር

1.1 በእንተ ስማ ለማርያም ፥ ቃሉ የግዕዝ ነው። ስለ እመቤታችን፣ በእመቤታችን ስም ማለት ነው። ይህ ድምጽ በኢትዮጵያውያን ሁሉ ዘንድ የሚታወቅ ዝነኛ ስም ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለፉ ምሁራንና ዛሬላይ በተለያየ መንፈሳዊውም ሆነ ዓለማዊ ህይወት ውስጥ የሚገኙና በአብነት ትምህርት ቤት የመማር ዕድሉ የገጠማቸው በሙሉ ይሄ ስም ምግብ በልቶ በህይወት ለመቆየት ብሎም ተምሮ ለመጨረስ ዋስትናቸው የነበረ ስም ነው።

•••
የተሜው የቆሎ ተማሪው ምሳና ራቱን፣ ስንቁን ከመላ ሀገሪቱ ነዋሪዎች የሚሰበስበው ይሄን ስም ጠርቶ ነው። “በእንተ ስማ ለማርያም” ስለ እማምላክ ስለወላዲተ አምላክ ብላችሁ ይላል።

                    አንቀፅ 2

    2.ማህበሩ የተቆቆመበት አላማ

2.1ነድያንን የመርዳት
2.2 ነድያንን የማግደፍ
2.3 ቤተክርስቲያንን ማገልገል

                             አንቀፅ 3

    3. ማህበሩ የሚገኝበት ቦታ

✝️ ጎንደር ደብረ መዊ ቀዳሚ አድባር አበራ ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተክርስትያን

                             አንቀፅ 4

   4 አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣

4.1 የኢትዮጵያ፣ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ የሆነ/ች/
4.2 በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ለመመራት ፈቃደኛ የሆነ/ች/
4.3 ዕድሜው/ዋ/ ከ 15 ዓመት በላይ የሆነ/ች
4.4 በማህበሩ የሚሰጠውን የቀዳማይ ተከታታይ ትምህርት ወስዶ/ዳ/ ፎርም የሞላ/ች/
4.5 በግቢ ጉባኤ፣በሰ/ት/ቤት እና በተለያዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሲያገለግል ቆይታ/ቶ ማስረጃ ይዞ/ዛ ከመጣ/ች ለ3 ወር እንቅስቃሴው/ዋ ታይቶ በሥራ አስፈፃሚ ሲወሰን፣
4.6 በማህበሩ የሚሰጠውን ቀዳማይ ኮርስ በሥራ፣በትምህርት እና በመሳሰሉት አሳማኝ ምክንያቶች መውሰድ የማይችሉ ከሆነ ለ6 ወር ማህበሩ ሳምንታዊ እና ወርሀዊ መርሐ ግብራት እንቅስቃሴው ታይቶ በሥራ አስፈፃሚ ከተወሰነላቸው፣
4.7 በአጥቢያው ያሉ ካህናት እና ዲያቆናት አባል ለመሆን በፈለጉ ጊዜ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ከአጥቢያው ውጭ የሆኑ ካህናት እና ዲያቆናት ግን ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
4.8 ከሌላ እምነት የመጣ/ች/ ሆና/ኖ በአጥቢያ ቤተክርስትያን በቃለ ዓዋዲው መሰረት ተምሮ የተጠመቀ ከሆነ እና አባል ለመሆን የሚያስችሉ መሰፈርቶችን ካሟላ/ች አባል መሆን ይችላል/ትችላለች፡፡

                                አንቀፅ 5

 5 የአባላት መብት እና ግዴታ

      5.1 የአባላት መብት

5.1.1 ማንኛውም አባል በጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ እና እንደደረጃው መርሐ ግብሮች ላይ የመገኘት መብት አለው፣
5.1.2 ማንኛውም አባል መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ በማህበሩ የሚሰጡ አገልገሎቶችን የማግኘት መብት አለው፡፡
5.1.3 በ አሳማኝ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ሲዘዋወር መሸኛ የማግኘት መብት አለው፣
5.1.4 በደስታ እና በሀዘን ጊዜ ማህበሩ በሚያወጣው መስፈርት መሰረት ድጋፍ የማግኘት መብት አለው፣
5.1.5 አንድ አባል በፈቃደኝነት አባል መሆን አልፈልግም ብሎ በጽሑፍ ካቀረበ ተቀባይነት ይኖረዋል፣ ነገር ግን መሸኛ ወረቀት አይሰጠውም፡፡
5.1.6 ማንኛውም አባል ማህበሩ የሚያወጣውን መስፈርት ካሟላ ማህበሩ የሚሰጡ ስልጠናዎች እና ሌሎች አገልግሎቶች የማግኘት መብት አለው፡፡
5.1.7 ማንኛውም አባለ ለማህበሩ በጽሑፍ እና በቃል ሐሳብ የመስጠት መበት አለው፣
5.1.8 ማህበሩ የሚያወጣውን መስፈርት ካሟላ በሥራ አስፈፃሚነት የመመረጥ እና የመምረጥ መብት አለው፣

                                አንቀፅ 6

      6.1 የአባላት ግዴታ

6.1.1 የማህበሩ አባላት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ፣ትውፊት እና ሥርዓት መጠበቅ እና በእርሱ የመመራት ፣
6.2.2 በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ የመመራት፣
6.2.3 በየ አሉበት ቦታ (አጥቢያ) ቅዳሴ ማስቀደስ
6.2.4 በጉባኤ ሰዓት ቀድሞ የመገኘት እና የፀሎት ሰዓትን ማክበር
6.2.5 የንስሃ አባት የመያዝ ፣
6.2.6 ወርሃዊ መዋጮ የመክፈል፣
6.2.7 ማህበሩ በሚመድባቸው ወቅታዊ ሥራዎች ላይ የማገልገል፣
6.2.8 ቤተክርስቲያን እውቅና ባልሰጣቸው መንፈሳዊ ማኀበራት አባል መሆን የለበትም፣
6.2.9 የማህበሩን እና የቤተክርስቲያኒቷን ነዋያተ ቅዱሳት የመጠበቅ እና የመንከባከብ ግዴታ አለበት፣
6.2.10 ማንኛውም አባል በተከለከሉ ቦታዎች ማለትም፡-
በመናፍቃን አዳራሽ ሲማር ወይም ሲያስተምር፣
ለመንፈሳዊ ሕይወት በማይስማሙ/አልባሌ ቦታዎች/፣
የቤተክርስትያንን ስም በሚያስነቅፍ ቦታዎች መገኘት የለበትም እንዲሁም በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው ከተለዩ ስዎች ጋር ማንኛውም ዓይነት መንፈሳዊ ግንኙት ማድረግ የለበትም፣
6.2.11 ማንኛውም የማህበሩ አባል ማሀረበሩ ሳይወክለው ወይም ሳይልከው፣ በማንኛውም ቦታ ማህበሩን መወከል፣
በማህበሩ ስም ማንኛውንም ዓይነት መርሐ ግብር መዘርጋት፣
በማህበሩ ስም ዕርዳታ ማሰባሰብ፣ በማህበሩ ስም ማስተማር እና ጽሑፎችን መበተን፣ የማህበሩን መገልገያ ንብረቶች ማዋስ አይችልም፡፡
6.2.12 ማንኛውም አባል የማህበሩን አንድነት የሚያፈርስ ተግባር መፈጸም የለበትም፡፡ እንዲሁም የቡድን ስሜት መፍጠር የለበትም፣
6.2.13 ከማህበሩ የሚዋሳቸውን ንብረቶች በወቅቱ የመመለስ ግዴታ አለበት፣
4.2.14 ማንኛውም አባል ለሌሎች አባላት እንዲሁም ምዕመናን ማሰናከያ የሚሆን ነገር መሥራት የለበትም፣
6.2.15 ማንኛውም አባል ለፈተና የሚያጋልጡ እና ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ውጭ የሆነ አለባበስ፣ የተለያዩ ቀለሞች እና ጌጣጌጦች መጠቀም የለበትም፣
6.2.16 በማህበሩ መደበኛ መርሐ ግብራት እንዲሁም በአውደ ምህረት ስብከት ወንጌል እየተሰጠ ተስብስቦ መቆም፣የግል ወሬ ማውራት እና የግል ሥራ መስራት የተከለከለ ነው፡፡
6.2.17 የስም መቆጣጠሪያው ላይ ስሙን የማስመዝገብ እና ምልክት የማስደረግ ግዴታ አለበት፣
6.2.18 ረጅም ጊዜ በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች ራቅ ብሎ የሚሄዱ አባል በማህበሩ መርሐ ግብራት ለረጁም ጊዜ መካፈል የማይችል ከሆነ እስኪመቻችለት ድረስ በአባልነት ለመቆየት እንዲፈቀድለት የሚመለክተውን ክፍል መጠየቅ እና ፈቃድ ማግኘት አለበት፣
6.2.19 ማንኛውም የማሀረበሩ አባል በማህበሩ በሚካሄደው ሳምንታዊ እና ወርሀዊ መርሐ ግብርና መደበኛ ተከታታይ ትምህርት እንዲሁም ማህበሩ በሚጠራው ስብሰባ ላይ መቅረት የለበትም፣ የሚቀር ከሆነም ችግሩን በማመልከቻ ገልጾ ሲፈቀድለት መሆን አለበት፣
6.2.20 በተለያዩ ምክንያቶች ከማህበሩ ለመልቀቅ የሚፈልግ አባል የማህበሩን ከመልቀቁ በፊት የሚለቅበት ምክንያት በግልጽ በጽሑፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
6.2.21 ማንኛውም አባል ጋብቻውን መፈጸም ያለበት በሥርዓተ ቤተክርስቲያን መሆን አለበት
6.2.22 ማንኛውም አባል ከማህበሩ አባላት ጋር ተቻችሎ መኖር አለበት፣
6.2.23 የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ የመጠበቅ፣

                            አንቀፅ 7

     7. ከአባልነት የሚያሳግዱ ነጥቦች

7.1 የሌላ እምነት ተከታይ ሆኖ ሲገኝ፣
7.2 በቀሪ ብዛት የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ አልፎ ሲገኝ እና ሥራ አስፈጸሚው ሲያምንበት፣
7.3 የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ተላልፎ ሲገኝ እና ሥራ አስፈጻሚው ሲያምንበት፣

                               አንቀፅ 8

    8 የአገልጋይ መብት እና ግዴታ

8.1 የአገልጋይ መብት፣

8.1.1 ማህበሩ በመደበው የአገልግሎት ክፍል የማገልገል፣
8.1.2 ማህበሩ የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ካሟላ በተዋረድ ባሉ ክፍሎች በሥራ አስፈጻሚነት እና አባልነት የመመረጥ፣
8.1.3 በአሳማኝ ምክንያት ማህበሩን ሲለቅ እና በጽሑፍ መልቀቂያ ሲጠይቅ መረጃ የማግኘት፣
8.1.4 ማንኛውም አገልጋይ በአገልጋይነቱ ማህበሩ የሚሰጣቸውን ማንኛውንም አይነት፣አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፣
8.1.5 አንድ አገልጋይ ከአገልግሎት ርቆ ቆይቶ መመለስ ቢፈልግ ለሥራ አስፈፃሚው አቅርቦ ሥራ አስፈፃሚው ካመነበት ወደ አገልግሎት ይመለሳል፡፡
8.1.6 አንድ አገልጋይ ከተመደበበት ክፍል በፈቃደኝነት አላገለግልም ብሎ በጽሑፍ ቢያቀርብ እና ሥራ አስፈጻሚው ካመነበት ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
8.1.7 አንድ አገልጋይ በአገልግሎት የሚያጋጥሙትን ችግሮች በጽሑፍም ሆነ በቃል የማቅረብ መብት አለው፡፡

8.2 የአገልጋይ ግዴታ

8.2.1 አንድ አገልጋይ ለማገልገል ከጽ/ቤቱ የአገልግሎት ፈቃድ ማግኘት አለበት፣
8.2.2 አንድ አገልጋይ በተመደበበት የአገልግሎት ክፍል የማገልገል ግዴታ አለበት፣
8.2.3 አንድ አገልጋይ የክርስቲያኖችን ሕይወት ለመምራት (አርአያ) ለመሆን ጥሩ የሥነ-ምግባር ባለቤት የመሆን ግዴታ አለበት፣
8.2.4 የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ የመጠበቅ፣
8.2.5 ማህበሩ በሚያዘው የሥራ መስክ ሁሉ እንደ አቅሙ የመታዘዝ ግዴታ፣
8.2.6 ጥፋት አጥፍቶ ሲገኝ የሚሰጡትን የቅጣት ማስጠንቀቂዎች እንዲሁም ቅጣቶችን የመቀበል ግዴታ አለበት፣
8.2.7 የማህበሩን ወርሀዊ መዎጮ የመክፈል ግዴታ አለበት፣

                                አንቀፅ 9 

    9. ለሥራ አስፈፃሚነት ለመመረጥ መሟላት ያለባቸው ነጥቦች፣

9.1 በኢ/ኦ/ተ/ ሃይማኖቱ ጽኑ የሆነ እና በግብረገብነቱ የተመሰከረለት
9.2 በማህበሩ በአባልነት ቢያንስ ለ3 ዓመታት የቆየ፣
9.3 በሥራ አስፈፃሚነት አባል ለመሆን 2/3ኛ የሥራ አስፈፃሚ ድምጽ ማግኘት አለበት፣
9.4 ዕድሚያቸው ሃያ/20 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
9.5 ለአገልግሎት በቂ ጊዜ ያለው፣
9.6 የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ጠብቆ ማስጠበቅ የሚችል፣

                                 እንቀፅ 10

    10.  ከአገልጋይነት የሚያሳግዱ ነጥቦች፣

10.1 የሌላ እምነት ተከታይ ሆኖ ሲገኝ
10.2 የማህበሩን ብሎም የአጥቢያውን እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ፣
10.3 የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት ካልቻለ
10.4 ማህበሩ ያወጣውን መተዳደሪያ ደንብ ማክበር እና በደንቡ መሰረት መመራት ካልቻለ፣
10.5 በቀሪ ብዛት የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች ተላልፎ ሲገኝ እና ሥራ አስፈፃሚው ካመነበት፣

                               አንቀፅ 11 

     11.የማህበሩ መዋቅር እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

11.1 የማህበሩ መዋቅር
11.2 ማህበሩ ተጠሪነቱ ለቤተክርስቲያኑ ሰበካ ጉባዔ ነው
11.3  የማህበሩ ሥራ አመራር ብዛታቸው ከ7-12 ሊደርስ ይችላል፡፡
11.4 የማህበሩ የሥራ አመራር (ሥራ አስፈፃሚ) ከዚህ በታች
               የተዘረዘሩት ክፍሎች አሉት፡-

1 የማህበሩ ሊቀመንበር እና ፀሐፊ (ጽሕፈት ቤት)
2 የሰበካ ጉባዔ ተወካይ
3 ትምህርት ክፍል (መርሐ ግብር ክፍል)
4 አባላት ጉዳይ ክፍል
5 ግንኙነት ክፍል (ልማት ክፍል)
6 ንብረት ክፍል ( ሂሳብ ክፍል) 
7 በጎ አድራጐት ክፍል

ማሳሰቢያ፡- ይህ መዋቅር እንደ አስፈላጊነቱ በጊዜው ባሉ ሥራ አስፈፃሚዎች ሊቀያየር እና ሊሻሻል ይችላል፡፡

                               አንቀፅ 12

      12. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

12.1 ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ይሆናል፣
12.2 ከ7-12 አባላት ይኖሩታል፣
12.3 በጠቅላላ ጉባኤ ተመርጦ የሚሰየም ሲሆን ጠቅላላ የማህበሩ እንቅስቃሴ ይመራል
12.4 የማህበሩን በጀት ያፀድቃል፣
12.5 በየሦስት ወሩ የማህበሩን የስራ አፈፃፀም (ሪፖርት)ይገመግማል፣
12.6 የማህበሩ ዓላማዎች መተግበራቸውን ይከታተላል፡፡
12.7 የማህበሩ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከሚመለከተው አካል ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣
12.8 የማህበሩ ተግባራት ለማከናወን የተለያዩ ዘዴዎችን ይቀይሳል፣
12.9 የማህበሩን ዓላማና ተግባር ለማሳካት እንቅፋት የሚሆኑ ማንኛውንም አባልት ላይ የተለያዩ የማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ይወስዳል፣በዚህም የማይስተካከል ከሆነ ጉዳዩን ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ከአባልነት እንዲሰረዝ ያደርጋል፡፡
12.10 የሥራ አስፈፃሚ ከተመረጠበት አንስቶ ለ3 ዓመታት ያገለግላል፡፡

                                አንቀፅ 13

    13.የማህበሩ የሥራ አስፈፃሚ ተግባር እና ኃላፊነት

13.1 የማህበሩ ሊቀመንበር ተጠሪነቱ ለሥራ አስፈፃሚ ሲሆን የማህበሩ ጸሐፊ ተጠሪነቱ ለሰብሳቢ  ይሆናል፡፡ ሌሎች የማህበሩ የሥራ አመራሮች ተጠሪነታቸው ለዚህ ጽ/ቤት ነዉ፡፡ እንደአስፈላጊነቱ ማህበሩ ባመነበት ክፍሎችን በሰብሳቢ  እና በጸሐፊው የበላይነት እንዲመሩ ያደርጋል፡፡ አጠቃላይ ሥራ አስፈፃሚው ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ነዉ፡፡ የሥራ አስፈፃሚውን በሊቀመንበርነት የሚመራው የማህበሩ ሰብሳቢ ነዉ፡፡ በአጠቃላይ በሥራ አስፈፃሚነት ተመርጦ የሚሰራ ሰው ቃል የገባውን ኃላፊነት ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ ታዛዥነትን በመቀበል የማህበሩን ህልውና መጠበቅ አለበት፡፡ የእያንዳንዱ ክፍል ኃላፊነት እና ተግባር ከዚህ በታች በዝርዝር ይገኛል፡፡

      13.1.1የማህበሩ ሰብሳቢ ኃላፊነትና ተግባር

13.1.1 ተጠሪነቱ ለማህበሩ  ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይሆናል፣
13.1.2 ከሰበካ ጉባዔ የሚተላለፉትን መመሪያዎች ተግባራዊ ያደርጋል፣
13.1.3የማህበሩን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በበላይነት ይመራል፣ ውሳኔውንም ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያስተላልፋል፣ተፈፃሚነታቸውንም ይከታተላል፣
13.1.4 ጽ/ቤቱን በተመለከተ ከፀሐፊው ጋር በመነጋገር አጀንዳዎች እንዲዘጋጁ ያዛል
13.1.5 የማህበሩ ክፍሎች ጠቅላላ መርሐ ግብር እና እንቅስቃሴያቸውን ይከታተላል፣
13.1.6 ከተለያዩ ቦታዎች የማህበሩ የሚመጡትን ደብዳቤዎች በማስተናገድ አስፈላጊውን መልስ ይሰጣል ወይም ለሚመለከተው ክፍል በመምራት በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
13.1.7 ማህበሩን በተመለከተ ከተለያዩ ቦታዎች ለሚመጡ የስብሰባ ጥሪዎች ማህበሩን ውክሎ ይገኛል ወይም በተዋረድ የሚመለከተውን ክፍል እንዲሳተፉ ያዛል፣
13.1.8 አንድ ስራ አስፈፃሚ በሥራው ቢደክም፣መመሪያ እና ደንብ ባይጠብቅ፣በሥነ-ምግባር ብልሹ ቢሆን፤ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት ባይችል….ወዘተ ሰብሳቢ ይመክራል በደብዳቤ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ካለው የሥራ ኃለፊነት እንዲወርድ የሥራ አስፈፃሚን ልዩ/መደበኛ ስብሰባ በመጥራት ያሉትን ችግሮች ለሥራ አስፈፃሚ በማቅረብ ስራ አስፈፃሚ ሲያምንበት ከሥራው/ከስራ አመራርነቱ እንዲታገድ ያፀድቃል፣ በድምጽ አሰጣጥ ስዓት የሰብሳቢ  ድምጽ ተቆጣሪነት ይኖረዋል፡፡ ሥራ አስፈፃሚው ያመነበትን ውሳኔ ለተወሰነበት ሰው በደብዳቤ እንዲገለጽለት ያደርጋል፣
13.1.9 የማህበሩ የሥራ አስፈፂሚዎች በወጣው የሥራ መመሪያና ደንብ መሰረት መስራታቸውን ይቆጣጠራል፣
13.1.10 የማህበሩ ሰብሳቢ ለአመቱ የወጡትን እቅዶች ከሥራ አስፈፃሚው ጋር በመሆን ተገምግመው በሥራ ላይ እንዲውሉ ያፀድቃል፣
13.1.11 ሰብሳቢ  የወጡትን እቅዶች መተግባራቸውን በመደበኛ እና እንደአስፈላጊነቱ ልዩ ስብሰባ  በመጥራት ተፈፃሚነታቸውን ይገመግማል፣ ውሳኔ ያስተላልፋል፣ያፀድቃል
13.1.12 ለማህበሩ እድገትና መጠናከር ከሰ/ት/ቤቶችና ማህበራት ከቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ጋር በመነገጋገር ግነኙነት ይፈጥራል፣
13.1.13 ግማሽ እና ከግማሽ በላይ የሆኑ ስራ አስፈፃሚዎች በተገኙበት ሰብሰባውን የማካሄድና የማስወሰን ኃላፊነት አለበት፣
13.1.14 በከፍተኛ የሂሳብ ሰነዶች ላይ ይፈርማል ከብር 100 በታች በቋሚ ውክልና ለፀሐፊው እንዲያፀድቅ በደብዳቤ ያዛል፣
13.1.15 ከሥራ አስፈፃሚ አቅም በላይ የሆኑ ጉዳዩች ሲያጋጥሙ ሰብሳቢ  ለሰበካ ጉባኤ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
13.1.16 በማንኛውም ስብሰባ ወቅት በውሳኔ አሰጣጥ በኩል እኩል ድምጽ በሚሆንበት ጊዜ ሰብሳቢ  የደገፈው ሃሳብ ይፀድቃል፡፡

                            አንቀፅ 14

     14.የማህበሩ ጸሐፊኃላፊነት እና ተግባር፣

14.1 ተጠሪነቱ ለማህበሩ ሰብሳቢ ይሆናል፣
14.2 የጽ/ቤቱን አጀንዳዎች ከሰብሳቢ  ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣
14.3 ለሥራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ መኖሩን በውስጥ ማስታወሻ እና በቃል ያሳውቃል፣
14.4 የማህበሩ የተለያዩ ክፍሎች እንዲቀርብላቸው የሰጡትን አጀንዳዎች በቅደም ተከተል እንደ አስፈላጊነቱ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
14.5 የጽሕፈት ቤት ሥራዎችን ከስብሳቢው ጋር በመሆን ያከናውናል፡፡
14.6 በእያንዳንዱ የስብሰባ እለት ቃለ ጉባዔ ይይዛል፣ ተሰብሳቢዎች እንዲፈርሙ ያደርጋል፣ የተወሰኑ ውሳኔዎች ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል፣
14.7 በማህበሩ ሥር ያሉትን የተወሰኑ ክፍሎችን በበላይነት ያገለግላል፣
14.8 በማህበሩ መርሀ ግብር በመገኘት የዕለታዊ መርሐ ግብራት ይዘት ይቆጣጠራል፣
14.9 በሚመራቸው ክፍሎች የሥራ ድክመት ሲኖር ለሰብሳቢ  ሪፖርት በማድረግ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፣
14.10  ፀሐፊው ወጪን በተመለከተ ሰብሳቢ  እስከ 100 ብር ድረስ ቋሚ ውክልና ሲሰጠው በሰነድ  ላይ ይፈርማል፣
14.11 በበላይነት ሆኖ ከሚከታተላቸው ክፍሎች ያገኘውን የሦስት ወር ሪፖርት አጠቃሎ  ያቀርባል፣
14.12 ሰብሳቢ በሌለበት ጊዜ በውክልና ፀሐፊው የበላይ ሆኖ ይቆጣጠራል፣
14.13 የማህበሩ ወጭ እና ገቢ ደብዳቤዎች በመዝገብ እየመዘገበ ያስቀምጣል፣
14.14 በስብሰባ ጊዜ ስብሰባው በስዓቱ እንዲጀምር እና እንዲቋጭ ያደርጋል/የስብሰባ ስዓት ይቆጣጠራል፣
14.15 በአስፈላጊ ጊዜ እና በማህበሩ ዓመታዊ በዓል ላይ አጠቃላይ የማህበሩን ሪፖርት አርቅቆ ያቀርባል፣

       14.1. የስበካ ጉባዔ ተወካይ ዓላማው፣

14.1.1 በሰበካ ጉባኤ ምርጫ ጊዜ የማህበሩ  ስራ አስፈፃሚ ሁለት እጩወች ያቀረርባል ዓላማውም ማህበሩ ተጠሪነቱ ለስበካ ጉባዔ እንደመሆኑ በማህበሩ ጽ/ቤት በኩል ወደ ሰበካ ጉባዔ ዕውቅና እንዲኖራቸው የሚታዘዙ ጉዳዮችን፣ማህበሩን ወክሎ ስብሰባዎችን፣እንዲሁም ከሰበካ ጉባዔ ወደ ማህበሩ የሚመጡ ውሳኔዎችን ለማህበሩ ማቅረብ እና ወዘተ.. የመሳሰሉትን በመሥራት የማህበሩን ፍላጐት ማሟላት ናቸው፡፡

ተግባር፡-
1  ተጠሪነቱ ለበሰበካ ጉባኤ ይሆናል፣
2  ተወካዩ የሥራ አስፈፃሚው ያላመነበትን እና ያላፀደቀውን ጉዳይ ወደ ሰበካ ጉባዔ ሊወስድ አይችልም፣
3 ማህበሩን ወክሎ በሰበካ ጉባዔ ስብሰባ ላይ ይካፈላል፣ የሚሰጡ ውሳኔዎችንም ለጽ/ቤቱ በሰዓቱ ያቀርባል፣
4 ከማህበሩ ወደ ሰበካ ጉባኤ የሚደርሱ አጀንዳዎችንና ሥራዎችን በሰዓቱ ያቀርባል፣
5 እነዚህን ተግባራት መፈጸም ካልቻለ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ በጽ/ቤት በኩል ለሰበካ ጉባኤ እንዲቀርብ ያደርጋል፣  
   
          <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

  እኛን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ባሉት አድራሻዎች ያግኙን፡

            በኢሜይል አድራሻችን፡ markachew.mb@gmail.com

   በስልክ አድራሻችን፡ 0918475307

 

Comments