✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቅ ንጉሥ "አፄ ገብረ መስቀል" እና "ቅዱስ አካክዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችህ ✞✞✞
" ኅዳር 30 "
+"+ ጻድቅ አፄ ገብረ መስቀል +"+
=>የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ነገሮቿ የታደለች ናት:: ከእነዚህም መካከል በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ነገሥቶቿ (መሪዎቿ) ቅዱሳን (ጻደቃን) ናቸው:: ለአንዲት ሃገር የመሪዎቿ ጥሩ ክርስቲያን መሆን እጅግ ወሳኝ ነው::
+ባለፉት 40 ዓመታት እንኩዋ የደረሰብንን የመንፈስ ዝለትና የሞራል ዝቅጠት ስንመለከት አንድም ችግሩ ከመሪዎቻችን እንደ ሆነ እናስተውላለን:: የሃገራችንን ታሪክ ስንመለከት ግን በእሳትና በጦርነት መካከል ሆነው ለፈጣሪ የተገዙ ብዙ ነገሥታትን እናገኛለን::
+እንደ ምሳሌም:-
1.ንግሥተ ሳባ
2.ቀዳማዊ ምኒልክ
3.አብርሐ ወአጽብሐ
4.ካሌብ
5.ገብረ መስቀል
6.ሐርቤ
7.ላሊበላ
8.ይምርሐ
9.ነአኩቶ ለአብ
10.ዳዊት
11.ቴዎድሮስ ቀዳማዊ
12.ዘርዓ ያዕቆብ
13.በእደ ማርያም
14.ናዖድ
15.ልብነ ድንግል
16.ገላውዴዎስ
17.ዮሐንስ
18.ኢያሱ ቀዳማዊና
19.ተክለ ሃይማኖት መናኔ መንግሥትን እናገኛለን::
+ከእነዚህ መሪዎቻችን መካከል እኩሉ መንግስታቸውን ትተው በርሃ የገቡ ሲሆኑ እኩሉ ደግሞ በዙፋናቸው ላይ ሳሉ በጐ ሠርተው የተገኙ ናቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ በጥፋታቸው ተጸጽተው ንስሃ የገቡ ናቸው::
+ከነገሥት ጻድቃን መካከልም ይህች ዕለት የአፄ ገብረ መስቀል መታሰቢያ ናት:: ጻድቁ ንጉሥ የአፄ ቅዱስ ካሌብ ልጅ ሲሆን በኢትዮዽያ የነገሠው በ515 ዓ/ም ነው:: ሲነግሥም እጅግ ወጣት ነበረ:: ምክንያቱም አባቱ ካሌብ ከናግራን ጦርነት መልስ በመመነኑ በዙፋኑ የተቀመጠ ልጁ እርሱ ነበርና::
+ከዚህ ቅዱስ የመጀመሪያ የምናደንቀው ስሙን ነው:: የዛሬ 1,500 ዓመት እንኩዋ በመስቀል የሚመኩ: ለመስቀል የሚገዙ መሪዎች መኖራቸው በዘመኑ የነበረውን የክርስትና ደረጃ ያሳያል:: "ገብረ መስቀል" ማለት "የመስቀል አገልጋይ (ባሪያ)" ማለት ነውና::
+አፄ ገብረ መስቀል በጐ ንጉሥ እንዲሆን የቅዱስ አባቱ ማንነት የረዳው ይመስላል:: ያ ኃያል: ብርቱና ዓለም የፈራው አባቱ ሲጀመር በፍቅረ ክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር የተያዘ ደግ ሰው መሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስቱን እንደ ጨርቅ ትቶ ሲሔድ መመልከቱ እርሱንም ያው አድርጐታል::
+እርሱም ከአባቱ እንዳየው በአክሱም ላይ በነገሠባቸው ዓመታት በጾምና በጸሎት: ፍትሕ ርትዕ ሳደያጉዋድል: ድሃም ሳይበድል ይኖር ዘንድ ጥረት አድርጉዋል::
+"+ አፄ መስቀል +"+
=>ይህ ጻድቅ ንጉሥ ለእኛ ከተወልን ትሩፋቶቹ አንዱ በዓለ መስቀልን በአደባባይ ማስከበሩ ቅድሚያውን ይይዛል:: በዓሉ መስከረም አካባቢ የሚደረግ ሲሆን "አፄ መስቀል" ይባላል::
+ሕዝቡ: ካህናቱና መሳሣፍንቱ አድዬ አበባ እየዘነጠፉ ወደ ንጉሡ አደባባይ ይተማሉ:: በዚያም በያሬድ ዝማሬ
ለቅዱስ መስቀሉ ታላቅ በዓል ይከበራል:: ይህ በዓል ይኼው ዛሬ በUNESCO ተመዝግቧል::
+"+ ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ +"+
=>ሃገራችን ታላቁን ሰማያዊ ዜማ ያገኘችው በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ነው:: ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ ያገኘውን ማኅሌት ለመጀመሪያ ጊዜ በአክሱም ጽዮን:- "ሃሌ ሉያ . . .! ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ:: ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ::" ብሎ ከ3ቱ ጸዋትወ ዜማ በአንዱ በአራራይ
ሲያዜም ንጉሡ በዜማው ተመስጦ እየሮጠ ወደ ጽዮን ደርሷል::
+ከዜማው ጥፍጥና (ጣዕም) የተነሳ ሁሉም ተደመሙ:: ንጉሡም ከዚያች ቀን ጀምሮ ከቅዱስ ያሬድ የማይለይ ሆነ:: ስብሐተ እግዚአብሔርንም ለብዙ ጊዜ ከቅዱሱ ሊቅ በጥዑም ዜማ ተቀምሞለት ተመገበ::
+እንዲያውም አንዴ ሊቁ ሲያዜምለት ጻድቁ አፄ ገብረ መስቀል የቅዱስ ያሬድ እግር ላይ በትረ መንግስቱን ተክሎበታል:: ሁለቱም ከተመስጧቸው ሲነቁ ግን ንጉሡ
ደንግጦ "ምን ልካስህ?" ቢለው "ወደ በርሃ አሰናብተኝ" አለው::
+አፄ ገብረ መርስቀልም እያዘነ ፈቅዶለታል:: ቅዱስ ያሬድም ከመሬት ክንድ ከፍ ብሎ ተንሳፎ: የመሰናበቻ
ምስጋናን:- "ውዳሴ ወግናይ: ለእመ አዶናይ: ቅድስት ወብጽዕት . . ." ብሎ አንቀጸ ብርሃንን: በሚጣፍጥ ዜማ ሰተት አድርጐ አደረሰ:: ይህንን ሲሰማ ንጉሡ ፈጽሞ አለቀሰ::
+እስከ መንገድ ድረስ ከሕዝቡና ሠራዊቱ ጋር ከሸኘው በሁዋላም ቅዱስ ያሬድ ጸለምት ላይ ሲደርስ በዜማ አሰምቶ "ሰላም ለኩልክሙ" አለ:: አፄ ገብረ መስቀልና ሕዝቡም "ምስለ መንፈስከ" ብለውት ቀና ሲሉ ከዓይናቸው ተሰወረ:: ንጉሡም በዘመኑ ማኅሌተ ሰማይ እንዲስፋፋ ብዙ ጥሯል::
+"+ ንጉሡና 9ኙ ቅዱሳን +"+
=>ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ወንጌልን እንዲሰብኩ: መጻሕፍትን እንዲተረጉሙና ገዳማዊ ሕይወትን እንዲያስፋፉ አፄ ገብረ መስቀል ትልቅ ጥረት አድርጉዋል::
+በተለይ ከአባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል ጋር ልዩ ቅርበት ነበረው:: ዘወትርም ከእነርሱ ይባረክ ነበር:: አቡነ አረጋዊንም በየጊዜው ይጐበኛቸው እንደ ነበር ይነገራል::
+"+ ንጉሡና ታቦት +"+
=>ልክ እንደ ቅዱስ መስቀሉ ሁሉ ታቦተ እግዚአብሔር
በዑደት እንዲከበር ያደረገ ይህ ንጉሥ ነው ይባላል:: መነሻው ደግሞ የደብረ ዳሕሞ መታነጽ ነው:: አንድ ቀን አቡነ አረጋዊን ምን እንደሚሹ ቢጠይቃቸው
"የድንግል እመቤታችን ማርያምን መቅደስ አንጽልኝ" አሉት::
+በደስታ አንቆጥቁጦ አነጻት:: የምርቃቱ ዕለትም ንጉሡ: ጻድቁና ሊቁ (ማለትም ገብረ መስቀል: አረጋዊና ያሬድ) ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ተገኙ:: በጊዜውም ታቦቱ ሲነግሥ ቅዱስ ያሬድ ባቀረበው ማኅሌታዊ ዜማና አበው ባደረጉት
ዝማሬ: ታቦቱ እየዞረ ታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ሆነ::
+ደብረ ዳሞ ያኔ መወጣጫ ደረጃ ነበረው:: ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ ከበዓል ሲመለሱ በአቡነ አረጋዊ ጥያቄ መወጣጫው ተደርምሷል::
+ጻድቁ "ዳሕምሞ (ደርምሰው)" ስላሉት ቦታው ዳሕሞ (ዳሞ) ተብሎ ቀርቷል:: ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::
+"+ ቅዱስ አካክዮስ +"+
=>ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: ተወልዶ ያደገው በቁስጥንጥንያ
ሲሆን ትምሕርተ ሃይማኖትንም እዚያው ተምሯል:: በ451 ዓ/ም ጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ አብዳን) ሲጠራ እሱም ጥሪ ደርሶት ነበር::
+ነገር ግን ከመጀመሪያው ንጉሡ መርቅያንና ዻዻሱ ልዮን የተበተቡትን ሴራ ያውቅ ነበርና ሳይሔድ ቀረ:: ጉባኤው ተጠናቆ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ መገደሉንና ሃይማኖት መካዱን (በተሰብሳቢዎቹ) ሲሰማ አዘነ::
+ንጉሡን ረግሞ "ጌታ ሆይ! ከዚህ ከረከሰ ጉባኤ ያልደመርከኝ ተመስገን" አለ:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላም ምዕመናን ሃይማኖቱ የቀና መልካም እረኛ
መሆኑን ሲረዱ የታላቂቱ ቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::
+ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ:: ወዲያው ግን ከመሪዎች ተዋሕዶን እንዲተው ትዕዛዝ መጣለት:: እንቢ በማለቱም ስደት ተፈርዶበት በስደት ላይ ሳለ ዐርፏል::
=>አምላከ ነገሥት ጻድቃን ቅኑን መሪ በሁሉም ሥፍራ ያድለን::ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::
=>ኅዳር 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አፄ ገብረ መስቀል ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ አካክዮስ ሊቅ
3.ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ
4.ቅዱስ አናንዮስ ዘዓምድ
5.አባ መርቆሬዎስ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
++"+ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ
እጅግ ሐሴትን ያደርጋል::የልቡን ፈቃድ
ሰጠኸው::የከንፈሩንም
ልመና አልከለከልኸውም::በበጐ በረከት
ደርሰህለታልና::ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ
አኖርህ::ሕይወትን ለመነህ
ሰጠኸውም::ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ::በማዳንህ ክብሩ
ታላቅነው:: +"+ (መዝ. 20:1-5)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethellettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━
Comments
Post a Comment