✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ነገሥታት "አብርሃ ወአጽብሃ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ "*+
=>እነዚህ ነገሥታት ሞገሶቻችን: ብርሃኖቻችን ናቸውና ደስ እያለን እንወዳቸዋለን: እናከብራቸዋለን:: ሥላሴ
ቢመርጧቸው ዛሬ ላለንበት ሕይወት መሠረቱን ጥለው
አልፈዋልና::
+2ቱ ቅዱሳን ነግሥታት መንትያዎች ሲሆኑ ወላጆቻቸው (ንጉሥ ታዜር - አይዛና - ሠይፈ አርዕድ) እና (ንግሥት አሕየዋ - ሶፍያ) ይባላል:: ንጉሡና ባለቤቱ ልጅ ቢያጡ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ:: ፈጣሪም በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት 2 ዕንቁዎችን አስረከባቸው::
+ንግስት አሕየዋ (ሶፍያም) መጋቢት 29 ቀን በ311 ዓ/ ም ጸንሳ : ታሕሳስ 29 ቀን በ312 ዓ/ም 2ቱን ቅዱሳን ወልዳቸዋለች:: "አምላክ ሽሙጥን አራቀልኝ" ስትልም "አዝጉዋጉ" ብላቸዋለች:: እነዚህ 2 ፍሬዎች
በልጅነታቸው ከወቅቱ ሊቀ ካህናት እንበረም ኦሪቱን
ጠንቅቀው ተምረዋል::
+ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸውና በ12 ዓመታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ገብተዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን አባታቸው ታዜር በማረፉ ሕዝቡ 2ቱን ቅዱሳን "ንገሡልን" አሏቸው:: እነርሱም "እኛ የፈጣሪ አገልጋዮች ነንና አንችልም" በማለታቸው ለተወሰነ ጊዜ እናታቸው አስተዳደረች::
+ቆይቶ ግን ቅዱስ ሚካኤል ለሊቀ ካህናቱ እንበረም
"የፈጣሪ ፈቃዱ ስለ ሆነ አትዘኑ:: 2ታችሁም በአንድ ዙፋን ላይ ንገሡ:: ታላቅ ጸጋ ለሃገሪቱ ይሆናል በላቸው" አለው::
+ሊቀ ካህናቱም የታዘዘውን ተናግሮ: በ19 ዓመታቸው:
2ቱንም በአንድ ዙፋን ላይ "ነገሥተ ኢትዮዽያ" ሲል
አስቀምጦ ቀባቸው:: ስማቸውን "ኢዛና" እና "ሳይዛና"
አላቸው:: ቅዱሳኑ እንደ ነገሡ ቀዳሚ ሥራቸው
የቀናችውን ሃይማኖት መፈለግ ሆነ::
+በወቅቱ ፍሬምናጦስ (የሁዋላው አቡነ ሰላማ) በቤተ
መንግስቱ ውስጥ የቅርብ አማካሪ ነበርና ጠርተው
ተጨዋወቱት:: "አንተ ወንድማችን! ክርስቶስ ይወርዳል:
ይወለዳል ተብሎ የተቆጠረው ሱባኤ እኮ አልፏል:: ምነው ቀረሳ? በርግጥ ምሥጢሩ ንገረን" አሉት::
+እርሱም አትቶ: አመሥጥሮ: ከ300 ዓመታት በፊት
አምላክ ሰው መሆኑንና ዓለምን ማዳኑን አስተማራቸው::
"አጥምቀን?" ቢሉት "አልችልም" አላቸው:: እነርሱም
ከብዙ ስጦታ ጋር ወደ ግብጽ ላኩት::
+ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "አቡነ ሰላማ" ብሎ ከብዙ መጻሕፍት ጋር ላከው:: በመጀመሪያ ኢዛናና ሳይዛና ተጠመቁ:: ስማቸውም "አብርሃ ወአጽብሃ" ተባለ:: ቀጥሎም ሠራዊቱና ሕዝቡ ተጠመቀ::
+ሃገራችንም በእነዚህ ቅዱሳን አማካኝነት ከጨለማ ወደ ብርሃን መጣች:: የክርስትና ደሴት ሆነች:: ሃገረ
እግዚአብሔርነቷንም አጸናች:: ቅዱሳኑ ከዚህ በሁዋላ
በሞገስ ክርስትናን ያስፋፉ ዘንድ ደከሙ:: ከ154 በላይ
አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጹ አብዛኞቹ ፍልፍል ነበሩ::
+በተለይ ግን በአክሱም ከተማ ላይ ያነጿትና 12 ቤተ
መቅደሶች የነበሯት የጽዮን ቤተ ክርስቲያን ልናያት
ትናፍቀናለች:: ጌጧ: ብርሃኗ ውል ውል ይልብናል::
ይህቺው ቤተ ክርስቲያን በ10ኛው ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት በእሳት አውድማታለችና:: መሠረቱ ግን ዛሬም አለ::
+ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ ግን ክርስትናን ለማስፋፋትና መንግስትን ለማጽናት ሲሉ ከአክሱም በተጨማሪ በሽዋም ዙፋንን ዘረጉ:: ለብዙ ዓመታትም አምላክ በፈቀደው መንገድ እስከ የመን ድረስ ገዙ:: ክርስትናንም አስፋፉ::
+ቅዱስ አብርሃ በተወለደ በ52 ዓመቱ: በ364 ዓ/ም
ጥቅምት 4 ቀን ሲያርፍ ወንድሙ ለ15 ዓመታት ብቻውን አስተዳድሯል:: በ379 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ በጥቅምት 4 ቀን ቅዱስ አጽብሃም በተወለደ በ67 ዓመቱ በክብር ዐርፏል::
+ከሁለቱም መቃብር ላይ ለ30 ቀናት የብርሃን ምሰሶ
ተተክሎ ታይቷል:: ጌታችንም በማይታበል ቃሉ "ስማችሁን የጠራውን: መታሰቢያችሁን ያደረገውንም እምርላቹሃለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::
=>አምላከ አብርሃ ወአጽብሃ "ድሃ ተበደለ: ፍርድ
ተጉዋደለ" የሚል ዳኛ: ሃይማኖቱ የቀና መሪንም
ያምጣልን:: የቅዱሳኑን ክብር በእኛ ላይ ያድርግልን::
=>+"+ እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና
በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና
ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ
ነገሥታትና መኩዋንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት
እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ
ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት
መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው:: +"+ (1ጢሞ.
2:1-4)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment