✝✝✝ እንኳን አደረሳችሁ ✝✝✝
+*" ቅዱስ አልዓዛር "*+
=> ሳምንት ይህች ዕለተ ረቡዕ "አልዓዛር"
ትባላለች:: ጌታችን ከሙታን ስላስነሳው ዕለቷ የሐዋርያው
መታሰቢያ ሆናለች::
+ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ
ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው
ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት
ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት
ቆጥሯቸዋል::
+በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ
አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ
የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው
እንጂ::
+ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት
በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ
ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ
ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::
+ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ
ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል::
(ዮሐ. 11)
ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው
ይመጣል::
+ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው
ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር
ተቀበለችው::
+"አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ
"አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ
ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
+ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ
አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ
ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ
እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)
+ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ
መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት
ነውና) : ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ : በ74 ዓ/ም
አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::
=>የጌታችን ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::
=>+"+ ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር
እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት . . . ይሕንም ብሎ
በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ::
የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ::
ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም
'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው:: +"+ (ዮሐ. 11:40-44)
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Comments
Post a Comment