✞✝✞ ሚያዝያ 18 ✞✝✞
✞✝✞ እንኩዋን ለጻድቅና ሰማዕት "አባ ዼጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✝✞
*+" ጻድቅና ሰማዕት አባ ዼጥሮስ "+*
=>ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል
የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው
ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል::
ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት
ነው::
+ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል::
የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ
ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ
መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::
+እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ
ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ
ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን
የሚመለከት ሕግ የለውም::
+እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን
መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ.
5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና
በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም
የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ
ይመጣል::
+በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል
ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን
እንድንጸና ነውና::
❖ቅዱስ አባ ጴጥሮስም ከዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች አንዱ
ነው፡፡ በዚያ የመከራ ዘመን (3ኛው መቶ ክ/ዘ) ግብፅና
ሶርያ በብዙ መከራ ውስጥ ሳሉ በርካታ ቅዱሳን
ተሰውተዋል፡፡ በተለይ በግብፅ ደግሞ ብዙ ንጹሐን አበውና
ቅዱሳት አንስት መከራውን ታግሠው ለክብር በቅተዋል፡፡
❖ከእነዚሁ አንዱ የሆነው አባ ጴጥሮስ ገና ከልጅነቱ
ጣዕመ ክርስትናን የተማረው ከአሳዳጊው (ከአክስቱ)
ነበር፡፡ በፍፁም ልቡ የሚወደው ወንድም እና ባልንጀራም
ነበረው፡፡ ስሙ ደግሞ አባ ብሶይ ይሰኛል፡፡ ሁለቱም በበጎ
ምግባር ተኮትኩተው ፡ ዓለምንም ንቀው በርሃ ገብተው ፡
በጾም በጸሎት ተወስነው ብዙጊዜ ኑረዋል፡፡
❖በመከራው ዘመን ደግሞ ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ
ተከሰው ታስረዋል፡፡ ተገርፈው ተደብድበዋል፡፡ ጭንቅ
ስቃይንም በትእግስት አሳልፈዋል፡፡ በፍጻሜውም አባ
ጴጥሮስ በዚህች ቀን ተሰውቶ ለክብር አክሊል በቅቷል፡፡
ወዳጁና ወንድሙ ቅዱስ ብሶይም በክብር ገንዞ
ቀብሮታል፡፡
=>አምላከ ሰማዕታት ከጸናች ገድላቸው ፡ ከበዛች
ትእግስታቸው ፡ ከፍጹም በረከታቸው ያሳትፈን፡፡
=>ሚያዝያ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት
2.አባ ዼጥሮስ ሰማዕት
3.ሰማዕታተ ጠርሴስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
=>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር:
አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት:
ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ
ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . .
የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ
የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ
11:23)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Comments
Post a Comment