† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ሚያዝያ ፬†
† ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት) †
=>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ አራት በዚች ቀን የከበሩ ፊቅጦርና ዳኬዎስ ኤርሞ ሌሎችም ብዙዎች ሰዎች ሴቶችና ወንዶች ደናግሎች በሰማዕትነት ሞቱ።
እሊህም ቅዱሳን በታላቁ ቈስጠንጢኖስና በልጁ ዘመነ መንግስት የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰው ጣዖታትንም ሰብረው አቃጥለው በቦታቸውም አብያተ ክርስቲያናትን ሠርተው አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሌሎችም በብዙዎች ቅዱሳን ስም ታቦቱን ሰይመው ነበር።
ከሀዲ ዮልያኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቆመ የጣዖቱንም ካህናቶች አከበራቸው ብዙዎች ክርስቲያኖችንም አስገደለ።
የእሊህ ቅዱሳን ዜናቸው አስቀድሞ በጣዖታት ቤቶች ላይ ያደረጉት ጣዖታትን እንደሰበሩ ሁሉ ተሰማ።ይዘውም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው ብዙ ቀንም ሲሰቅሏቸውና ሲገርፉአቸው ቆዳቸውንም በሾተል ሲነጥቁ ኑረው በኃላም ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ቆረጡ።
በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ በረከታቸው ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
=>ሚያዝያ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት=
1.እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፈጠረ
2.ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሐ (ጻድቃን ነገሥት)
3.ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው)
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
=>+"+ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ:: በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው:: ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው . . . እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ:: እነሆም እጅግ መልካም ነበረ:: +"+ (ዘፍ. 1:26-31)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━⊱✿⊰━━
Comments
Post a Comment