✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቅ ሰው "አባ ሳሙኤል
ዘቆየጻ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞✞✞
+*" አባ ሳሙኤል ዘቆየጻ "*+
=>በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን
(በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ
ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::
+ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው
ነው::
+በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር::
ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት
አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና
ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት
አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::
+ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው:
መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው
እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ
ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ
የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ
ይባላል::
=>ከ7ቱ ከዋክብት አንዱ የሆኑት የቆየጻው አባ ሳሙኤል
የመድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዝሙር ናቸው:: ፋሾ ውስጥ
(ትግራይ አካባቢ) ተወልደው : እንደሚገባ አድገው :
መጻሕፍትን ተምረው ደብረ በንኮል ገብተዋል::
+በዚያም ከ6ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር የምናኔን ምሥጢርና
ተጋድሎን አጥንተው በመነኮሱበት ቀን ብርሃን
ወርዶላቸዋል:: በጻድቁ መምህራቸው ለአገልግሎት
ሲላኩም ለእርሳቸው ቆየጻ (ትግራይ) ደርሷቸዋል::
+በዚያም በጾም በጸሎት እየተጉ : ስብከተ ወንጌልን
እያስፋፉ : ደቀ መዛሙርትን እያፈሩ ለዘመናት ኑረዋል::
አባ ሳሙኤል በተለየ መንገድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይጽፉ
ነበርም ይባላል::
+በጊዜው 72ቱ ከዋክብት (70ው ሊቃናት) ከሚባሉ
አበው ጋር በመተባበር 4ቱ ወንጌል በብራና : በልዩ ጌጥ :
በ120 ሐረግ : በ4 ዓምድ ተጽፏል:: ያንንም ወስደው
በመቃብራት አካባቢ ቢያስቀምጡት 211 ሰዎች ከሞት
ተነስተዋል::
+"ማን አስነሳችሁ?" ሲባሉም "አምላከ ጻድቃን ወሰማዕት
: ወአምላከ ሳሙኤል ጻድቅ" ሲሉ መስክረዋል:: ይህን
ወንጌል ሲጽፉም ቅዱሳን መላእክት ረድተዋቸዋል::
+ጻድቁ አባ ሳሙኤል ዘቆየጻ ከብዙ ድካምና ተጋድሎ
በሁዋላ እዚያው በገዳማቸው ዐርፈዋል::
መቃብራቸውንም 5 አናምርት (5 ነብሮች) ቆፍረውላቸው
ተቀብረዋል::
(ስዕሉ የአባ ሳሙኤል ዘቆየጻ ነው)
=>አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ በረከት ይክፈለን::
=>+"+ በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው:: የኃጥአንን አፍ
ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሠቢያ ለበረከት ነው::
+"+ (ምሳ. 10:7)
=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━
Comments
Post a Comment