Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

የዐቢይ ጾም 8ተኛ ሳምንት ሆሣዕና

 

የዐቢይ ጾም 8ተኛ ሳምንት ሆሣዕና 

#ሆሣዕና (#በዓለ_ተፂዕኖ) (#የፀበርት_እሑድ) #ወሥርዐተ_ማኅሌት

፠ የሰሙነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን፤ የዐቢይ ጾም ስምንተኛውና የመጨረሻው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል፤
፠ በዕብራይስጡ ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን ትርጕሙም ‹‹እባክህ አሁን አድን፤ አንድም መድኀኒት›› ማለት ነው፡፡ በትንቢተ ዘካርያስ ላይ በአህያ ላይ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (በግእዙ ተፂዕኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ኢየሩሳሌም በክብር) ስለሚል በአብዛኛው የሃገራችን ክፍል
ከጥንት ጀምሮ በዋነኛነት ‹‹የተፂዕኖ በዓል›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንዲሁም ዘንባባ በግእዙ ፀበርት እየተባረከ ስለሚሰጥ ‹‹የፀበርት እሑድ›› ይባላል፡፡
፠ በዚህ ዕለት ጌታችን የማዳን ሥራውን ወደሚፈጽምባት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡... ቤተ ፋጌ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ‹‹ያስፈልጉኛልና የታሠሩትን አህያና ውርንጫ ይዛችሁልኝ ኑ፡፡›› ብሎ ላካቸው፡፡
በምስጢሩም የአዳምን ልጆች ከዲያብሎስ ቁራኝነት ሊፈታ እንደ መጣ ለማጠየቅ ነው፡፡ እነርሱም እንደታዘዙት አመጡ፤ እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲሆን 14ቱን በእግሩ፣
2ቱን ምዕራፍ (ከደብረ ዘይት ተራራ አካባቢ አንስቶ እስከ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ) በአህያ ሄዶ፣ ቤተ መቅደሱን 3 ጊዜ በውርንጫላዋ ከዞረ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡

#ለምን_ጌታችን_በአህያ_ውርንጫ_ተቀምጦ_ወደ_ቤተ_መቅደስ_ገባ
* ቀድሞ በነቢያት ዘመን ጸብዕ (ጥል) በሆነ ጊዜ በፈረስ ተቀምጠው፥ የጦር ዕቃ ይዘው፥ ዘገር ነቅንቀው፥ ጦር ሰብቀው፥ (ነጋሪት እያጎሰሙ፥ መለከት እያስነፉ) ይታዩ ነበር፤ ዘመነ ሰላም፥ ዘመነ ምሕረት በሆነ ጊዜ ደግሞ በአህያ ተቀምጠው፥ መነሳንስ ይዘው ይታያሉ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በነቢያት ሥርዐት ‹‹ዘመነ ሰላም ይዤላችሁ›› መጣሁ፤ በ7ቱ መስተጻርራን /ተጣልጠው የነበሩ/ (በሰውና በእግዚአብሔር ፣ በሰውና በመላእክት፣ በሥጋና በነፍስ፣ በተገዘሩት በሕዝበ እሥራኤልና ቆላፍ በሆኑት በአሕዛብ መካከል) የነበረው ጠብ ማብቃቱን ለመግለጥ እንዲሁም በነቢያት የተተነበየውን ሊፈጽም፤ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ 117፥25-26 ‹‹በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፡፡›› ብሏል፤ ነቢዩ ዘካርያስም በትንቢቱ በአህያ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር ‹‹የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡›› /ዘካ. 9፥9/፡፡
* ጌታችንም ኢየሩሳሌምን ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላሟን አውጆላታል፤ በሌላ አንቀጽም ከተማይቷን እየተመለከተ አልቅሶላታል፡፡(ስለ ሰላምሽ የሚሆነውን አንቺስ ብታውቂ … … ፡፡) /ሉቃ. 19፥24/፡፡

*  የተዋረደች እንስሳ (አህያም) በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ መቀመጫ አደረጋት፤ ሸክም ያቆሰላት፥ ዱላ የሰለቻት፥ ዕረፍት የናፈቃት ‹‹ቀንበሬ ልዝብ፥ ሸክሜ ቀላል ነው›› ያለ ንጉሥ ተቀመጠባት፡፡

#ለምን_የዘንባባ_ዝንጣፊ (ፀበርት)፤ (የቴምር ዛፍ ዝንጣፊና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ) ይዘው #ዘመሩ
* በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባም ደቀ መዛሙርቱና በግራና በቀኝ የነበሩ ሕዝቦችም ‹‹እንኳን አንተ የተቀመጥክባትም አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም›› እያሉ ግማሹ ልብሱን፥ ግማሹ የዘንባባ ዝንጣፊ አነጠፉለት፤ ክብሩንና መድኀኒትነቱን ገለጡ፡፡
* አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ፣ እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ዮዲት ሃገሯን ሊወር የመጣውን ሆሎፎርኒስ የተባለ የአይሁድ ንጉሥ በገደለች ጊዜ ዘንባባ ይዘው አመስግነው ነበር፤ በዚያ ልማድ ጌታችንንም ዘንባባ ይዘው ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፥ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፥ ሆሣዕና በአርያም›› /መዝ. 8፥2፣ ሉቃ. 19፥38/ እያሉ አመሰገኑት፤ ዘመን የተቈጠረለት፥ ምሳሌ የተመሰለለት፥ ትንቢት የተተነበየለት፥ ምሥጢር የተመሠጠረለት የዳዊት ልጅ፤ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን መሰከሩ፡፡
* አይሁድም ሕፃናት ሲያመሰግኑ ሰምተው በቅንአት በታወረ ልቦናቸው ‹‹ዝም አስብላቸው እንጂ›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ አፍ ምስጋና ለራስህ አዘጋጀህ›› /መዝ. 8፥2/ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል ጠቅሶ አሳፍሯቸዋል፡፡ በሌላም አንቀጽ ዝም በሉ እያሉ ሊያስቆሙ ሲሞክሩ የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው አመስግነውታል፤ ይህንንም ተመልክተው አፍረዋል፡፡
* አንድም ዘንባባ እሾኻም ነው የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤

* አንድም ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ፤
* አንድም ዘንባባ ረጅም (ልዑል) ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ አንጥፈው ተቀብለውታል፡፡
* አንድም ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፤ አንተም የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ፤
* ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ፤
* ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ፡፡

፠ ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በዚያ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ በመቆጣት የለዋጮችን ገበታ እየገለበጠ አስወጣቸው፡፡
፠ ይህ በዓል ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡ እኛም የዕለቱን ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡
፠ ታሪኩ በነቢያት መጻሕፍትና በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ይገኛል፡፡ (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)፨

       


             ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam

                    ━━⊱✿⊰━━

Comments