Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ጥር ፩

በእንተ ስማ ለማርያም:
✝✝" #ጥር 1 "

✝<<< እንኩዋን ለቅዱስ "እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት" እና "ለአክሚም ሰማዕታት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ >>>✝

+*" ✝ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ✝ "*+

=>በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::

+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን : ዻውሎስን : ናትናኤልን : ኒቆዲሞስን . . .) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::

+በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::

+ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ  የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::

"ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18)

በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: (ሉቃ. 10:17)

ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ::
ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ
ባርኳል:: በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ
አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት:ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን
ይሰብክ ገባ::

በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7
ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል:: 8ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው::

አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር' ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5) አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም::

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማኅበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ'
አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል
ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት::

+እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ
እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ
ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::

*"ፍልሠት"*

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመታት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም
ሉክያኖስ ይባል ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን
አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም ደስ ብሎት
ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል (የመምሕሩ ርስት ነው) ሔደ::

+ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ:: መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ መላእክትም
ተሰማ:: ሕዝቡና ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ
ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ ጽዮን (በተቀደሰችው
ቤት) አኖሩት::

እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ
ክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ5 ዓመታት በኋላም እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን
ስለ ፍቅሩ አኖሩት::ሚስቱ ወደ ሃገሯ ቁስጥንጥንያ ስትመለስ
የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ
በመርከብ ጭና ወሰደችው:: መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ
ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ አላት: አምላክ ለዚህ አድሏታልና::

እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም ታላቅ ሐሴት ተደረገ::ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ
በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች:: በዚያም ላይ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ
ሲመቱ ጥቅምት 17: ዕረፍቱ ጥር 1:ፍልሠቱ ደግሞ መስከረም 15 ቀን ነው::

'' ሰማዕታተ አክሚም ''

+በቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከተካሔደባቸው አካባቢዎች አንዷ ሃገረ አክሚም ናት::
አክሚም ማለት የቀድሞ የግብጽ አውራጃ ናት:: በተለይ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በርካታ ክርስቲያኖች በፍቅር ይኖሩባት
ነበር::

በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ጥቡዓን: ታማኞች:ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉና ዘወትር ቅዱስ ቃሉን ለመስማት የሚተጉ ነበሩ:: ለዚህም ደግሞ ከሊቀ ዻዻሱ አባ ብኑድያስ ጀምሮ ካህናቱ: ዲያቆናቱ: ንፍቅ ዲያቆናቱ: መጋቢዎቹ: አናጉንስጢሶቹ (አንባቢዎቹ): መምሕራኑ: መሣፍንቱም ሳይቀር ለክርስቶስ ፍቅር የተጉ መሆናቸው አስተዋጽኦ ነበረው::
በተለይ ግን 2 ወንድማማቾች የነበራቸው ቅድስና ብዙዎችን ስቧል:: እኒህ ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ ይባላሉ::

ከባለ ጸጋና ባለ ስልጣን ቤተሰብ ቢወለዱም ክርስትናቸው አልቀዘቀዘም:: የወጣትነት ስሜት ሳያሸንፋቸውም ወደ በርሃ ተጓዙ::

+በዚያም በቅድስና ኑረው ለክህነት ማዕረግ በቅተዋል:: ቅዱሳኑ በገዳም ሳሉም መድኃኒታችን ክርስቶስ ተገልጦ "ወደ ትውልድ ሃገራችሁ አክሚም ተመለሱ:: ክብረ ሰማዕታት ይጠብቃቹሃል" አላቸው:: እነርሱም ደስ እያላቸው በፍጥነት ወደ አክሚም ወጡ::በዚያ ሰሞን የጌና ጾም ተፈጽሞ
የአክሚም ክርስቲያኖች ለበዓለ ልደት ዝግጅት ሲያደርጉ በጠላት ሠራዊት ተከበቡ::ይህ ሠራዊት የተላከው ከርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ሲሆን መሪው ደግሞ አርያኖስ ነው:: ዋናው ተልዕኮው
ክርስቲያኖችን ለጣዖት ማሰገድ: እንቢ ካሉ ደግሞ መግደል ነው:: ክርስቲያኖቹ መከበባቸውን እያወቁ አልፈሩም:: ታኅሳስ 29 ቀንም ሁሉም የከተማዋ ክርስቲያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰበሰቡ::በዚያም ሊቀ ዻዻሱ ሥርዓተ ቅዳሴን አደረሱ::

ሁሉም በተመስጦ ይጸልዩ ነበርና የክብር ባለቤት ክርስቶስ በገሃድ ተገለጠላቸው:: በዓይናቸው እያዩም ሥጋ ወደሙን አቀበላቸው:: ቅዳሴው ሲጠናቀቅ ግን አርያኖስና ሠራዊቱ ደርሰው ሁሉንም ክርስቲያኖች ያዛቸው::

+ክርስቶስን ክደው ከመገደል እንዲድኑ ተጠየቁ:: እነርሱ ግን በአንድ ድምጽ "አይሆንም" አሉ:: በዚያን ጊዜ ወታደሮቹ በክርስቲያኖች አንገት ላይ በሰይፍ ይጫወቱ ያዙ::በተራ አሰልፈው ዻዻሱን: ካህናቱን: ዲያቆናቱን: አንባቢዎችን:መሣፍንቱን ሳይጨምር ከ16,000 በላይ ክርስቲያኖች ደማቸው ፈሰሰ:: የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ሞልቶ ደም ወደ ውጭ 20 ክንድ ያህል ፈሰሰ::

በክርስቲያኖች ላይ ግፍ ተፈጸመ::አካባቢውም ያለ ወሬ ነጋሪ ቀረ:: ግድያው ለ3 ቀናት ቀጥሎ ጥር 1 አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ ሲገደሉ ተጠናቀቀ::

✞አምላከ ሰማዕታት ፍቅረ ሃይማኖታቸውን ያሳድርብን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ጥር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት (ሊቀ ዲያቆናት)
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም
3.ቅዱሳን ዲዮስቆሮስ ወሰከላብዮስ
4.ቅዱስ ለውንድዮስ ሰማዕት
5.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት

 => ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

✞እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ
ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ
በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት:: (ሐዋ. 6:8-15)

    ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
        ✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
    ✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!። 

  "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn 
Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments