Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ጥር ፲፯


✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞

✞✞✞ ጥር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✝" አበዊነ መክሲሞስ ወዱማቴዎስ "✝

=>እኒህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ተወዳጅ አባቶች ናቸው:: ስንጠራቸውም "አበዊነ ቅዱሳን: ወክቡራን: ሮማውያን: መስተጋድላን: ወከዋክብት ብሩሃን" ብለን ነው::

+ይኸውም "እንደ ንጋት ኮከብ የምታበሩ: ተጋዳይ: ቅዱሳንና ክቡራን የሆናችሁ ሮማውያን አባቶቻችን" ማለት ነው:: ሃገረ
ሙላዳቸው ሮም ሁና አባታቸው ንጉሥ ለውንድዮስ ይባላል::

+ይህ ንጉሥ ሮምን በምታክል ታላቅ ሃገር በ4ኛው መቶክ /ዘመን ነግሦ ሳለ መልካም ሰው ሆኖ ተገኝቷል::
ከመልካም ሚስቱ (ንግሥቲቱ) ከወለዳቸው መካከልም 2ቱ ከዋክብት
ይጠቀሳሉ:: 2ቱ ቅዱሳን በአጭር የጊዜ ልዩነት የተወለዱ በመሆናቸው
እንደ መንትያ ይቆጠራሉ::

+ንጉሡ ለውንድዮስም ከእግዚአብሔር ዘንድ ላገኛቸው ልጆቹ ስም ሲያወጣ ታላቁን መክሲሞስ: ታናሹን ደግሞ
ዱማቴዎስ ብሎታል:: ቅዱሳኑ በንጉሥ አባታቸው መልካም ፈቃድ ክርስትናን ተምረዋል::

+ምንም እንኳ የንጉሥ ልጆች እና ልዑላን ቢሆኑም ተቀማጥለው አላደጉም:: ምቾት ብዙዎችን አጥፍቷልና:: ይህንን የተረዳ
አባታቸው ሞገስን በፈጣሪያቸው ዘንድ እንዲያገኙ እንዲህ በበጐ ጐዳና አሳደጋቸው::

+ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ካደጉና ለአካለ መጠን ከደረሱ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ ይተጉ ነበር:: በተለይ ዜና ቅዱሳንን ከማንበብ አይጠግቡም ነበር:: እግዚአብሔርንም በፍቅር እያመለኩ በጾምና በጸሎት
ይገዙለት ነበር::

+ቅዱሳኑንም ለየት የሚያደርጋቸው አንዱ ይሔው ነው:: ወርቅና ብር በፊታቸው ፈሶ: በእግራቸው እየረገጡት: አገሩና ምድሩ እየሰገደላቸው: የላመ የጣመ ምግብ እየቀረበላቸው: የሞቀ የደመቀ መኝታ እየተነጠፈላቸው . . . ሁሉንም ስለ ፍቅረ ክርስቶስ መናቃቸው ይደነቃል::

+እነርሱ በክርስቶስ ፍቅር ሆነው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀዋልና የአባታቸውን ቤተ መንግስት ሊተዉ አሰቡ:: አሳባቸው ደግሞ በመመካከር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንዲሉ አበው በጌታ መሪነት ነው::

+ወደ በርሃ ሔደው ለፈጣሪ ለመገዛት ሲያስቡ መውጫ መንገዳቸውን ይሹ ነበርና አንድ ጐዳና ተገለጠላቸው:: ከዚያም ለንጉሥ አባታቸው ሔደው "አባ! እኛ ወደ ኒቅያ (ታናሽ እስያ) ሔደን መባረክ እንፈልጋለን" ሲሉ ጠየቁት::

+ወቅቱ ቦታዋ ስለ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ሞገስን ያገኘችበት ጊዜ ነበር:: አባታቸውም መንፈሳዊ ሰው ነበርና ደስ እያለው ፈቀደላቸው:: ብዙ ወርቅን ሰጥቶ: ሸልሞ ከብዙ ሠራዊት ጋር ሸኛቸው::

+ቅዱሳኑ መክሲሞስና ዱማቴዎስም ለጥቂት ጊዜ በኒቅያ ሲጸልዩና ሲባረኩ ሰነበቱ:: ቀጥለውም የአባታቸውን ሰራዊት ሰብስበው "እኛ ሱባኤ ልንይዝ ስለ ሆነ እንመጣለን" የሚል ደብዳቤን ሰጥተው ወደ ሮም ሸኟቸው::

+ወታደሮችን ከሸኙ በኋላ ቅዱሳኑ በአካባቢው ወደ ሚገኝ አንድ ገዳም ሒደው ለአንድ ደግ መናኝ ምሥጢራቸውን ገለጹለት::
ልክ የንጉሡ ለውንድዮስ ልጆች መሆናቸውን ሲያውቅ 'አመንኩሰን' ያሉትን እንቢ አላቸው::

+"ለምን?" ሲሉት "ደጉን አባታችሁን ማሳዘን አልፈልግም:: ግን ፈቃዳችሁ እንዲፈጸምላችሁ ወደ ሶርያ ዝለቁ:: በዚያ አባ አጋብዮስ የሚባል ጻድቅ ገዳማዊ ሰው ታገኛላችሁ" ብሎ ወደ ሶርያ አሰናበታቸው::

+በምድረ ሮም: በተለይም በቤተ መንግስቱ አካባቢ የ2ቱ ልዑላን መጥፋት (መሰወር) ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: ንጉሡ አባታቸው በወታደሮቹ ዓለምን ቢያካልልም ሊያገኛቸው አልቻለም:: እርሱ ፈጽሞ ሲያዝን እናታቸው ፈጽማ መጽናናትን
እንቢ አለች::

+መክሲሞስና ዱማቴዎስ ግን ምድረ ሶርያ ገብትው የጻድቁ አባ አጋብዮስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ:: በእርሱም ዘንድ ለምናኔ የሚያስፈልጉ በጐ ምግባራትንና ትሩፋትን ከተማሩ በኋላ 2ቱንም አመነኮሳቸው:: በዚያ ቦታም እየታዘዙ: ፈጣሪን እያመለኩ: በጾም: በጸሎትና በትህትና ኖሩ::

+አንድ ቀን ግን አባ አጋብዮስ ጠርቶ "ልጆቼ! ተባረኩ! በእናንተ ምክንያት ደስ ብሎኛልና:: በዚህች ሌሊት የመነኮሳት ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ በራዕ ተገልጦ: ልጆች እንዲሆኑኝ ስጠኝ ብሎኛልና እኔ ሳርፍ ወደ ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ እንድትሔዱ" አላቸው::

+አባ አጋብዮስ ካረፈ በኋላ ግን እንደ ትዕዛዙ አልሔዱም:: ውዳሴ ከንቱን ይፈሩ ነበርና:: በዚያው በምድረ ሶርያ ግን በጥቂት ጊዜ: ገና በወጣትነት ከብቃት መዓርግ ስለ ደረሱ በርካታ ተአምራትን ሠሩ:: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ ሆኑ::

+ስም አጠራራቸውም ሶርያን መላት:: በዘመኑ በአካባቢው አንድ ግዙፍ ዘንዶ ተነስቶ ሰውንም እንስሶችንም ፈጃቸው:: ሕዝቡም ሒደው በቅዱሳኑ ፊት አለቀሱ:: ያን ጊዜ ቅዱስ መክሲሞስ (ትልቁ) ክርታስ አውጥቶ "አንተ ዘንዶ ይህ ክርታስ ወደ አንተ ሲደርስ ከማደሪያህ ውጣ: ሙት: ወፎችም ይብሉህ" ሲል ጻፈበት::

+"ሒዳችሁ በበሩ ጣሉት" አላቸው:: አንድ ደፋር ሰው ተነስቶ ሰዎች ሁሉ እያዩት ወስዶ በዘንዶው መውጫ ላይ ጣለው:: በቅጽበትም ዘንዶው ወጥቶ ሞተ:: አሞሮችም ተሰብስበው በሉት:: ከዚህ ድንቅ ተአምር የተነሳ ሕዝቡ የቅዱሳኑን
አምላክ አከበረ::

+ከዚህ በተረፈም በቅዱሳኑ ስም ታላላቅ ተአምራት ተደረጉ:: ርኩሳት መናፍስት ሁሉ ስማቸውን እየሰሙ ይሸሹ ነበርና:: ድውያን እነሱ በሌሉበት ስማቸው ሲጠራላቸው ይፈወሱ ነበር:: የአካባቢው ሰው ስማቸውን እየጠራ: በእነርሱም
እየተማጸነ ከመከራው ሁሉ ይድን ነበርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሞገስ ሆኑ::

+መርከበኞች ደግሞ ከማዕበል ለመዳን የቅዱሳኑን ስም በጀልባዎቻቸው ላይ ይጽፉ ነበር:: አንድ ቀን ግን የንጉሡ ለውንድዮስ ባለሟል ይህንን ጽሑፍ ተመልክቶ ስለ ጠረጠረ መርከበኛውን በንጉሡ ፊት አቀረበው::

+ንጉሡም መርከበኛውን "የጻፍከው የማንን ስም ነው?" ቢለው "በሶርያ የሚገኙ 2 ወንድማማች ቅዱሳን ስም ነው" አለው:: ልጆቹ እንደ ሆኑ ገምቶ በመርከበኛው መሪነት ንግሥቲቱንና ሴት ልጁን ላካቸው:: እነርሱ በሐዘን ተሰብረው ነበርና::

+ወደ ሶርያ ወርደው ባገኟቸው ጊዜም ከናፍቆትና ደስታ የተነሳ ታላቅ ጩኸትን እየጮሁ አለቀሱ:: "እንሒድ ወደ
ሮም" ሲሏቸው ግን ቅዱሳኑ "የለም! እኛ የክርስቶስ ነን" ብለው እንቢ ስላሏቸው እያዘኑ ተመለሱ:: ንጉሡ ግን ይህንን ሲሰማ ደስ አለው:: "እነርሱ የዚህን ዓለም ኃላፊነት ተረድተዋል" ሲልም አወደሳቸው::

+በኋላ ግን "የሮሜ ሊቀ ዻዻሳት መሆን አለባችሁ" የሚል ነገር ሲሰማ ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ከሶርያ ወጥተው ወደ ግብጽ ወረዱ:: የከታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዘንድ ደርሰውም ልጆቹ እንዲሆኑ ለመኑት::

+"ልጆቼ! በርሃ አይከብዳችሁም?" ቢላቸው "ግዴለም!" አሉት:: በዚያም ከተራራው ሥር በዓት ሠርቶላቸው ለ3
ዓመታት በአርምሞ ቆዩ:: አንድ ቀንም ቅዱሳኑ እየጸለዩ ከአፋቸው የወጣ የብርሃን ምሰሶ ከመንበረ ጸባኦት ሲደርስ አይቶ ታላቁ መቃርስ አደነቀ::

+በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢም ጥር 14 ቀን ታላቁ ቅዱስ መክሲሞስ ዐረፈ:: በዕለቱም የሰማይ ቅዱሳን ሁሉ ወርደው እየዘመሩ ወሰዱት:: ከ3 ቀን በኋላ ደግሞ ቅዱስ ዱማቴዎስ ዐረፈ::+በተመሳሳይ ቅዱሳኑ ሲወስዱት 2ቱንም ቅዱሳን ታላቁ መቃርስ በበዓታቸው ቀብሯቸዋል:: ቦታውም ደብረ ብርስም (በርሞስ) ተብሏል:: ትርጉሙም የሮማውያኑ ቅዱሳን ደብር እንደ ማለት ነው::

✞አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን:: ክብራቸውንም አያጉድልብን::

ጥር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱሳን እና ክቡራን የሚሆኑ አባቶቻችን "መክሲሞስ
እና ዱማቴዎስ"

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

++"+ ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር
አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም::
ብቻዬን
ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን
አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ
ደስ
አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን
ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል:: +"+ (1ቆሮ. 13:4)

     ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
        ✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
    ✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
   

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!። 

  "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn 
Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments