<<< በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ >>>
<<< ታሕሳስ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት >>>
+" ቅድስት አንስጣስያ "+
=>እስኪ ዛሬ በጥቂቱ የተባረኩ (ቡሩካት) እናቶቻችን እንዘክር:: "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ 'ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን ናትና::
+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::
+እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው:: 1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::
"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)
2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ
ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም- ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)
3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ- የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::
4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::
+የእመ ብርሃን ይቆየንና ደግሞ ሌሎች ቅዱሳት እናቶቻችንን እንመልከት:: እናቶቻችን ስናከብር የምንጀምረው በቅድስት ሔዋን ነው:: ብዙ ጊዜ የእናታችን ሔዋን ጥፋቷ እንጂ በጐ ነገሯ: ደግነቷ: ንስሃዋ አይነገርላትም:: ሆኖም እናታችን ቅድስት ሔዋን ክብር የሚገባት ሴት ናት::
*ክርስቶስ ሰው የሆነ እርሷንና ልጆቿን ለመቀደስ ነውና:: "ከመ ይስዓር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፅ ተሰቅለ" እንዲል:: (ድጉዋ)
+ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን እነ ሐይከል: እድና: ሣራ: ርብቃ: አስኔት: ሲፓራ: ሐና: ቤርሳቤህን የመሰሉ እናቶቻችን በበጐው መንገድ ፈጣሪን ደስ አሰኝተዋል:: በዘመነ ሥጋዌም ቅዱሳቱ ሐና: ኤልሳቤጥ: ማርያም: ሶፍያ: ሰሎሜ: ዮሐና እና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በጐነታቸው ያበራል::
+ከዚያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለ2,000 ዓመታት የተነሱ አእላፍ ቅዱሳት እናቶቻችንን ግን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም:: በቅድስናቸው አራዊትን ያሰገዱ: ነገሥታትን ያንቀጠቀጡ: አጋንንቸትን የረገጡ: በዘንዶ ላይ የተጫሙ ብዙ እናቶችን ቤተ ክርስቲያን አፍርታለች::
+ዛሬም ቢሆን በበርሃና በከተማ በጐውን ጐዳና የተከተሉ ብዙ እናቶች እንዳሉን እናውቃለን:: አንድም እናምናለን:: ግን ግን በከተሞች የምንመለከተው ሥርዓቱን የለቀቀው የበርካታ እህቶቻችን አካሔድ ለሃገርም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ ስጋት
ነው:: ክብርና ነውር የማይለይበት ዘመን ይመስላል::
+ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ እህቶቼ! አንድ ነገር ልንገራችሁ:: በመልካቸው ብዙዎችን ያጋጩ: አጊጠው በመታየታቸው ብዙዎችን ያሰናከሉ: ለብዙ ምዕመናንም የጥፋት ምክንያት የሆኑ ብዙ ሴቶች በታሪክ ነበሩ::
+የሚያሳዝነው ግን ዛሬ ያሉት ከመሬት በታች ነው:: አፈር በልቷቸዋል:: ስም አጠራራቸውም ጠፍቷል:: በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬ በዘለዓለማዊው እሳት እየተቃጠሉ በሲኦል: በጥልቁ ውስጥ አሉ::
+እናም ወገኖቼ! ይህን አውቀን እንንቃ:: ይህ ዓለም ጠፊም: አጥፊም ነውና:: እድሜአችን ቢረዝምና ከዚህ
በኋላ ለ100 ዓመታት ብንኖርም እርሱም ማለቁ አይቀርምና:: ምርጫችን ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን::
+" ቅድስት አንስጣስያ "+
+ይህች ቅድስት እንደ በርካቶቹ ቅዱሳት እናቶቻችን ሁሉ የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ናት:: በቀደመችው ታናሽ እስያ አካባቢ ተወልዳ: የነገሥታት ዘር በመሆኗ ያደገችው በቤተ መንግሥት ነው:: አባቷ ከክቡራኑ አንዱ ቢሆንም ሙያው ጣዖትን ማምለክ ነበር::
+ጊዜው የመከራ በመሆኑ ብዙ ሴቶች የሚኖሩት ክርስትናቸውን ደብቀው ነው:: ከእነዚህ መካከል አንዷ ደግሞ የቅድስት አንስጣስያ እናት ናት:: ማንን እንደምታመልክ አረሚ ባሏ አያውቅም ነበር::
+አንስጣስያን በወለደች ጊዜም በድብቅ አስጠመቀቻት:: ከሕጻንነቷ ጀምሮም ፍቅረ ክርስትና እንዲያድርባት ነገረ ሃይማኖትን አስተማረቻት:: ቅድስት አንስጣስያ ወጣት በሆነች ጊዜ ግን ከውበቷ የተነሳ ተመልካቿ በዛ:: እርሷ ግን ይህ ሁሉ የዓለም ኮተት አይገባትም ነበር::
+በፈጣሪዋ ፍቅር ከመጠመዷ የተነሳ ለመሰል ነገሮች ትኩረት አልነበራትም:: ትጾማለች: ትጸልያለች: ነዳያንና እሥረኞችን ትጐበኛለች:: በዚህም ዘወትር ደስ ይላት ነበር:: ነገር ግን አባቷ ባላሰበችው ጊዜ ለአንድ አረማዊ አጋባት:: በጣም አዘነች: ግን ተስፋ አልቆረጠችምና መፍትሔ ፈለገች::
+ድንግልናዋን እንዳያረክስ በጫጉላዋ ቀን ታመምኩ ብላ ተኛች:: ከዚያ በኋላም አንዴ በልማደ አንስት: አንዴ
በሕመም እያመካኘች አላስቀርብ አለችው:: እርሱ የጦር አለቃ በመሆኑ ወደ ጦርነት ሲሔድ እርሷ ታጥቃ ስለ ቀናች እምነት የታሠሩ ክርስቲያኖችን ታገለግል ነበር::
+ቁስላቸውን እያጠበች: አንጀታቸውን በምግብ እየደገፈች ደስ ታሰኛቸውም ነበር:: ባሏ ሲመለስ ግን ይህንን በመስማቱ ድጋሚ እንዳትወጣ ቆልፎባት ወደ ጦርነት ተመለሰ:: ፈጽማ ስላዘነችበትም እግዚአብሔር በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠውና ሞተ::
+እርሷም ከነ ድንግልናዋ ቀሪ ሕይወቷን ስትመራ መከራው ወደ እርሷ ደረሰ:: ተይዛ ቀርባ በአረማውያን እጅ ብዙ ተሰቃየች:: በዚህች ቀንም ስለ ክርስቶስ ተገድላ ክብረ ሰማዕታትን ተቀዳጀች::
✝ ቅዱስ አቦሊ ጻድቅ ✝
+ቅዱሱ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የክርስቶስን ሕማማት ለመሳተፍ ሲተጉ ከኖሩ ጻድቃን አንዱ ነው:: መሉ ጊዜውን በበርሃ ሲያሳልፍ ብዙ ተጋድሎን ፈጽሟል:: በተለይ ሲጸልይ እግሩን ከዛፍ ላይ አስሮ: ቁልቁል ከባሕር ውስጥ ሰጥሞ ነው:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ዕረፍቱን ታስባለች::
=>አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን: ክብሩን ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::
=>ታሕሳስ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት አንስጣስያ ሰማዕት
2.ቅዱስ አቦሊ ጻድቅ
3.ቅድሰት ዮልያና ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
++"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ
ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment