❖ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ❖
❀ ሚያዝያ ፳፯ ❀
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ ፊቅጦር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*"+ ማር ፊቅጦር +"*+
=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ!
+ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው:: እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል::
=>ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው 20 ዓመት ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ 3ኛ አድርጐ ሾመው::
+የድሮዋ አንጾኪያ (ሮም) እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት: ይወዱትም ነበር:: እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል ነበር::
+ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ: እኩሉን የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ እርሱ የንጉሡ 3ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::
+ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ47 ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ: በመጋዝ ተተረተሩ: ለአራዊት ተሰጡ: በግፍም ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::
+በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ:: ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::
+ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ መኳንንቱ ሁሉ
ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ ሲል
መናቅን መርጧልና::
+ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኳንንቱ እየተፈራረቁ አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት
አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል: ምላሱንም
ቆርጠዋል::
+በዚሕች ዕለት ግን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች::
እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው:-
"እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ስምህን ያከበረ:
የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባዋለሁ::"
❖ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን::
❖ሚያዝያ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጽኑዕና ኃያል ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
2.ቅድስት ማርታ (የፊቅጦር እናት)
3.ብጽዕት እስጢፋና (በክርስቶስ ስላመነች ከ2
ሰንጥቀው የገደሏት የ15 ዓመት ወጣት)
4.ቅዱሳን ሳሲማና አባ ኖባ (ሰማዕታት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
++"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ:
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ
እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment