✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖✝ ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝ ቅዱስ እንድራኒቆስ +"+✝
=>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር ደምሮ አስተምሮታል::
+ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር:: ይሕ የተፈጸመ ገና መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20)
+ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10 ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት
ተቀብሏል:: እንደ ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን ሰብኳል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት አምላኩን አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ
እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ መልዕክቱ 16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው::
+ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል አብርተዋል:: እጅግ ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት ቤቶችን አፍርሰው አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል:: በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል::
+ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ
በዚሕች ቀን አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር ገንዞ ቀብሮታል::
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+
=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
+ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ
(ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል:: በዚህም ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል:: እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል::
❖የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ ክብራቸውን ያድለን::
❖ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ደቅስዮስ
3፡ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5፡ አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
6፡ አባ ጳውሊ የዋህ
++"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ: ደግሞም
ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና
ዮልዮስ) ሰላምታ አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment