✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝✝✝
=>+"+ እንኩዋን ለእናታችን ቅድስት ሣራ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+"+ ቅድስት ሣራ +"+
=>እናታችን ቅድስት ሣራ በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዷ ናት:: ተወልዳ ያደገችው በሃገረ አንጾኪያ (ሶርያ) ውስጥ ነው:: ለክርስቲያን እንደሚገባ አድጋ በመንፈሳዊ ሥርዓት አግብታለች::
+የመከራው ዘመን እየገፋ ሲመጣ ባሏ ሃይማኖቱን በመካዱ ሕይወቷ ተመሰቃቀለ:: በመሐል ላይ ደግሞ ነፍሰ ጡር ነበረችና መንታ ልጆችን ወለደች:: ልጆቿን ክርስትና ለማስነሳት ምድረ ሶርያን ዞረች:: ግን አልቻለችም::
+ምክንያቱም ከመከራ ብዛት አብያተ ክርስቲያናት የሚበዙቱ ተቃጥለውና ፈርሰው ነበር:: ቀሪዎቹ ደግሞ ካህናትና ምዕመናን በማለቃቸው ምክንያት ተዘግተው ነበር::
+ቅድስት ሣራ ልጆቿ የሥላሴ ልጅነተነን ሳያገኙ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለምና ሕይወቷን አደጋ ላይ የሚጥል ግን መንፈሳዊ ውሳኔን ወሰነች:: ከሶርያ ተነስታ: በመርከብ ተጭና ወደ ግብፅ ወረደች::
+በውሃው መካከል ላይ ሲደርሱ ታላቅ ማዕበል ተነስቶ አናወጣቸው:: በዚህ ጊዜ ቅድስት ሣራ ደነገጠች:: ልጆቿ ጥምቀትን ሳያገኙ መሞታቸው ነውና በእምነት ወደ ፈጣሪዋ ጸለየች:: ሁለቱን ልጆቿን ወስዳ በባሕሩ ላይ በአብ: በወልድ: በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቃ: ከጡቷ አካባቢ በጥታ በሜሮን አምሳል ቀባቻቸው::
+ድንገት ግን በዚህ አፍታ ማዕበሉ ጸጥ አለ:: እርሷም እያደነቀች ወደ ግብጽ ደርሳ ሊቀ ዻዻሳቱን (ቅዱስ ዼጥሮስን) "አጥምቅልኝ" አለችው:: ቅዱስ ዼጥሮስም ሥርዓቱን አድርሶ ሊያጠምቃቸው ባልዲውን ሲዘቀዝቀው ውሃው ረጋበት:: ሁለተኛም: ሦስተኛም ሞከረ:: ግን አሁንም ለሌሎቹ ሕጻናት የሚፈሰው ለቅድስት ሣራ ልጆች እንቢ አለ::
+ቅድስት ሣራም "ምናልባት በድፍረቴ ምክንያት ይሆናል" ብላ የሆነውን ሁሉ እያዘነች ነገረችው:: ቅዱስ ዼጥሮስ ግን እግዚአብሔርን አመሰገነ:: አላትም "ፈጣሪ ባንቺ እጅ ስላጠመቃቸው የእኔን እንቢ አለ:: ልጄ ሆይ! ሃይማኖትሽ ትልቅ ነው::"
+ከዚህ በሁዋላም ሥጋውን ደሙን አቀብሎ ባርኮ አሰናብቷታል:: ወደ ሶርያ ስትመለስ ግን ሌላ የከፋ ነገር ጠበቃት:: በባሏ ከሳሽነት ወደ ከሃዲው ንጉሥ (ዲዮቅልጥያኖስ) ቀረበች:: ንጉሡ ክርስቶስን ካጂ: የት እንደ ነበርሺም ተናገሪ አላት:: እርሷ ግን ሃይማኖቷ የጸና ነበርና እንቢ አለች::
+በዚህም ምክንያት በ303 ዓ/ም አካባቢ በዚሁ ቀን አንድ ልጇን በሆዷ: ሌላኛውን በጀርባዋ አድርገው በእሳት አቃጥለው ገድለዋታል:: እነሆ ቤተ ክርስቲያን ታስባታለች:: ታከብራታለችም::
=>አምላካችን ቅድስት ሣራን እንዳጸና እኛንም ያጽናን:: ከበረከቷም ያድለን::
=>ሚያዝያ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ሣራና 2 ልጆቿ (ሰማዕታት)
2.አቡነ ገብረ ማርያም ጻድቅ-ዘልሆኝ (ኢትዮዽያዊ)
3.አባ በብኑዳ ባሕታዊ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ መስተጋድል
5.ቅድስት ዶራ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment