✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ሚያዝያ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ +"+
+ቅዱስ ዮሐንስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ቅዱስ ሰው ነው:: ወላጅ አባቱ ጣኦት ጠራቢና አምላኪ: የጣኦቱ
አጣኝም ነበረ:: እናቱ ግን በድብቅ ክርስቶስን ታመልክ ነበር::
+ልጇን ክርስትና ብታስተምረው አባቱ ጨካኝ በመሆኑ ይገድለዋልና ዘወትር ጧት ማታ ወደ ፈጣሪዋ በዕንባ ትለምን ነበር:: ጧት ጧት አባቱ ጣኦት መጥረብና ማምለክን ያስተምረው ነበር:: አንድ ቀን እግዚአብሔር ለሕጻኑ ዮሐንስ በራዕዩ
ተገለጠለት:: ምስሥጢራትንም አስተማረው::
+ለተወሰነ ጊዜ በሚደነቅ የክርስትና ሕይወት ከኖረ በኋላ ምንም ገና እድሜው 12 ዓመት ቢሆንም አባቱን ጦኦትህን ተው ሲል መከረው:: አባት ግን ጨካኝ ነውና ትልቅ መጥረቢያ አንስቶ አንገቱን መታው:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ መሬት ላይ
ስትወድቅ አካሉ ግን ለ1 ሰዓት ቆሞ በደሙ ተጠመቀ:: ይሕ ሁሉ
ሲሆን የተባረከች እናቱ ቆማ ታይ ነበር::
+መንፈሳዊት እናት ናትና አላዘነችም:: ይልቁኑ ከልጇ ደም ለበረከት ተቀባች:: አለችም:- "ጌታ ሆይ! የምሰጥህ
ምንም የለኝም:: ይህንን ንጹሕ መስዋዕት ግን ተቀበለኝ::"
+ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ካለፈ በኋላ አባቱን ርኩሳን መናፍስት አሳበዱት:: እናት ግን አረማዊ ባለቤቷን ወደ ቅዱስ
ዮሐንስ መቃብር ወስዳ ጸለየች:- "ልጄ ሆይ! አባትህን ይቅር ብለህ ከፈጣሪ ዘንድ አማልድ::"
+ይሕንን ብላ ባሏን ከመቃብሩ አፈር ወስዳ ቀባችው:: አባትም በቅጽበት ድኖ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ስለ ሰራው ሁሉ ተጸጽቶ አለቀሰ:: በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: በመልካም ክርስትና ኑሮ ኑሮ: ከተባረከች ባለቤቱ ጋር
ለገነት በቅቷል::
+"+ ቅዱስ ሱስንዮስ +"+
+ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሱስንዮስ ተሰይፏል:: ቅዱሱ በዘመነ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያንን በገድላቸው ካስጌጧት
ታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው::
❖እግዚአብሔር አምላክ ከሰማዕታቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::
❖ሚያዝያ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት (ወልደ ፀራቢ)
2.ቅዱስ ሱስንዮስ ሰማዕት (ሶርያዊ)
3.ሰማዕታት (የቅዱስ ሱስንዮስ ማሕበር)
4.አባ ሠርጋ
5.ቅዱስ ይድራስ
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ አቡነ ሐብተ ማርያም
2፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ
3፡ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
4፡ ቅዱስ ቶማስ
5፡ ሰማዕታተ ናግራን
++"+ ሰውን ከአባቱ: ሴት ልጅንም ከእናቷ: ምራትንም ከአማቷ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ
ጠላቶች ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን
ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: መስቀሉን የማይዝ በኋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን
አይገባውም:: +"+ (ማቴ.
10:35-39)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment