Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ሐምሌ 7

=>+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን

አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ

ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+

=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)

የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ

#እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::


+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ "እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን

#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮንበመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉትየፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::

+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግልእመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

+"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+

=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-

¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ

¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ

¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት

¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት

¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ

¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ

¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ

¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ

አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን

(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ

¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ

¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ

¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ

¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ

¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና

¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው::

+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ

#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )

+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::

+በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው #አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::

+"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

(#GIYORGIS_OF_SEGLA )+"+


=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ

#አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ::

+ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው::

+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው፧ መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ)

+ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/

ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-

1. #ሊቀ_ሊቃውንት

2. #በላዔ_መጻሕፍት

3. #ዓምደ_ሃይማኖት

4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ

5. #ጠቢብ_ወማዕምር

+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን ነው::

=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)

2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ

3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)

4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ

የሃይማኖት ምሰሶ)

5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)

6.አባ መቃቢስ

7.አባ አግራጥስ

=>ወርሐዊ በዓላት

1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት

2.አባ ባውላ ገዳማዊ

3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ


=>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ::

እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ.6:13)

=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ:የእግዚአብሔርም ፍቅር:

የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+(ቆሮ. 13:14)

      <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር

🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ

መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት

@FasilKFCይላኩልን

✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር

Join Us Today And Lets learn Together

https://gondarmaheber.blogspot.com

https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam

━━━━━━━༺✞༻━━━━━

Comments