Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

በእመቤታችን ስም የተሠራች የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ቅዳሴ ቤት የእመቤታችን 2ቱ ክብረ በዓላት ታሪክ

#ሠኔ_20_እና_21 በእመቤታችን ስም የተሠራች የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ቅዳሴ ቤት የእመቤታችን 2ቱ ክብረ በዓላት ታሪክ
[✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ]

♥ በሠኔ 20 ለመጀመሪያ ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በፊልጵስዩስ የተሠራችው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ትታሰባለች፤ ይኸውም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን ጳውሎስና በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ከተማ ገብተው ባስተማሩ ጊዜ ሕዝቡ “መካነ ጸሎት ለዩልን” ብለዋቸዋል፤ ይኽነንም ለጴጥሮስ በነገሩት ጊዜ ጌታችን የሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን አሠራር እንዲገልጽላቸው ሱባዔ ገቡ፤ ሱባዔውም ሲፈጸም ጌታ ሐዋርያትን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፨

♥ “በናቴ ስም አብያተ ክርስቲያናት ሊታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ላሳያችኊ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናትን ላስተምራችኊ ሰብስቤያችኋለኊ” ብሏቸው፤ ወደ ምሥራቅ አገር ይዟቸው ወጣ፤ በዚያ በምሥራቅ ሀገር ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ ተራርቀው የነበሩትን አቀራረባቸው፤ ጥቃቅን የነበሩትን ታላላቅ አደረጋቸው፤ ቁመቱን ወርዱን ለክቶ ሰጣቸው፤ ቁመቱ 24 ወርዱ 12 ክንድ ነው፡፡ 

♥ 24ቱ የ24ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ 12ቱ የ12ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፤ ከዚኽ በኋላ ሥራ ጀመሩ፤ ሲሠሩትም ሰም እሳት ሲያሳዩት እንዲለመልም በእጃቸው ላይ እየተሳበ ሠርተው ፈጽመውታል፤ ይኽ የኾነ እመቤታችን ባረገች በአራተኛው ዓመት በሠኔ 20 ቀን ነው፨

♥ በሠኔ 21ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ መጣ፤ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋያትን ልኡካን አድርጎ፤ ጌታ ዐቢይ ካህን ኾኖ ቀድሶ አቊርቧቸዋል፤ ከዚያም “እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ” (ከእንግዲኽ ወዲኽ እናንተ እንዲኽ ሥሩ) ብሎ አዝዟቸው ዐርጓል፤ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረ በቅድስት ድንግል ስም ነው፡፡ 

♥ ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው 3 ከላይ ሕንፃቸው 1 ነው ይኽም የአንድነታቸው የሦስትነተኛው አምሳል ነው።

♥አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፡- 

“በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ
ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ
አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ
እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ
ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ
ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ”

(ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራት ከፈጸመ በኋላ፤ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግል በከበሮ ምስጋናን አቀረቡ) በማለት ገልጸዋል፡፡ 

♥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯ በሰማያት አምሳል እንደኾነ ሊቃውንት ይተነትናሉ፤ ይኸውም የመጀመሪያዋ ሰማይ “ጽርሐ አርያም” ስትባል ከእሳት ብርሃኗን ነሥቶ ከብርሃን ብርሃንን ጠምቆ አጥርቶ፤ ኹለንተናዋን በብርሃን ቀለም ሸልሟታል “አልቦ ሰማይ ዘይጼልል ላዕሌሃ እስመ መልዕልታዊት ወጽንፋዊት ይእቲ ወኲለንታሃ ብርሃን ፍጹም ዘኢይትነገር በልሳነ ኲሉ ፍጡር ወኲሎሙ ብርሃናት አምሳለ ቀለምጺጸ እሳት በኀቤሃ” ይላል ፤ ብርሃኗን ማንም ከቶ ሊገልጸው አይችልም፤ ከርሷ ብርሃን አንጻር ሲታዩ ሌሎቹ ብርሃናት የእሳት ፍንጣሪ ያኽላሉ፤ ከሰማይ ኹሉ በላይ ስትኾን ከርሷ በላይ ምንም ሰማይ የለም፤ ከዚኽ የተነሣ “ሰማየ ሰማያት” ትባላለች (ዘዳ ፲፥፲፬፤ ፩ነገ ፰፥፳፯)፡፡ 

♥ ምሳሌነቷን ሊቃውንት በመጽሐፈ ቅዳሴ መቅድም ላይ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ስለመሠራቱ ሲተነትኑ በጽርሐ አርያም ውስጥ መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን፣ አራቱ ጸወርተ መንበር፣ ኻያ አራቱ ዐጠንተ መንበር ይኖራሉ፤ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፤ መንበረ ብርሃን የመንበር፤ ታቦተ ብርሃን የታቦት፤ መንጦላዕተ ብርሃን የመንጦላዕት፤ አራቱ ጸወርተ መንበር የአራቱ ሊቃነ ጳጳሳት፤ 24ቱ ዐጠንተ መንበር የጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል ናቸው፡፡
♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ሰዓታቱ ላይም “ወኊልቈሙ ለእሙንቱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት... ወቡርክት ዛቲ ቤተ ክርስቲያን እንተ አሕዛብ ትመስል ኀይለ ሰማያት” (የእነዚኽ መላእክት የመላእክት አለቆች ቊጥርም መናብርትና ሥልጣናት፣ አጋዕዝትና ኀይላት፣ ሊቃናት፣ ኪሩቤልና ሱራፌል ነው፤ እየጮኹም እንዲኽ ይላሉ የእስራኤል አምላክ ይመስገን የሕዝቡ የአሕዛቡ የምትኾን የተባረከች ቤተ ክርስቲያን የሰማያት ኀይልን ትመስላለች) ይላል፡፡

♥ ሊቁ ሰራዊተ መላእክትን በሚያመሰግንበት በዚኽ ክፍል ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯና እና አከፋፈሏ በመላእክት ከተማ እና በአሰፋፈራቸው ልክ የተመሰለች መኾኗን አስረግጦ አስተምሯል፡- ይኸውም ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች (መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌት) የሦስቱ ዓለመ መላእክት ምሳሌ ሲኾን ይኸውም መቅደስ የኢዮር፤ ቅድስት የራማ፤ ቅኔ ማሕሌት የኤረር ምሳሌ ናቸው፡፡

♥ ኢዮር በተባለችው ሰማይ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኀይላት ይኖራሉ፡፡ ራማ በተባለችው ሰማይ አርባብ፣ መናብርት፣ ሥልጣናት ይኖራሉ፡፡ ኤረር በተባለችው ሰማይ ሊቃናት፣ መኳንንት፣ መላእክት ይኖራሉ፡፡ እነዚኽ 9ኙ ነገድ የ9ኙ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን አምሳል ናቸው፡፡ 

♥ ይኸውም በኢዮር የሚኖሩት ኪሩቤል የሊቃነ ጳጳሳት፤ ሱራፌል የጳጳሳት፤ ኀይላት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል፡፡ 
♥ በራማ ሰማይ የሚኖሩት አርባብ የቆሞሳት፤ መናብርት የቀሳውስት፤ ሥልጣናት የዲያቆናት አምሳል፡፡ 
♥ በኤረር ሰማይ የሚኖሩት ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፤ መኳንንት የአናጒንስጢሳውያን፤ መላእክት የመዘምራን አምሳል ናቸው፡፡

♥ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ፦ “እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ ወተቀደሰት በደሙ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጊሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ” (በስሙ ታነጸች፤ በደሙም ከበረች፤ በዕፀ መስቀሉም ተባረከች፤ ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ኺዱ የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና) ይላል፡፡

♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ተአምኆ ቅዱሳን በሚባለው ታላቅ መጽሐፉ ላይ፡- 
“ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ”
(የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፡፡

♥ ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ መልኩ እናትነቷን በሰባቱ ጊዜያት የሕማማት ሰላምታው ላይ፡-
“ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ ዘትጼንዊ መጽርየ
ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ
ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ”
(እንደ ቀጋ የምትሸትቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኊ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል)

♥“በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ
ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ
እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ
ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ”
(ሰላምታ የተገባሽ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሰላም ሰላም እንልሻለን፤ በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ፤ ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ፤ ልመናሽም ከእኛ ጋራ ይኹን) በማለት እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አወድሷል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በረከት ይደርብን፡፡
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ


"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━

Comments