✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞
❖ ✝እንኳን አደረሳችሁ ✝❖
❖ ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ +"+
=>ቤተ_ክርስቲያን
በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል
የተባለ የቅዱስ_ያዕቆብ
ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል::
ታላቁ ቅዱስ_መጽሐፍ
ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው::
+ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን
ለማግኘት ኦሪት_ዘፍጥረትን
ከምዕራፍ 39 እስከ 50 ድረስ ማንበብ ይኖርብናል::
ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ
ተብሏል::
+መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም
ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ
ሴት
ሔኖክ
ኖኅ
ሴም
አብርሃም
ይስሐቅና
ያዕቆብ
ነግሮን ቅዱስ_ዮሴፍ
ላይ ይደርሳል::
+ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት
ሚስቱ ራሔል
ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም
እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ
ነበረው::
ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና::
+እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን
አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ
ሊፈልጋቸው
በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ::
+መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን
አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ
አድርጐ
መግቦታል:: 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ
ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም
"ሊነግሥብን
ነው" ብለው ቀንተውበታልና::
+በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን
ሸጠውታል:: በዚህም ለምስጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና
ሕማማት) ምሳሌ
ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ
ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት
በተሸጠበት በዺጥፋራ
ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው::
+ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ
ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ
አላንበረከከውም:: "ማንም
አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ
እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት
ኃጢአትን
አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ
ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል::
+ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና
አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት"
እንዲል
መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች
ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ
አስደመመ::
ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው::
+ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ
ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት
ወንድሞቹም መጋቢ
ሆናቸው:: አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም
ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል::
+በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ
ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ
በዚህች ቀን በመልካም
ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ
ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት
መሠረትም ልጆቹ
(እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ
ከነዓን አፍልሠዋል::
+" ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት "+
=>ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ
ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት
ነገሥታቱን
ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ
ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::
+እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር
ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ
ይጸልየው:
ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት
የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት:
ከክፋት ወደ
ደግነት መልሷል::
+የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን
ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ
ጊዜም
አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት:
ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::
+በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል::
ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና
በእምነት
እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት
ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው::
=>አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና
የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን
ይክፈለን::
=>ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ)
2.እናታችን አስኔት (የቅ/ ዮሴፍ ሚስት)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት
4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
5.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ልደታ ለማርያም
2፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
5፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
=>+"+ እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ
ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ
አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን
ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር
ላይ
ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም
አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ::" +"+ (ዘፍ.
45:4-8)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Comments
Post a Comment