†✝† እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃነ ዴጌ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ጻድቃነ ዴጌ †††
††† እነዚህ ጻድቃን ኢትዮዽያውያን ባይሆኑም ያበሩት በሃገራችን ነው:: ቅዱሳኑ በቁጥር 3,000 : በዜግነት ሮማውያን ናቸው:: ከሺህ አዝማናት በፊት ከሮም ግዛት ተሰባስበው እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮዽያ (አክሱም) መጥተዋል::
ቀጥለውም እዛው አካባቢ ወደሚገኝ ገዳም ገብተዋል:: ይህ ቦታ ለአክሱም ቅርብ ሲሆን በዘመነ ሐዋርያት የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ በዓት ነበር:: የሐዋርያው በትረ መስቀልም እስካሁን አለች::
ጻድቃነ ዴጌ ሕጋቸው አንዲት : እርሷም ፍቅር ናት:: ለዘመናት በፍቅረ ክርስቶስ ታሥረው : ፍቅርን ለብሰው : በፍቅር ኑረዋል:: ሁሌም በ29 የጌታችንን ስም እየጠሩ ጽዋ ጠጥተዋል:: ስለ ፍቅራቸውም ጌታችን 3,001ኛ ሆኖ : ነዳይ መስሎ አብሯቸው ጠጥቷል::
በመጨረሻም 3ሺው በአንድነት ተሠውረዋል::
††† ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን:: እኛንም በወዳጆቹ ጸሎት ይማረን:: . . .አሜን!
††† ጥር 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጻድቃን ቅዱሳን ማሕበረ ዶጌ (ዴጌ ጻድቃን)
(አክሱም አካባቢ በቁጥር ወደ 3,000 ሲሆኑ ከመድኃኔ ዓለም ጋር ማሕበር ይጠጡ የነበሩና በአንድ ላይ የተሠወሩ ቅዱሳን ናቸው)
2.አባ ገብረ ናዝራዊ ዘቃውንት (ኢትዮዽያዊ)
3.ቅድስት አክሳኒ ፈላሲት
4.ቅዱስ ሰርያኮስ ሰማዕት
5.አባ እስጢፋኖስ ገዳማዊ
6.ከድሮዋ ሮም የተነሱ ቅዱሳት አንስት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት አርሴማ ሰማዕት
2.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እናታችን
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍፃሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
††† "ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. 36:29)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━⊱✿⊰━━
Comments
Post a Comment