Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ጥቅምት ፮

በእንተ ስማ ለማርያም:
🌻✝✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፮ (6) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ዲዮናስዮስ ሐዋርያዊ" ወአባ "ዸንጠሌዎን" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሐዋርያዊ ሊቅ +"+

=>በዘመነ ሐዋርያት ከነበሩና አስደናቂ ታሪክ ከነበራቸው
ቅዱሳን አንዱ ይህ አባት ነው:: ቅዱስ ዲዮናስዮስ
በትውልዱ አረሚ (ግሪካዊ) የሆነ ፈላስፋ: ከነ አሪስቶትል
ሲያያዝ የመጣውን ፍልስፍና ጨርሶ በማጥናቱ ርዕሰ
ሊቃውንት (የፈላስፎች አለቃ) የሚል ስም ተሰጥቶት
ነበር::

+በግሪክ አቴና (ATHENS) ለነበሩ ፈላስፎችም ሁሉ
የበላይ ሲሆን በአርዮስፋጐስ (ሐዋ. 17) ታላቁ ሰው
እርሱ ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እድሜው ገና ወጣት
ነበር:: ቅዱስ ዲዮናስዮስ ፈላስፋ ስለ ሆነ ቅሉ
ይመራመር ነበር::

+ይልቁኑ ስለ እውነተኛው አምላክ ያስብ ነበር:: በግሪክ
ምድር ከሚመለኩ 250 አማልክት መካከል ቁም ነገር
አልተገኘምና:: ነገር ግን አንድ ቀን ዓለም በተፈጠረች
በ5,534 ዓመት: መጋቢት 27 ቀን: በዕለተ ዓርብ: 6
ሰዓት ላይ ምድር ተናወጠች:: ፀሐይ ጨለመች: ጨረቃ
ደም ሆነች: ከዋክብትም ረገፉ::

+በዚህ የተደናገጡ የአቴና (ATHENS) ነዋሪዎችና
ፈላስፎች ወደ ዲዮናስዮስ ተሰብስበው "መምሕራችን
የተፈጠረውን ነገር መርምረህ አስረዳን" አሉት::

+ዲዮናስዮስም ባለው ጥበብ ባሕሩን: የብሱን: ፀሐይ:
ጨረቃን: ከዋክብትን መረመራቸው:: "ወረከቦሙ
ኅዱዓነ" እንዲል በቀደመ ቦታቸው አገኛቸው:: ግራ
ቢገባው እንቅልፍ ከዐይኑ ተከለከለ::

+ከዚያም ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ መጻሕፍትን
ሲያገላብጥ "አርስጣላባ" የሚባል ግዙፍ መጽሐፍ
አግኝቶ ቢገልጠው "እልመክኑን" የሚል ጽሑፍ አገኘ::
ወደ ውጪ ወጥቶ በሕዝቡና ጠቢባኑ ፊት ልብሱን ቀድዶ
አለቀሰ::

+እነርሱም ደንግጠው "ምነው መምሕራችን? ምን
ሆንህ?" ቢሉት "የማይታየው አምላክ ቢወርድ
በምቀኝነት ገደሉት የሚል ጽሑፍ አገኘሁ" አላቸው::
"እልመክኑን" ማለት "የማይታይ አምላክ" ማለት ነውና::
"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ:
እሳት በላኢ አምላክነ" እንዲል::

+ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዛሙርቱን (ተማሮቹን) ጠርቶ
(ኡሲፎስና ኡርያኖስ ይባላሉ) "እልመክኑን" የሚለውን
ስም "ከቤተ ጣዖቱ በር ላይ ለጥፉት" ብሏቸው
ለጠፉት:: በእንዲህ ያለ መንገድ 14 ዓመታት አልፈው
ቅዱስ ዻውሎስ ወንጌልን እየሰበከ አቴና ደረሰ:: ዘመኑም
በ48 ዓ/ም ነበር::

+ወደ ከተማዋ ሲገባ በጣዖት ቤቱ በር ላይ
የተለጠፈውን ጽሑፍ ተመለከተና ያስተምራቸው ያዘ::
ትምሕርቱን የሰሙ ጠቢባኑና ሕዝቡ ሐዋርያውን ይዘው
ወደ ዲዮናስዮስ ፊት አቀረቡት:: "ምንድን ነው በደሉ?"
ቢላቸው "አዲስ አምላክን ሲያስተምር አግኝተነዋል"
አሉት::

+ቅዱስ ዻውሎስም "እኔ አዲስ አምላክን
የምሰብክላችሁ አይደለሁም:: ይልቁኑ ከቀድሞም
የፈጠራችሁ: ቀጥሎም የሞተላችሁ: እናንተም
"እልመክኑን" ብላችሁ ሳታውቁት ታመልኩት የነበረውን
ጌታ እንጂ:: እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አላቸው::

+ዲዮናስዮስም ቅዱስ ዻውሎስን "ለዚህ ምን ምልክት
አለህ?" ቢለው "የዛሬ 14 ዓመት: መጋቢት 27 ቀን:
በዕለተ ዓርብ 6 ሰዓት ላይ ታላላቅ ተአምራት የተደረጉ
አይደለምን! እነዚህ ሁሉ የተደረጉት በስቅለቱ ጊዜ ነው"
ሲል መለሰለት::

+ዲዮናስዮስም ፈጥኖ በክርስቶስ አመነ:: የአካባቢው
ጠቢባንና ሕዝቡም አምነው ከመሪያቸው ጋር ተጠመቁ::
ቅዱስ ዻውሎስም ቅዱስ ዲዮናስዮስን አስተምሮ የአቴና
የመጀመሪያው ዻዻስ አደረገው:: ቅዱሱም ክርስቲያኖችን
ያበዛ: መንጋውንም ያጸና ዘንድ ብዙ ተጋ::

+በተለይ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ታዋቂ
ደራስያን አንዱ ሆነ:: በርካታ ድርሰቶችንም በመንፈስ
ቅዱስ ደረሰ:: ዛሬ ድረስ እንኩዋ ሃይማኖተ አበው
ውስጥ የሚገኘው ድርሰቱ (ዘዲዮናስዮስ) ጣዕሙ ልዩ
ነው:: ቅዱሱ ለብዙ ዘመናት ለወንጌል አገልግሎት
ተግቶ: በዚህች ቀን የአካባቢው አገረ ገዥ አንገቱን
አስቆርጦት ሰማዕት ሆኗል::

+የሚገርመው ግን ሲገድሉት በቦታው ሰው ስላልነበረ
ቅዱሱ ተነስቶ: ተቆርጣ የወደቀች ራሱን አነሳት:: በጐኑ
አቅፎም ደቀ መዛሙርቱ እስካሉበት ሒዶ በፊታቸው
ዘንበል አለ:: ምዕመናንም እያለቀሱና እየዘመሩ
ከአርድእቱ ኡሲፎስና ኡርያኖስ ጋር ቀብረውታል::
እነርሱም አብረውት ተሰይፈዋልና::

+"+ አባ ዸንጠሌዎን ዘጾማዕት +"+

=>ታላቁ ጻድቅ: ሰባኬ ወንጌልና ገዳማዊ አባ
ዸንጠሌዎን የተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን መሪ (አባት)
ናቸው:: ጻድቁ ሃገረ ሙላዳቸው ሮም ቢሆንም
ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ነው::

+ወላጆቻቸው በሮም ቤተ መንግስት የቀኝ መንበር
ያላቸው ክቡራን ቢሆኑም ልጃቸውን ይማር ብለው ወደ
ገዳም ከተቷቸው:: በገዳም ትምሕርቱን ከጠነቀቁ
በሁዋላ በዚያው ጠፍተው ወደ ግብጽ ወረዱ:: በዚያም
መነኮሱ::

+እድሜአቸው እየገፋ ሲሔድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት
8ቱን ቅዱሳን ሰብስበው: በአቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
መሪነት ወደ ሃገራችን መጡ:: በ470ዎቹ አካባቢ
የነበረው ንጉሥ አልዓሜዳም በክብር ተቀብሎ አክሱም
ውስጥ "ቤተ - ቀጢን" የሚባል ቦታን ሰጣቸው::

+ዘጠኙ ቅዱሳን በአንድነት: ቀን ቀን ወንጌልን
ሲያስተምሩ ውለው ሌሊት ሲጸልዩና መጻሕፍትን
ሲተረጉሙ ያድሩ ነበር:: ነገር ግን ለየብቻቸው
መኖራቸውን መንፈስ ቅዱስ ስለ ወደደ ሁሉም
በየራሳቸው ገዳማትን መሠረቱ::

+አባ ዸንጠሌዎንም ከአክሱም ከተማ በላይ ከደብረ
ቆናጽል ጐን ወደ ሚገኝና 'ጾማዕት' ወደ ሚባል ረዥም
ተራራ ወጡ:: ቦታው ዛሬ "እንዳባ ዸንጠሌዎን" ይባላል::
በዚያም አስቀድመው ለወንጌል አገልግሎት እየተጉ
ድውያንን ፈወሱ::

+ሙታንን አስነሱ: አጋንንትን አሳደዱ:: ብዙ ተአምራትንም
አደረጉ:: እንዲያውም አንድ ቀን ወይራውን በጧት
ተክለው: በሠርክ ትልቅ ዛፍ ሆነላቸው:: ከዚያ ዘንጥፈው
እሳቱን በቀሚሳቸው ላይ አፍመው ማዕጠንት
አሳርገዋል::

+የሚገርመው ያ ዛፍ ዛሬም ድረስ ለምስክርነት ቁሟል::
እኛም ሳይገባን ሔደን በዓይናችን አይተነዋል:: አምላከ
ቅዱሳን ግሩም ነው !!! በመጨረሻ ዘመናቸው ግን ጻድቁ
5 ክንድ ርዝመት ባላት ጾማዕት (በዓት) ውስጥ ገብተው
ቆሙ:: ለ45 ዓመታት ሳይቀመጡና ሳይተኙ በእንባ
ቢጸልዩ ቅንድባቸው ተላጠ:: አካላቸውም በአጥንቱ ብቻ
ቀረ::

+በ6ኛው ክ/ዘመንም በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት
መድኃኔ ዓለም መጥቶ "ወዳጄ! ስምህን የጠራ:
መታሰቢያህን በእምነት ያደረገውንም ሁሉ እምርልሃለሁ"
አላቸው:: ያን ጊዜ አጥንቶቻቸው ተወዛወዙና ነፍሳቸው
በክብር ዐረገች:: ከዚህ አስቀድሞም ንጉሡን አፄ
ካሌብን አባት ሆነው ያመነኮሱት እርሳቸው ናቸው::

=>አምላከ አበው የወጡ ወገኖቻችንን ሁሉ በሰላም
ይመልስልን:: ከክብረ ቅዱሳንም አይለየን::

=>ጥቅምት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሐዋርያዊ
2.አባ ዸንጠሌዎን ዘጾማዕት

3.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ (ዕን. ከ1 - 3 ያንብቡ)
4.ቅድስት ሐና ነቢይት (የሳሙኤል እናት - 1ሳሙ. ከ1 - 2ን ያንብቡ)
5.ቅዱሳን ኡሲፎርና ኡርያኖስ (ሰማዕታት)
6.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮዽያዊ (ፍልሠቱ)
7.ቅዱስ ሄኖስ ነቢይ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና
እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=>+"+ ምንም እንኩዋ በለስም ባታፈራ:
በወይን ሐረግም ፍሬ ባይገኝ:
የወይራ ሥራ ቢጐድል:
እርሾችም መብልን ባይሰጡ:
በጐች ከበረቱ ቢጠፉ:
ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ:
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል:: በመድኃኒቴ
አምላክ ሐሴት አደርጋለሁ:: +"+ (ዕን. 3:17)

        ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethe
llettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments