Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ከማኅሌተ ጽጌ ምዕራፎች መካከል ሐተታ

#ከማኅሌተ_ጽጌ ምዕራፎች መካከል ሐተታ

⩩ጽጌ አስተርአየ ሠሪፆ እምዐፅሙ፣
ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፣
ወበእንተዝ #ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ፣
ለተአምርኪ አኃሊ እሙ፣ ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ 

⩩የክርስቶስ እናቱ ማርያም ሆይ መልአኩ ገብርኤል፣
    ደስ ይበልሽ እያለ ከአቀረበልሽ ሰላምታ ጋር ፣
    እጅ ከነሳሽ ሰው ዐጽም የጽጌረዳ አበባ በቅሎ ታየ፣
    ስለዚህ የተአምርሽ የጣዕሙ ዜና ባስደሰተኝ ጊዜ ፣
    ስሙ የአበባ ማኅሌት ለሚባል ተአምርሽ እዘምራለሁ። 

ታሪክ ፦ 

በኢያሪኮ የሚኖር አንድ አስቴራስ የሚባል አገልጋይ ዲያቆን ነበር። እርሱም በሉቃ 1:26 የተጻፈውን ብሎም የቅዱስ ገብርኤልን ብስራት የቅድስት ኤልሳቤጥን ሰላምታ በአንድ ላይ የያዘውን 
#በሰላመ_ቅዱስ_ገብርኤል የሚለውንን እና የእመቤታችንን ምስጋና ዘወትር ያለማቋረጥ ይጸልይ ነበር። ከዕለታት በአንድ ቀን ይህ ዲያቆን ለተግባር ከሀገሩ ተነስቶ በረኸውን አቋርጦ በዱሩ ሲሄድ ርኅራኄ የሌላቸው ክፉ አረሚዎች ዘርፈው ገድለው በመንገድ ጥለውት ይሄዳሉ። እመቤታችንም የእርስዋ ተአምር በእርሱ ይገለጥ ዘንድ ፈቃዷ ነውና በእዚያ ለሚኖር ለአንድ ዲያቆን በራእይ ተገልጣ '' ወዳጄ ሆይ ቤተክርስቲያንን በቅን የሚያገለግልና በእኔና በልጄ ዘንድ ጸሎቱ የተወደደችለት ዲያቆንን ስለገደሉት ሰዎች አዝኛለሁ፣ ሂድና ከጓደኞችህ ጋር በመንገድ ዳር የተቀበረውን ወዳጄን አውጥታችሁ ከቤተክርስቲያን አጸድ ቅበሩት አለችው። 

እርሱም በነገረችው መሠረት ከጓደኞቹ ጋር ሂዶ አስከሬኑን ባወጣ ጊዜ ርሔ እንደሚባል ሽቱ መዓዛው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ከአፉ የበቀለ አንድ የጽጌረዳ አበባ 🌹 አገኙ ደራሲው ይህንን አይቶ በዚህ አንጻር እመቤታችንን አመሰገናት 

#መንክር_እግዚአብሔር_በላዕለ_ቅዱሳኒሁ።
#እግዚአብሔር1በቅዱሳኑ_ላይ_ድንቅ_ነው።
                                                     መዝ 67 : 35 

⩩እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ፣
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፣
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሠሕ፣
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፣ 

⩩መልካሚቱ ርግብ የተባልሽ ማርያም ሆይ፣
ነጭና ቀይ መልክ ያለው አበባ ልጅሽን ታቅፈሽ፣
እንደ ሥርዓቱ ወደ ቤተ መቅደስ እንደገባሽበት ጊዜ ሁሉ፣
ደስ ካለው ከገብርኤልና እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤል ጋ፣
ከኅዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ። 

''ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ'' ክርስቶስ ለምን ተባለ ? 

ይህንን ቃል አስቀድመን በመኃ 5:10 ላይ እናገኘዋለን ኢየሱስ ክርስቶስ በልዩነት ቤተክርስቲያን ጸዐዳ በመለኮቱ ወቀይሕ በትስብእቱ እያለች ትሰብካለች ትናገራለች ይህም ሊቃውንት ሲታተት እንዲህ ነው። 

#ጸዐዳ መባሉ ንጽሐ ባሕሪውን ፤ አለመለወጡን ፤ አይመረመሬነቱን ይገልጻል። 

#ቀይሕ መባሉ በሰውነቱ የደረሰበትን ግፍ ፣ በደል ፣ ግርፊያ ፣ስቅለቱን ፣ ሞቱን ያሳያል። 

#ንዒ ርግብየ (መልካሚቱ ርግቤ ሆይ ነይ ) ርግብ ለምን እመቤታችን ተባለች ? 

ርግብ ኅዳጊተ በቀል ናት እመቤታችንም ናትና። 

ርግብ ርኅሩኅ ናት እመቤታችንም ናትና። 

ርግብ ለልጆቿ ትሳሳለች እመቤታችንም በልጇ አምነን የተጠምቀነውን እኛን ትሳሳልናለችና። 

ርግብ ለኖኅ ሐፀ ማየ አይኅ ነትገ! ማየ አይኅ ! ብላ በአፏ የወይራ ዝንጣፊ ይዛ  አብስራዋለች። አሁንም ለኛ ለምዕመናን የዓለም ሁሉ የጥፋት ውኃ መቅለሉን የመሻገሪያ ድልድይ መሰራቱን ከጥፋት ወደ ሕይወት መሻጋገራችን በክንዶቿ ክርስቶስን ታቅፋ አማናዊቷ ርግብ እመቤታችን ለዓለሙ ድኅነትን ታበስራለች። 

ስለዚህ ነገር እመቤታችንን ደራሲው ርግቤ አላት! 

ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ (ከደስተኛው ገብርኤል ጋር) ማለቱስ ? 

የገብርኤል የስሙ ትርጉም ብዙ ነው ለምሳሌ ፦
ኃያል
ድንቅ
አምላክ ወሰብእ
መልአከ ሰላም .... 

ከብዙ በጥቂቱ ይለዋል ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ የሚያረጋጋ ነውና አረጋጊ አፅናኝ መልአክም ነው ዓለመ መላእክት በታወከ ጊዜ እንዲህ ብሎ ያረጋጋቸው ፦ 

ንቁም በበሕላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ ! 

ሁላችንም በያለንበት ጸንተን እንቆይ ! አምላካችን እስኪገለጥልን ድረስ። 

ብሎ ዓለመ መላዕክትን ያበሰረ መልአክ የተሰጠው ሽልማት ድንግል ማርያምን ማብሰር ነው።*ከቶ ከዚህ በላይ ምን ሽልማት አለ ? 

ለዚያ ነው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ 

ዓቢይ ውእቱ ክብር ዘተውህበ ለከ ኦ ገብርኤል መልአክ ዜናዊ ፍሡሐ ገጽ ሰበከ ለነ ልደት እግዚእ ዘመጸአ ኃቤነ። 

ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምስራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው ! 

ደስተኛነቱ እየገለጸ የሚያመሰግነው በዚያውም ላይ ፈጥኖ ደራሽ ፍጡነ ረድኤት ነውና ከእርሱ ጋር ነይ አለ ይህነን ይዞ  #ቅዱስ_ገብርኤልን ደራሲው በመልክአ ገብርኤል እንዲህ ይለዋል። 

አልቦ እምሰብእ ዘከማየ ዘይቴክዝ ነግሐ ወሠርከ፣
ወአልቦ እመላእክት ናዛዜ ኅዙናን ዘከማከ፣
ወበእንተዝ ኀሠሥኩ አእሚርየ ኪያከ፣
ገብርኤል ናዝዘኒ ወአስምዐኒ ቃለከ፣
እሴተ ጸሎትየ ዝንቱ ዘአቅረብኩ ለከ። 

ከሰው ሁሉ እንደ እኔ የሚተክዝ የሚያዝን የለም
ከመላእክትም ወገን እንዳንተ ያለ አጽናኝ የለም
ይህንን አውቄ አንተን ፈለኩ
ገብርኤል ሆይ አረጋጋኝ ድምጽሕንም አሰማኝ
እያልኩ ይህንን ጸሎቴን አቀርባለሁ። 

''ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ'' ማለቱስ ? 

ቅዱስ ሚካኤል ርኅሩኅ ቸር መሆኑ በቅዱሳት መጻሕፍት በአበው ንግግር የተረዳ ነው (ሌሎቹ አይደሉም አላልንም !)
እንዲያውም ከዓይነ ሞት የተሰወረው ታላቁ ሄኖክ እንዲህ ይላል 

''ቅዱሳን ከተባሉ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ከጌታ በተሰጠው ቸርነት ለሰው ሁሉ ታዣዥና ምሕረትን የሚለምን ነውና።'' ሄኖ 16-5 

ብሎ ነገራችንን ያጸናልና ቅዱስ ያሬድም ድጓ በተባለ ድርሰቱ እንዲህ ይላል 

ሚካኤል እመላዕክት መኑ ከማከ ልዑል ?
አስተምህር ለነ ሰአልናከ፣
በዐሠርቱ ወበአርባዕቱ ትንብልናከ። 

ሚካኤል ሆይ ከመላእክት ወገን እንዳንተ ያለ ከፍ ያለ ማን ነው ?
በ14ቱ ምልጃዎችህ ማልድልን። 

እያለ ያነሳሳዋል #14ቱ_ምልጃዎች የተባሉትን በሌላ ጊዜ እናየዋለን። 

ሌላኛውም ደራሲም እንዲህ ይላል 

አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፣
እንበለ ባሕቲታ ማርያም ድንግል። 

በምሕረት እና በቸርነት ማንም የሚመስልህ የለም፣
ከእኅትህ ❤*ከማርያም ድንግል በቀር። 

#ንዒ_ርግብየ_ትናዝዝኒ_ኃዘነ_ልብየ። 
እመቤቴ ሆይ የልቤን ኃዘን ታረጋጊ ዘንድ ነይ ነይ ነይ ❤ 
ሁላችንንም በአማላጅነቷ አትለየን እመአምላክ ወላዲተ አምላክ ትርዳን። አሜን
                                                                

         ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethe
llettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments