Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ጥቅምት ፲፫


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፲፫ (13) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለዓለም ሁሉ መምሕር "ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ" እና ለአባ "ዘካርያስ ገዳማዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ ዮሐንስ አፈ ወርቅ +"+

=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ
ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ?
ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና
ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን
እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር "አፈ ወርቅ"
መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት
ልሞክር::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?

=>ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት
ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ
በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ
የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ
በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::

+ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

+ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ
ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት
እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ
ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ
አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ
ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

+ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ
በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው
ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል "አፈ ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው "አፈ ወርቅ" የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ
ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም
ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ
ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ "አልመልስም"
በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና
መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት
ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም
አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት
እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና
ለቅሶ ተደረገ::

=>ከዕረፍቱ አስቀድሞ አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ
አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ)

በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ:
አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ
መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ
ሲወርዱ ተመለከተ::

+ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው"ቁስጥንጥንያ:
ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን
እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ
እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ"
አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን
ቀጠሉ::

+በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ:
መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ
በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ
ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ
አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል
ጠየቀው::

+"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ
አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ
ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?"ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ
ይተረጉምለት ጀመር::

+"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ
የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ
ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ
መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ
ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ
ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ
ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች
አላወቀም::

+አሁን ግን ልጇ አምላክ ዘበአማን: እርሷም ወላዲተ
አምላክ መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም
ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ
"አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

+ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::

=>ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
¤ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
¤አፈ በረከት
¤አፈ መዐር (ማር)
¤አፈ ሶከር (ስኩዋር)
¤አፈ አፈው (ሽቱ)
¤ልሳነ ወርቅ
¤የዓለም ሁሉ መምሕር
¤ርዕሰ ሊቃውንት
¤ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
¤ሐዲስ ዳንኤል
¤ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
¤መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
¤ጥዑመ ቃል - - -

+"+ አባ ዘካርያስ ገዳማዊ +"+

=>ይህ ታላቅ ጻድቅ ባለ ጥዑም ዜና ነው:: ወላጆቹ
እሱንና አንዲት ሴትን ከወለዱ በሁዋላ አባቱ መንኖ
ገዳም ገባ:: ከዘመናት በሁዋላ ረሃብ በሃገሩ ሲገባ እናቱ
ወስዳ ለአባቱ ሰጠችው:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 7 ዓመት ነበር::

+በገዳም ከአባቱ ጋር ሲኖር ከመልኩ ማማር የተነሳ
አባቶች መነኮሳት "ይህ ልጅ ይህን መልክ ይዞ እንዴት
መናኝ መሆን ይችላል!" ሲሉ ሰማ:: በሌሊትም ተነስቶ
በሕጻን አንደበቱ "ጌታየ! መልኬ ካንተ ፍቅር ከሚለየኝ
መልኬን አጠፋዋለሁ" አለ:: ከገዳሙም ጠፋ::

+አባትም በጣም አዘነ:: ከ40 ቀናት በሁዋላ ግን ሊያዩት የሚያሰቅቅ: አካሉ ሁሉ የቆሳሰለ አንድ ነዳይ ሕጻን መጥቶ ወደ ገዳሙ ተጠጋ:: ይህ ሕጻን በጾም: በጸሎትና በትሕትና ተጠምዶ ለ45 ዓመታት አገለገለ::

+በነዚህ ዓመታት ሁሉ ይህ አካሉ የተለወጠ ሕጻን ቅዱስ ዘካርያስ መሆኑን ያወቀ የለም:: እንዲህ የቆሰለውም አሲድነት ካለው የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ሰጥሞ ለ40 ቀናት በመጸለዩ ነው::

+በመጨረሻ ግን አባቱ በምልክት ለይቶት አለቀሰ::
"ልጄ! አንተ ለእኔ አባቴ ነህ" ብሎታል:: አበው
መነኮሳትም ተሰብስበው እጅ ነስተውታል:: በ7 ዓመቱ
የመነነው አባ ዘካርያስ በ52 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ
በክብር ተቀብሯል::

=>አምላከ አፈ ወርቅ ዮሐንስ የድንግል እመ ብርሃንን
ፍቅሯንና ውዳሴዋን ይግለጽልን:: ከአባቶቻችን ክብርና
በረከትንም ያሳትፈን::

=>ጥቅምት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት
=
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
2.አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
3.አባ ማርዳሪ ጻድቅ
4.ቅዱስ አብጥማዎስ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

=>+"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ
የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ
ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16)

         ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethe
llettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments