✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ነሐሴ ፲፰ ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለሊቁ #ቅዱስ_እለእስክንድሮስ
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ #ቅዱስ_እለእስክንድሮስ_ሊቅ +"+
=>ቅዱሱ ታላቅ የሃይማኖት ጠበቃ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ
(የተወለደባት) #ግብጽ ናት:: የተወለደው በ3ኛው መቶ
ክ/ዘመን ሲሆን በምግባሩ: በትምሕርቱ ለምዕመናን
ጥቅም ሆኗቸዋል:: ቅዱስ እለእስክንድሮስ ገና ልጅ ሳለ ምሥጢረ ክርስትናን ይማር ዘንድ ወደ #ቅዱስ_ዼጥሮስ
#ተፍጻሜተ_ሰማዕት ሔዷል::
+ቅዱስ ዼጥሮስ የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክና ሊቅ ሲሆን
በታሪክ የዘመነ ሰማዕታት መጨረሻ ተብሎ ይታወቃል::
ከዚህ ሰማዕት ሥር የሚማሩ ብዙ አርድእት ቢኖሩም 3ቱግን ተጠቃሽ ነበሩ::
1.ቅዱስ እለእስክንድሮስ (ደጉ)
2.አኪላስ (ውዳሴ ከንቱ ወዳጅ)
3.አርዮስ (የቤተ ክርስቲያን ጠላት)
+ከእነዚህም አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ሲታትር ነበር:: አኪላስ ደግሞ ሆዱ ዘመዱ: ስለ ምንም
የማይጨንቀው ሰው ነበር:: ቅዱስ እለእስክንድሮስ ግን
በጾምና በጸሎት እየተጋ መምሕሩን ቅዱስ ዼጥሮስን
ለመተካት (ለመምሰል) ይጥር ነበር::
+ወቅቱ ዘመነ ሰማዕታት እንደ መሆኑ ቅዱሱ ከመምሕሩ ጋር ብዙ ነገሮችን አሳልፏል:: አርዮስ ክዶ: ቅዱስ ዼጥሮስ ካወገዘው በሁዋላ እንደ ባልንጀራ ገስጾ
ሊመልሰውም ሞክሮ ነበር:: ነገር ግን የአርዮስን ክፋት
ከጌታ ዘንድ የተረዳው ቅዱስ ዼጥሮስ ደቀ መዝሙሩን
እለእስክንድሮስን ጠርቶ መከረው::
+"እኔ ከሞትኩ በሁዋላ አኪላስ ይተካል:: ከአርዮስ ጋር
ስለሚወዳጅ በ6 ወሩ ይቀሠፋል:: አንተ ግን ከአርዮስ
መርዝ ተጠበቅ" አለው:: ይህንን ካለው በሁዋላ
ወታደሮች የቅዱስ ዼጥሮስን አንገት ቆረጡ:: ይህ
የተደረገውም እ.ኤ.አ በ311 ዓ/ም ነው::
+ወዲያውም አኪላስ ተሾመ:: እንደ ተባለውም ከአርዮስ ጋር ስለተወዳጀ በ6 ወሩ ተቀሰፈ:: በዚያው ዓመትም ቅዱስ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ (ግብጽ) 19ኛ ፓትርያርክ (ሊቀ ዻዻሳት) ሆኖ ተሾመ::
+ሊቁ ሲሾም መልካም አጋጣሚ የነበረው ያ የመከራ
ዘመን ማለፉ ሲሆን በጣም ከባዱ ግን የአርዮስ
ተከታዮች ከተገመተው በላይ መበብዛታቸው ነው::
ቅዱሱ ሊቅ በዽዽስና መንበሩ ለ17 ዓመታት ሲቆይ
ዕንቅልፍም ሆነ ዕረፍት አልነበረውም::
+በዚህ እየጾመ: እየጸለየ: ሥጋውን እየጐሰመ ለፈጣሪው ይገዛል:: በዚያ ደግሞ ሕዝቡን ነጋ መሸ ሳይል ያስተምራል:: ምዕመናንን ከአርዮስ የኑፋቄ መርዝ ለመታደግ ባፍም: በመጣፍም (በደብዳቤ) አስተማረ::
+ብርሃን የሆነ ደቀ መዝሙሩ #ቅዱስ_አትናቴዎስ
እያገዘው: አርዮስን ከነአበጋዞቹ አሳፈሩት:: ለእያንዳንዷ
የኑፋቄ ጥያቄ ተገቢውን መንፈሳዊ ምላሽ ከመስጠቱ
ባለፈ አርዮስን ከአንዴም 2: 3ቴ በጉባኤ አውግዞታል::
+ነገሩ ግን በዚህ መቁዋጨት ባለመቻሉ ንጉሡ ቅዱስ
ቆስጠንጢኖስ ጉባኤ ኒቅያ እንዲደረግ አዋጅ ነገረ::
እ.ኤ.አ በ325 ዓ/ም (በእኛ በ318 ዓ/ም) ከመላው
ዓለም ለጉዳዩ 2,348 የሚያህሉ ሰዎች ተሰበሰቡ::
ከእነዚህ መካከል 318ቱ ሊቅነትን ከቅድስና የደረቡ: ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ያሳለፉ ነበሩ::
+ይህንን የተቀደሰ ጉባኤ እንዲመራ ደግሞ መንፈስ
ቅዱስ ቅዱስ እለአእስክንድሮስን መረጠ:: ሊቁም አበው ቅዱሳንን አስተባብሮ በሺህ የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉትን አርዮስን ተከራክሮ ረታው::
+በጉባኤው መጨረሻ አርዮስ "አልመለስም" በማለቱ
እርሱን አውግዘው: ጸሎተ ሃይማኖትን ሠርተው: 20
ቀኖናወችን አውጥተው: መጽሐፈ ቅዳሴ ደርሰው:
አሥራው መጻሕፍትን ወስነው: ቤተ ክርስቲያንን በዓለት
ላይ አጽንተው ተለያይተዋል:: የዚህ ሁሉ ፍሬ አበጋዙ ደግሞ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ነው::
+እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን "#ወልድ_ዋሕድ:
#አምላክ: #ወልደ_አምላክ: #የባሕርይ_አምላክ"
መሆኑን መስክሮ ክብርን አግኝቷል:: የእምነታችንም
መሠረቱ ይሔው ነው:: ክርስቶስን "ፈጣሬ ሰማያት
ወምድር: የባሕርይ አምላክ: ዘዕሩይ ምስለ አብ
በመለኮቱ (ከአባቱ ጋር በመለኮቱ የሚተካከል)" ብለው
ካላመኑ እንኩዋን ድኅነት ክርስትናም አይኖርም::
+ከጉባኤ #ኒቅያ በሁዋላ ቅዱስ እለእስክንድሮስ
በመልካሙ ጐዳና ሲጋደል: ምዕመናንንም ሲያጸና ኑሯል:: ዘወትር ወንጌልን በፍቅር ያነብ ነበርና ሲጸልይ የብርሃን ምሰሶ ይወርድለት ነበር::
+ስለ ውለታውም #ቤተ_ክርስቲያን በግብጽ ካበሩ 5ቱ
#ከዋክብት_ሊቃውንት እንደ አንዱ ታከብረዋለች:: ቅዱሱ ሊቅ በ328 ዓ/ም (በእኛ በ320 ዓ/ም) በዚህች ቀን ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::
=>ቸር አምላከ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን ከነጣቂ ተኩላ
ይጠብቅልን:: ከቅዱሱ ሊቅም በረከትን ይክፈለን::
=>ነሐሴ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (3ኛ ቀን)
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ዲያቆን
4.አባ ዘክርስቶስ ዘወሎ (ኢትዮዽያዊ ጻድቅ)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
=>+"+ . . . ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ
ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩአችሁ እጽፍላችሁ
ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: +"+ (ይሁዳ. 1:3)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment