✞✞✞✝✝ እንኳን ለንጹሐት እናቶቻችን ቅድስት እንባ መሪና እና ቅድስት ክርስጢና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞
✞✞✞ ✝✝ቅድስት እንባ መሪና✝✝ ✞✞✞
✞✞✞ ቤተ ክርስቲያን "እንቁዎቼ" ከምትላቸው ሴት ጻድቃን አንዷ ቅድስት እንባ መሪና ናት:: ጣዕመ ዜናዋ: ሙሉ ሕይወቷ: አስገራሚም: አስተማሪም ነው:: ቅድስቷ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገች ክርስቲያን ናት:: ወላጆቿ ከእርሷ በቀር ሌላ ልጅ የሌላቸው ሲሆን በአኗኗራቸውም ደግና ቅን ነበሩ::
ቅድስት እንባ መሪና ትክክለኛ ስሟ "መሪና" ነው:: ምክንያቱም "እንባ መሪና" የወንድ ስም ነውና:: ነገር ግን በወንድ ስም የተጠራችበት የራሱ ታሪክ አለውና እርሱን እንመለከታለን::
ቅድስት መሪና ገና ልጅ ሳለች እናቷ ማርያም ሞተችባት:: ደግ አባት አንድ ልጁን በሥጋዊም: በመንፈሳዊም ሳያጐድልባት አሳደጋት:: ዕድሜዋ አሥራ አምስት ዓመት በሆነ ጊዜ ወደ ፊቱ አቅርቦ "ልጄ! እኔ ወደ ገዳም ስለምሔድ አንቺን መልካም ባል ላጋባሽ::" አላት::
ቅድስት መሪናም "ነፍሰ ዚአከ ታድኅን: ነፍሰ ዚአየኑ ታጠፍእ - የአንተን ነፍስ አድነህ እንዴት የእኔን ትተዋታለህ? እኔም እመንናለሁ::" አለችው:: አባቷ የተናገረችው ከልቧ እንደሆነ ሲያውቅ "ልጄ! ገዳም ሁሉ በአካባቢው የወንድ ብቻ ነውና ስሚኝ::" አላት::
እርሷ ግን "አባቴ! ግዴለህም: ስሜን እንደ ወንድ ቀይረህ: አለባበሴንም ለውጥ::" አለችው:: (እንደ ወንድ ለበሰች ማለት ግን እንደ ዘመኑ ዓይነት እንዳይመስላችሁ አደራ!)
ከዚያ አባትና ልጅ ሃብት ንብረታቸውን ሸጠው ለነዳያን አካፈሉ:: በፍጹም ልባቸውም መነኑ:: በደረሱበት ገዳም ቅድስት መሪና በወንድ ስም "እንባ መሪና" በሚል ገባች:: ቀጣዩ ሥራዋ እንደ ወንዶች እኩል መስገድ: መጾምና መጸለይ ነበር::
ይህችን ቅድስት ልናደንቃት ግድ ይለናል:: ማንም በእርሷ አይፈተንም:: አያውቋትምና:: እርሷ ግን ወጣት ሆና: አንድም ሴት በሌለበት ገዳም ጸንቶ መቆየት በራሱ ልዩ ነው:: መልአካዊ ኃይልንም ይጠይቃል::
ተጋድሎዋ በጣም ስለ በዛ ወንድሞች መነኮሳት ይደነቁባት ነበር:: ጺም ስለሌላትና ድምጿ ቀጭን ስለሆነ አልተጠራጠሩም:: ምክንያቱም ጃንደረባ ናት ብለው አስበዋልና:: ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን አባቷ ታሞ ከማረፉ በፊት አበ ምኔቱን ጠርቶ "ወደ ከተማ ልጄን እንዳትልክብኝ: አደራ!" ብሎት ነበር::
ያም ሆኖ አንዳንድ መነኮሳት ቅሬታ በማንሳታቸው ወደ ከተማ ተላከች:: ችግሩ ለተልእኮ ባደሩበት ቤት አንድ ጐረምሳ ገብቶ የአሳዳሪውን ልጅ ከክብር አሳንሷት ሔደ:: ሲወጣም "ድንግልናሽን ያጠፋ ማን ነው? ካሉሽ ያ ወጣት መነኩሴ አባ እንባ መሪና ነው በይ::" አላት::
ከሦስት ወራት በኋላ የዚያች ዘማ ሴት ጽንስ በታወቀ ጊዜ ለአባቷ "አባ እንባ መሪና እንዲህ አደረገኝ::" አለችው::
አባት መጥቶ እየጮኸ መነኮሳትን ተሳደበ:: አበ ምኔቱ ግራ ተጋብቶ ቢጠይቀው "የአንተ ደቀ መዝሙር እንባ መሪና ልጄን ከክብር አሳነሳት::" አለው:: አበ ምኔቱ እውነት መስሎታልና ቅድስቲቱን ጠርቶ ቁጣና እርግማንን አወረደባት:: በዚያች ሰዓት ተንበርክካ አንድ ነገር ወሰነች::
"ሴት ነኝ" ብሎ መናገሩስ ቀላል ነው:: ግን ደግ ናትና የእነዛን አመጸኛ ሰዎች ኃጢአት ልትሸከም ወሰነች:: ቀና ብላ "ማሩኝ ወጣትነት ቢያስተኝ ነው?" አለቻቸው:: ተቆጥተው ዕለቱን እየገፉ ከገዳም አስወጧት:: ከባድ ቀኖናም ጫኑባት:: ከስድስት ወራት በኋላም የእርሷ ልጅ ነው የተባለ ሕፃን አምጥተው ሰጧት::
ይህኛው ግን ከባድ ፈተና ሆነባት:: እንዳታጠባው አካሏ በገድል ደርቁአል:: በዚያ ላይ ድንግል የሆነች ሴት ወተት የላትም:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: የበጋውን ሐሩር: የክረምቱን ቁር ራሷ ታግሣ ለሕፃኑ ከእረኞች ወተት እየለመነች: እየመገበች ሦስት ዓመታት አለፉ::
በዚህ ጊዜ ወደ ገዳሙ ከከባድ ቀኖና ጋር ተመለሰች:: ሕፃኑን ስታሳድግ: ለገዳሙ ስትላላክ: ምግብ ስታዘጋጅ: ውኃ ስትቀዳ: የእያንዳንዱን ቤት ስታጸዳ ሰላሳ ሰባት ዓመታት አለፉ:: ሕፃኑም አድጐ ደግ መናኝ ወጣው:: (የቅድስቷ እጆች ያሳደጉት የታደለ ነው::)
በመጨረሻ ቅድስት መሪና (እንባ መሪና) ታማ ዐረፈች:: እንገንዛለን ብለው ቢቀርቡ ሴት ናት:: እጅግ ደንግጠው አበ ምኔቱን ጠሩት:: በዙሪያዋ ከበው እንባቸውን አፈሰሱ:: ጸጸት እንደ እሳት በላቻቸው:: ሥጋዋን በክብር ገንዘው: በአጐበር ጋርደው: በራሳቸው ተሸክመው ምሕላ ገቡ::
ሙሉውን ቀን "ስለ ቅድስት መሪና ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን?" ሲሉ ዋሉ:: ድንገት ግን ከተባረከ ሥጋዋ "ይቅር ይበለን::" የሚል ድምጽን ሰምተው ደስ ብሏቸው ቀበሯት:: እነዚያ ዝሙተኞችም ከእርሷ ይቅርታን እስካገኙበት ቀን አብደው ኑረዋል::
✞✞✞ ✝✝ቅድስት ክርስጢና (ክርስቲና)✝✝ ሰማዕት ✞✞✞
✞✞✞ በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን የተነሳችው ሰማዕቷ ቅድስት ክርስጢና ከዋና ሰማዕታት አንዷ ስትሆን በዓለማቀፍ ደረጃም ተወዳጅ ናት:: ከመነሻው የሃገረ ገዢ ልጅ ብትሆንም ቤተሰቦቿ ጣዖት አምላኪዎች ነበሩ:: አጥር አጥረው: በር ዘግተው: ከማንም ጋር ሳትገናኝ: ጣዖት እንድታጥን አደረጓት::
ወጣት በሆነች ጊዜ ግን ጣዖቱን ተመለከተችው: መረመረችው:: አምላክ እንዳልሆነም ተረዳች:: ወደ ምሥራቅ ዙራ "እውነተኛው አምላክ ራስህን ግለጽልኝ?" ስትል ጸለየች::
መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ክርስትናን በልቡናዋ አሳደረባት:: ቅዱስ መልአክም መጥቶ ሰማያዊ ሕብስትን መገባት::
ፈጥና ተነስታ አብርሃማዊት ቅድስት ጣዖታቱን ሰባበረች:: በዚህ አባቷ ተቆጥቶ (ርባኖስ ይባል) በዛንጅር (ሥጋን የሚልጥ: የሚቆርጥ ጀራፍ ነው::) አስገረፋት:: ንጽሕት ናትና ከአካሏ ደም ሳይሆን ጣፋጭ ማር ፈሰሰ::
በድጋሚ በእሳት ቢያቃጥላትም አልነካትም:: ድንገት ግን አባቷ ርባኖስ ተቀሰፈ:: ሌላ ንጉሥ መጥቶ በእሳትም: በስለትም አሰቃያት:: እሱንም መልዐክ ቀሠፈው:: ሦስተኛው ንጉሥ ግን ብዙ አሰቃይቶ: ጡቶቿንና ምላሷን አስቆረጣት:: በመጨረሻውም በዚህች ቀን ለእፉኝት (እባብ) አስነድፎ ገድሏታል::
✞✞✞ የቅዱሳት እናቶቻችን አምላክ ለእነርሱ የሰጣቸውን ጽናት አይንሳን:: ከበረከታቸውም አብዝቶና አትረፍርፎ ያድለን::
✞✞✞ ነሐሴ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት እንባ መሪና ገዳማዊት
2.ቅድስት ክርስጢና ሰማዕት
3.ቅዱስ ለውረንዮስ ሰማዕት
4.ሰላሳ ሺ ሰማዕታት (የቅድስት ክርስቲና ማኅበር)
5.አበው ቅዱሳን ሐዋርያት (ወላዲተ አምላክን ለመገነዝ በዚህ ዕለት ተሠብስበዋል::)
✞✞✞ ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት
3.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
✞✞✞ "ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ::" ✞✞✞
(፩ጴጥ. ፫፥፫)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment