††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ብሩታዎስ †††
††† ሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው የውዳሴ ማርያም ደራሲ ነው::ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሙቶ ከተነሳ ከ8 ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ያምናል:: ባመነ በ6 ዓመቱ (ማለትም ከክርስቶስ ዕርገት 14 ዓመታት በኋላ) እየሰበከ ግሪክ አቴና /ATHENS/ ደርሶ ብዙ ፈላስፎችን ወደ ክርስትና ሲያመጣ አንዱ ይህ ቅዱስ ብሩታዎስ ነበር::
ቅዱስ ብሩታዎስ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: ሐዋርያትን ተከትሏቸው: እነሱም ቅስና ሹመውታል:: ጵጵስና እንሹምህ ቢሉት በፊታቸው ተንበርክኮ አልቅሷል:: አይገባኝም ማለቱ ነበር::
ታዲያ ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያት ስለ ድንግል እመቤታችን ሲጨዋወቱ እየሰማ "መቼ አይቻት" እያለ በፍቅሯ ይቃጠል ነበር:: አንዴ ግን ወሰነ:: "እመቤቴን ሳላያት እንቅልፍ አላይም" ብሎ በሽማግሌ እግሮቹ ከግሪክ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ::
የሚገርመው እርሱ እሥራኤል (ጽርሐ ጽዮን) የደረሰው በ49 ዓ/ም ጥር 21 ቀን እመቤታችን ልታርፍ ሰዓታት ሲቀራት ነበር:: ቅዱሱ ሽማግሌ እመቤታችንን በአካለ ሥጋ ስላያት በፊቷ እንደ እንቦሳ ዘለለ:: እየሰገደም አመሰገናት:: እመ ብርሃንም በንጹሐት እጆቿ ባረከችውና ዐረፈች::
ይሕን ጊዜ ምሥጢር ተገልጦለት ዜማና ቅኔ ያለውን የመጀመሪያውን ውዳሴ ማርያም ዕለቱኑ ደርሶ ለሐዋርያት ሰጣቸው:: እነርሱም ከምስጋናው ጣዕም የተነሳ ተደነቁ:: ከሐዘናቸውም ተጽናኑ::
ይሕ ድርሰት በዘመነ ሰማዕታት በመጥፋቱ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አምልቶና አጉልቶ ደርሶታል::
ቅዱስ ብሩታዎስ ግን ብዙ ሃገራትን በሐዋርያነት አዳርሶ በመልካም ሽምግልና አርፏል::
††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ብሩታዎስ ላይ ያሳደረውን የድንግል እናቱን ፍቅር በእኛም ላይ ያሳድርብን::
††† ሚያዝያ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያዊ
2.አባ ዕንባቆም ጻድቅ ሰባኬ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ (በትውልድ የመናዊ በጸጋና አገልግሎት ግን ኢትዮጵያዊ አባት ናቸው:: ደራሲ : ሰማዕት : ባሕታዊና ሊቀ ምኔትም ነበሩ::)
3.ቅዱስ አካክሪስ
4.ቅዱስ ይወራስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1፡ እግዝእትነ ማርያም
2፡ አበው ጎርጎርዮሳት
3፡ አባ ምዕመነ ድንግል
4፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
5፡ አባ አሮን ሶሪያዊ
6፡ አባ መርትያኖስ
7፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል
††† "ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሠጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና:: ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል . . . ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድለት እያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል::" †††
(፩ቆሮ. ፲፪፥፯-፲፩)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment