Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ሚያዚያ ፲፰ አቡነ አቢብ

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ✞✞✞

አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

✝ ልዩ ስሟ አምዓዳ በምትባል ሀገር በሉፊ አውራጃ በሮም አገር አንድ ጽኑ ክርስቲያን ነበር፡፡

✝ ይህ ክርስቲያን ስሙ አብርሃም ይሰኛል፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከአንዱ አገር ወደ ሌላ አገር ሲሰደድ የኖረ እግዚአብሔርን የሚፈራ ለሰው ሁሉ በጎን የሚያደርግ ለነዳይና ለምስኪን ባልቴቶች እናት አባት ለሞቱባቸዉ ልጆች ምጽዋትን የሚሰጥ ነበር፡፡

✝ እንዲሁም እንደርሱ ደግ የሆነች ስሟ ሐሪክ የምትባል ደግ ሚስት ነበረችው የስሟ ትርጉምም  በክርስቶስ የታመነች ማለት ነው፡፡ 

✝ እነዚህ ሁለት ደግ ክርስቲያኖች ታዲያ ልጅ አልነበራቸውም ነገር ግን
ልጅ ባይኖራቸውም እለት እለት እግዚአብሔርን ከማመስገን በቀር አማረው አያውቁም ነገር ግን ለቤተ እግዚአብሔር  አገልጋይ የሚሆን አንድ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ በአንቃዕድዎ ወደ እግዚአብሔር ይለምኑ ነበር፡፡

✝ አንድ ቀን መልዐከ እግዚአብሔር ለዚህ   ደግ ሰው ተገልፆ ይኽ ፍሬ የአንተ ነው እርሱም ወደ እኔ የሚቀርብ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ፈቃዱንም የሚፈፅም ያማረ መባዕ ነው ብሎ እጅግ መልካም ፍሬን በእጁ ሰጠው፡፡

✝ ይኽ ደግ ሰው አብርሃምም ከእንቅልፉ ተነስቶ ይህንን  በህልሙ የሰማውንና የአየውን ነገር ኹሉ ለሚስቱ ሐሪክ ነገራት እርሷም ታላቅ ደስታ ተደሰተች ልዑል እግዚአብሔርን በአንድነት አመሰገኑ፡፡ሚስቱ ሐሪክም ፀነሰች፡፡

✝ ይኽቺ ሚስቱ ሐሪክ በፀነሰች ጊዜም በቤታቸው መካከል ሁለንተናው መልካምና ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉ ላይ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈ ጽሕፈትን አዩ ጽሕፈቱም በጽዮን አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ቅዱስ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቡላ የሚል ነው፡፡

✝ ከዚህም በኀላ ሐሪክ መልከ መልካምና ከብርሃናት ይልቅ ፊቱ የሚያበራ ወንድ ልጅን ወለዱ፡፡እናቱና አባቱ ይህንን በአዩ ጊዜ ታላቅ ደስታ ተደስተው ለነዳያን ምጽዋትን ለአብያተ ክርስቲያናት የሚገባውን በወርቅና በብር ያጌጡ የነዋየ ቅድሳት አልባሳትን ሰጡ ስሙንም ቡላ ብለው ሰየሙት፡፡ትርጓሜውም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው፡፡

✝ እናትና አባቱም በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት አሥር አመት በሆነው ጊዜም በመጀመሪያ አባቱ አብርሃም አረፈ ከትንሽ ቀናት በኀላ እናቱ ሐሪክ አረፈች፡፡

✝ በዚያን ዘመን ታዲያ ንጉሡ ቤተ ክርስቲያንን እንዲዘጉ እና ቤተ ጣዖት እንዲከፍቱ ክርስቲያን ሁላቸው የምስጋና ባለቤት ጌታችንና መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን (ሎቱ ስብሐት) እንዲክዱ የሚል ወደዚያች አገር ደረሰ፡፡

✝ ይህ የተባረከ ብላቴና ቡላም ይህንን በሰማ ደጋጎች ክርስቲያንም ሲሰቃዩ ባየ ጊዜ ስለ ክርስቶስ በሰማዕትነት ይሞት ዘንድ ጨክኖ ሕዝብን ሰማዕትነት ለመቀበል በወዲህም በወዲያም ያሉትን ሕዝቡን እየገፋ ሄዶ ንጉሥ አቅሮጵስ ካለበት ቀርቦ ያፈርክና የተዋረድክ የረከስክ የጽድቅ ሁሉ ጠላት የዲያቢሎስ መልእክተኛ አንተና ንጉስክ የተነቀፋችሁ የምታመልኳቸው ጣዖታትም የተዋረዱና በምድር የረከሱ ናቸው አለው፡፡

✝ ንጉሡም ሰምቶ ይህንን ወጣቱ ቡላን አስረው ከፊቱ ያቆሙት ዘንድ አዝዞ ተመልከቱ የእሊክ ክርስቲያን ልቦናቸው የጸና ነው ትንሽ ብላቴና ሆኖ ሳለ ምንም አልፈራም ይልቁኑም እንድቀጣው ይቃወመኛል እንጂ አለ፡፡

✝ ይህንንም ብሎ በሚቆራርጥ ብረት ሠንሰለት አሰሩት ጀርባውን በአለንጋ እንዲገርፉት ሰውነቱም እየለያዩ እየቆራረጡ የውስጥ አንጀቱን በተቆለፈ ብረትና በስለታማ መጋዝ እጆቹንና እግሮቹን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡

✝ በእንዲህ ባለ መከራ ቢያሰቃዩትም ተመልሶ በእግሩ ይቆማል እንጂ አልሞተም ንጉሡ እሊህ ክርስቲያን መተታቸውን ተመልከቱ አለ፡፡

✝ እንዲሁም አባ ቡላ በአሥራ አምስት አመቱ ከሌላ ንጉሥ ጋር እንደ ቀድሞ ለረከሱ ጣዖቶች አልሰግድም በማለቱ ብዙ ስቃይ አሰቃየው በመጨረሻም አንገቱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ብጹዕ ጻድቅ ቡላም ራሱን ከመቁረጣቸው አስቀድሞ ከመዝሙረ ዳዊት ሳምኬት ዐማፅያንን ጠልቼ ሕግህን ተከተልኩ ረዳቴና መጠጊያዬ አንተ ነህ በቃልህም አመንኩ የአምላኬን ትዕዛዝ እፈፅም ዘንድ  ዐማፅያን ከእኔ ራቁ በሕይወት እኖር ዘንድ እንደ ቃልህ ተቀበለኝ ተስፋዬንም አታስቀርብኝ ርዳኝ አድነኝ ሁል ጊዜ ሕግህን እናገራለሁ ከትእዛዝህ የሚርቁ ሁሉ ምኞታቸው አመፃ ነውና አዋረድኻቸው እሊኽ በምድር ያሉ ኃጥአን ከዳተኞች ናቸው፡፡ ስለዚህም አምልኮተ ሕግህን ወደድኹ፡፡ከሕግህ የተነሣ ፈርቻለሁና በአንተ መታመንን ከሰውነቴ ጋራ አስማማ፡፡ የሚለውን ጸሎት ጸለየ፡፡

✝ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቡላም በዚህች ቀን በሚያዝያ 18 አንገቱን ተቆረጠ በዚህን ጊዜ መልአከ እግዚአብሔር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ወርዶ ራሱን ወስዶ ከሥጋው ቢያገናኘው እንደነበረ ሆኖ ተነሣ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም አይዞህ አትፍራ እመን ጽና እግዚአብሔር ይረዳሃል ፡፡በሃገሪቱ ዳረቻ ወደ አለዉ ገዳም ሂድ እኔ የምሰጥህ በእጄ ያለች ልብስህ ሁል ጊዜ ይህች ናት ጌታችን ከወዳጆቹ ቅዱሳን መነኮሳት ጋራ ተሳታፊ እንድትሆን አዝዞኻል ብሎ የብርሃን መስቀል ምልክት ያላት አስኬማንም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ተሰወረ፡፡

✝ ጻድቁ አባታችን አቡነ አቢብ(ቡላ) ጌታችንና መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መፍቅሬ ሰብእ (ሰውን ወዳጅ) አምላካቸውን አርአያ ያደረጉ ለሰው ያላቸውን ፍቅር አድንቆ ከማዕድ በኀላ ስብሐት ተብሎ የተረፈውን በእንተ አቡነ አቢብ ብሎ ሦስት ጊዜ የተመገበውን ሰው ሁሉ እስከ አሥር ትውልድ እምርልሃለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡

✝ የንዑድ ክቡር ጻድቁ አባታችን አቡነ አቢብ (ቡላ) ጸሎታቸዉና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኹን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ✞

(በዮሐንስ ዘሐረር - ዝክረ ቅዱሳን)

ምንጭ፡ ገድለ አቡነ አቢብ

     ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
        ✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
    ✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
   
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ


ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!። 
  "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://
gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments