††† እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ሰርጊስ ወቴዎፍሎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ †††
††† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::
ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::
እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::
እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::
በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል::
እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ባኮስ እና ሰርጊስ (ሰርግዮስ) ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም ነበር::
ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ ሁለቱ ቅዱሳን ሥራ አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና::
በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው::
ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ:: ይጸልያሉ:: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ::
ከቆይታ በኋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ::
ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ::
በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቂያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በኋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት::
መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት 4 ቀን በሆነ ጊዜ ግን ሁለቱን ለያዩዋቸው:: ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት::
ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው:: በአካባቢውም "ባባ" እና "ማማ" የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት::
ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ6 ቀናት ካሠሩት በኋላ እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል: ተአምራትም ታይተዋል::
††† ቅዱስ ቴዎፍሎስና ቤተሰቡ †††
††† ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ይኖር የነበረ ጽኑዕ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔር ሲያድለው ደግሞ ጸንታ የምታጸና: በርትታ የምታበረታ ሚስትን ሰጠው:: ስሟም ጰጥሪቃ ይባላል::
በክርስትናዋና በፈጣሪዋ ፍቅር ላይ ይሉኝታና ድርድርን የማታውቅ ብርቱ ሴት ናት:: ሁለቱ ተጋብተው በሕጉና በሥርዓቱ ሲኖሩ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኛቸውና ቅድስት ጰጥሪቃ ጸነሰች:: በወለደችውም ጊዜ "ደማሊስ" ስትል በሃገራቸው ልሳን ስም አወጣችለት::
ልክ ግን ከአራስነት አልጋዋ በተነሳችበት ወራት ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ድንገት ደረሰ:: እሷም አካሏ አልጸናም: ልጇም ገና 5 ወሩ ነው:: ባሏ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ደግሞ በጨካኙ ንጉሥ እጅ መውደቁን (መታሠሩን) ሰማች::
ይኼ እጅግ ከባድ ፈተና ቢመስልም እርሷ ግን ልጇን አዝላ ወደ እሥር ቤት ሔደች:: ባሏንም "ወንድሜ! እኔና ልጅህን በክርስቶስ ዘንድ ስለምታገኘን ጽና:: ክብርህን እንዳትተው" አለችው:: እርሱም ደስ ብሎት ብዙ መከራን ተቀበለ::
ግርፋቱ: እሳቱ ስለቱ ሁሉ ሲያልፍበት በተአምራቱ አሕዛብን ማረከ:: ቅዱስ መልአክም ከሰማይ ወርዶ ማርና ወተትን መገበው:: ከዚያም በዚህ ቀን ለአንበሳ ተሰጠ:: አንበሳውም ለቅዱሱ ሰግዶ: እግሩንም ስሞ: አንገቱን ተጭኖ ገደለው::
ወዲያው ሚስቱ ቅድስት ጰጥሪቃ ተይዛ እርሷም ከነ ልጇ ለአንበሳ ተሰጠች:: በዚህ ጊዜ የ5 ወር ሕጻን ቅዱስ ደማሊስ አፉን ከፍቶ "እኔስ በሥላሴ አምናለሁና አንበሳን አልፈራም" ሲል እየሳቀ ጮኸ:: ወዲያውም እናትና ልጅን አንበሳው ገደላቸው:: ቅዱሱ ቤተሰብም ለክብር በቃ::
††† አምላከ ሰማዕታት ጽንዐታቸውን: ትእግስታቸውንም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ኅዳር 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕት
2.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሰማዕት
3.ቅዱሳን ጰጥሪቃና ደማሊስ (የቅዱሱ ሚስትና ልጅ)
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ (ልደቱ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
6.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ
††† "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" ††† (ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethellettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment