በእንተ ስማ ለማርያም:
=>+"+ እንኩዋን "ለቅድስት ወብጽዕት ሐና" (እመ ማርያም) ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+*" ብጽዕት ሐና "*+
=>"ሐና" ማለት በእብራይስጥኛው "የእግዚአብሔር ስጦታ" እንደ ማለት ነው:: "ሐና: ዮሐና: ሐናንያ" የሚሉ የዕብራይስጥ ስሞች ትርጉማቸው ተወራራሽ ነው:: የዚህችን ቅድስት እናት ክብሯን መናገር የሚችል የለም:: እርሷ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ወልድ በሥጋ አያቱ ተብላለችና::
+አንድም ለሰማይና ለምድር ንግስት ለድንግል ማርያም ወላጅ እናቷ ናትና:: ከዓለም ሴቶች ሁሉ የቅድስት ሐና ማሕጸን እንደ ምን ይከብር! በፍጥረት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥንተ አብሶ (የአዳም በደል) መተላለፍ የቀረው በማሕጸነ ሐና ውስጥ ነውና:: (ለዚህ አንክሮ ይገባል!!!)
+ይስሐቅን የተሸከመ የሣራ ማሕጸን ቡሩክ ከተባለ የቅድስት ሐናማ እንደምን አይባል! ከፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንደ መረጠ ሁሉ ቅድስት ሐናንም ለአያትነት መርጧታል::
=>ለመሆኑ ቅድስት ሐና ማን ናት? ለዚህ ክብርስ ያበቃት ምሥጢረ ቅድስናዋ ምንድን ነው?
+ቅድስት ሐና ትውልዷ: ነገዷ ከላይ ከቅዱስ አብርሃም: ከታች ደግሞ ከነገደ ካህናት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
*አብርሃም ይስሐቅን: ይስሐቅ ያዕቆብን: ያያዕቆብ ደግሞ ሌዊንና 11 ወንድሞቹን ይወልዳል::
*ሌዊ ቀዓትን: ቀዓት እንበረምን: እንበረም አሮን ካህኑን ይወልዳሉ::
*ቅዱስ አሮን አልዓዛርን: አልዓዛር ፊንሐስን እያለ ትውልዱ እስከ ቴክታና በጥሪቃ ይወርዳል:: ቴክታና በጥሪቃም ልጅ በማጣት ኖረው: የእንቦሳዎች: የፀሐይና: የጨረቃን ምሥጢር ተመልክተው ሄኤሜንን ይወልዳሉ::
*ሄኤሜን ዴርዴን: ዴርዴ ቶናሕን: ቶናሕ ሲካርን: ሲካርም ሔርሜላን ይወልዳሉ::
*ሔርሜላም ከክርስቶስ ልደት 90 ዓመታት በፊት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል ደግ ሰው ከካህናት ወገን አግብታ በስርዓተ ኦሪት ትኖር ነበር:: እግዚአብሔር ለዚህች ደግ ሴት የተባረኩ 3 ሴቶች ልጆችን ሰጣት::
+የመጀመሪያዋን "ማርያም" አለቻት:: ይህቺውም የአረጋዊው ዮሴፍ ሚስትና የቅድስት ሰሎሜ ቡርክት እናት ናት:: ሁለተኛዋን "ሶፍያ" አለቻት:: እርሷም ቅድስት ኤልሳቤጥን (የመጥምቁን እናት) ወልዳለች::
+በመጨረሻ የወለዷትን ግን "ሐና" አሏት:: ይህቺውም የፈጣሪ የሥጋ አያቱ: የድንግል ማርያምም እናቷ ትሆን ዘንድ የተመረጠችውና ስም አጠራሯ የከበረው: ዛሬ የምናከብራት እናት ናት::
+መጽሐፈ ስንክሳርን ስመለከት እንዲህ የሚል ዓረፍተ ነገር አየሁ:: "ለዛቲ ቅድስት ኢያዕመርነ ገድላቲሃ ዘትገብሮን በኅቡዕ ከመ ንዝክሮን" ይላል:: ትርጉሙም "የዚህቺን ቅድስት ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳንዘረዝር አላወቅነውም" እንደ ማለት ነው::
+የሚገርመው አበው እንዲህ ያሉት ክብሯን መግለጹን አልጠግብ ብለው ነው:: እኛም በመጠናችን የብጽዕት ሐናን ሕይወት በአጭሩ ቀጥለን እንመልከት::
+ብጽዕት ሐና ወላጆቿ (ማጣትና ሔርሜላ) ከካህናት ወገን በመሆናቸው ልጆቻቸውን በጥንቃቄ: በሥርዓተ ኦሪት እንዳሳደጉ ይታመናል:: ቅድስት ሐናንም ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ በሕጉ: በሥርዓቱ አሳድገዋታል::
+በወቅቱ በፈቃደ እግዚአብሔር ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ የሚሆን አንድ ደግ ሰው አጩላት:: ይህ ሰው "ኢያቄም" ይባላል:: አንዳንዴም "ሳዶቅ" ወይም "ዮናኪር" እየተባለ ይጠራል:: ቅዱስ ኢያቄም ማለት ክፉ ከአንደበቱ የማይወጣው: ምጽዋትን የሚወድ: አምላከ እሥራኤልን በንጹሕ ልቡ የሚያመልክ ሰው ነበረ::
+እንደ ኦሪቱ ሥርዓት 2ቱ (ኢያቄም ወሐና) ከተጋቡ በሁዋላ ቶሎ መውለድ አልቻሉም:: ይሕ ደግሞ የወቅቱ ከባድ ፈተና ነው:: በዘመድ የከበሩ: በጠባያቸው የተመሰገኑ: መልካምንም የሚሠሩ ሰዎች ልጅ ስለሌላቸው ብቻ "ኅጡአነ በረከት" እየተባሉ ከቤተ እግዚአብሔር ይገፉ: በአደባባይም ይነቀፉ ነበር::
+ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ልጅ አለመውለድ እንደ ኃጢአተኛ ያስቆጥር ነበር:: ደግነቱ የወቅቱ ሊቀ ካህናት ቅዱስ ዘካርያስ (የመጥምቁ አባት) እንደ እነሱ ልጅ ያጣ በመሆኑ አብረው ይጽናኑ ነበር::
+የሆነው ሆኖ እኒህ ቡሩካን ሰዎች አምላከ እሥራኤልን ከመለመንና ከማመስገን በቀር ሌላ ትርፍ አልተገኘባቸውም:: ምንም የሞላቸውና የደላቸው ባይሆኑም ደሃን ሳያጐርሱ አይበሉም ነበር::
+ቅድስት ሐናን ግን "ቢወልዷት እንጂ አትወልድ: ድንጋይ: በቅሎ" እያሉ ጐረቤቶቿ ይሳለቁባት ነበር:: ከማልቀስ በቀር ደግሞ መልስ አልነበራትም::
+አንድ ቀን ግን ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ተመልክታ "ፈጣሪ ሆይ! የእንስሳትን ማሕጸን የምትከፍት: ዕፀዋትንም ከባሕርያቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ:: እውነትም ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ስትል አለቀሰች::
+ቅዱስ ኢያቄምም ወደ ተራራ ወጥቶ ለ40 ቀናት አለቀሰ: ተማለለ:: ይህ ሲሆን 2ቱም አርጅተው ነበር:: ሐምሌ 30 ቀን ግን ነጭ ርግብ 7ቱን ሰማያት ሰንጥቃ በማሕጸነ ሐና ስታድር አዩ:: ደስ ብሏቸው ለ7 ቀናት ሱባኤ ይዘው ቅድስት ሐና እመቤታችንን ነሐሴ 7 ቀን ጸነሰቻት::
+ይሕም ለእነርሱም: ለወገኖቻቸውም ታላቅ ተድላ ሆነ:: ብጽዕት ሐና ግን ፈጣሪዋን ታከብረው ዘንድ በጐነትንና ንጽሕናን አበዛች:: ጸንሳ ሳለም ዕውራንን አበራች: ድውያንን ፈወሰች::
+የጦሊቅ ልጅ በሞተ ጊዜም እያለቀሰች ስትዞረው ጥላዋ ቢያርፍበት አፈፍ ብሎ ተነስቶ:- "ሰላም ለኪ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ" ብሎ ድንግል ማርያምን::
"ወሰላም ለኪ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ" ብሎ ቅድስት ሐናን አመስግኗል:: ትርጉሙም ድንግልን "የፀሐየ ጽድቅ እናቱ": ሐናን "ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አያቱ" ማለት ነው::
+ይህንን ያዩ አይሁድ ቅድስት ሐናን ሊገድሉ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል:: ግን መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አልፈቀደላቸውም:: ግንቦት 1 ቀንም የሰማይና የምድር ንግስትን ሊባኖስ ተራራ ላይ ወልዳ ሽሙጥን ከሁላችንም አራቀች::
+ስሟን "ማርያም-የአምላክ ስጦታ" ብለው ሰይመው ለ3 ዓመታት አሳድገዋታል:: የሚገርመው በ3ቱ ዓመታት ውስጥ ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከክንዷ አውርዳት አታውቅም ነበር:: አንድ ጊዜም መላእክት ወስደውባት ፍጹም አልቅሳለች:: ሁዋላ ግን መልሰውላታል::
+ሌላኛው የሚደንቀው እግዚአብሔር የዓለም ውዱን ስጦታ እመ ብርሃንን ሰጣቸው:: እነርሱም ይሕችን ውድ ስጦታ ሳይሰስቱ ለፈጣሪ መለሱለት::
"እምቅድሜክሙ አልቦ::
ወእምድኅሬክሙ አልቦ::
ከመዝ መስዋዕት ለእግዚአብሔር ዘወሃቦ::" እንዲል::
+ቅድስት ሐና ድንግል ወደ ቤተ መቅደስ ከገባች በሁዋላ የእናትነት ፍቅሯ እያገበራት ለ5 ዓመታት እየተመላለሰች ትጐበኛት: ትስማት ነበር:: እመቤታችን 8 ዓመት በሞላት ጊዜ ግን የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ቅድስት ሐና ደረሰ::
+ከክርስቶስ ልደት 8 ዓመታት አስቀድማ ብጽዕት እናት ሐና በዚህች ቀን ዐረፈች:: ትንሽ ቆይቶም ባለቤቷ ቅዱስ ኢያቄም ተከተላት እኛም ልጆቿ "ብጽዕት ሐና ብጽዓን ይገባሻል!" እያልን እናመስግናት::
+ሊቃውንቱ ለእርሷ እንዲህ ብለዋልና:-
"ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኩሉ ምዕራጋ::
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ::
ሐና ብጽዕት ተፈስሒ እንበለ ንትጋ::
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ::
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ::" (አርኬ)
=>አምላከ ብጽዕት ሐና በምልጃዋ ከዘለዓለም እሳት ያድነን:: ጸጋ በረከቷንም ይክፈለን::

=>ኅዳር 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ሐና ቡርክት
2.ቅዱስ አርኬላዎስ ሰማዕት
3.አባ ኤልሳዕ አበ ምኔት
4.አባ ዻኩሚስ መነኮስ
5.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
6.ቅድስት አውራንያ (የሰማዕቱ እናት)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
=>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጥዋም ሰው ተወለደ:: እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethellettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment