ኦሪት ዘፍጥረት ¹¹፥¹–⁹።
«¹፤ምድርም፡ ዅሉ፡ ባንድ፡ ቋንቋና፡ ባንድ፡ ንግግር፡ ነበረች።
²፤ከምሥራቅም፡ ተነሥተው፡ በኼዱ፡ ጊዜ፡ በሰናዖር፡ ምድር፡ አንድ፡ ሜዳ፡ አገኙ፤ በዚያም፡ ተቀመጡ።
³፤ርስ፡ በርሳቸውም፦ ኑ፥ ጡብ፡ እንሥራ፥ በእሳትም፡ እንተኵሰው፡ ተባባሉ። ጡቡም፡ እንደ፡ ድንጋይ፡ ኾነላቸው፤ የምድርም፡ ዝፍት፡ እንደ፡ ጭቃ፡ ኾነችላቸው።
⁴፤እንዲህም፦ ኑ፡ ለእኛ፡ ከተማና፡ ራሱ፡ ወደ፡ ሰማይ፡ የሚደርስ፡ ግንብ፡ እንሥራ፤ በምድር፡ ላይ፡ ሳንበተንም፡ ስማችንን፡ እናስጠራው፡ አሉ።
⁵፤እግዚአብሔርም፡ የአዳም፡ ልጆች፡ የሠሩትን፡ ከተማና፡ ግንብ፡ ለማየት፡ ወረደ።
⁶፤እግዚአብሔርም፡ አለ፦ እንሆ፥ እነርሱ፡ አንድ፡ ወገን፡ ናቸው፥ ለዅሉም፡ አንድ፡ ቋንቋ፡ አላቸው፤ ይህንም፡ ለማድረግ፡ ዠመሩ፤ አኹንም፡ ያሰቡትን፡ ዅሉ፡ ለመሥራት፡ አይከለከሉም።
⁷፤ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ፡ የአንዱን፡ ነገር፡ እንዳይሰማው፡ ቋንቋቸውን፡ በዚያ፡ እንደባልቀው።
⁸፤እግዚአብሔርም፡ ከዚያ፡ በምድር፡ ዅሉ፡ ላይ፡ በተናቸው፤ ከተማዪቱንም፡ መሥራት፡ ተዉ።
⁹፤ስለዚህም፡ ስሟ፡ ባቢሎን፡ ተባለ፥ እግዚአብሔር፡ በዚያ፡ የምድርን፡ ቋንቋ፡ ዅሉ፡ ደባልቋልና፤ ከዚ ያም፡ እግዚአብሔር፡ በምድር፡ ዅሉ፡ ላይ፡ እነርሱን፡ በትኗቸዋል።»
የአባቶቻችን ሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች እንኳን አጋዕዝተዓለም ቅድስት ሥላሴ ጠላቶቻቸውን ለመበቀል የሰናዖርንም ግንብ ለናዱበትና ባቢሎንን ላደበላለቁበትና ፤ የማትመረመር አንድነት ሦስትነታቸውንም በግልጽ ላስተማሩባት የጥር ፯ አመታዊ ክብረ ታላቅ ክብረ በዓል ቀን እንኳን አደረሳችሁ ! አደረሰን !
ዛሬም የኢትዮጵያንና የተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጠላቶች በፍርዱ ተመልክቶ ቋንቋቸውን ያደበላልቅልን ! አሜን !
Comments
Post a Comment