††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ አልዓዛር ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አልዓዛር ሐዋርያ †††
††† ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::
በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: (ዮሐ. 11:3) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ::
ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: (ዮሐ. 12:1) በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::
ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ በዚሕች ቀን አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: (ዮሐ .11)
††† ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣልና ከበረከቱ ይክፈለን:: (ይቆየን)
††† መጋቢት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ቴዎቅሪጦስ አናጉንስጢስ (ሰማዕት)
3.ቅዱስ ተላስስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሴፍ ኤዺስ ቆዾስ
5.ቅዱስ ጊዮርጊስ መስተጋድል
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
4.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
5.አባ ገሪማ ዘመደራ
6.አባ ዸላሞን ፈላሢ
7.አባ ለትጹን የዋህ
††† "ጌታ ኢየሱስም:- 'ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ:: የሚያምንብኝ ቢሞት እንኩዋ ሕያው ይሆናል:: የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም:: ይህን ታምኛለሽን?' አላት:: እርስዋም (ማርታ):- 'አዎን ጌታ ሆይ: አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ::' አለችው::"†††
(ዮሐ. 11:25-27)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━⊱✿⊰━━
Comments
Post a Comment