††† እንኳን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የተድላና የደስታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† በዚሕች ቀን ለ40 ዓመታት በመላው ዓለም የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት የተከፈቱበት ቀን ይታሠባል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ:-
¤አበው ተስፋ ሲያደርጓት
¤ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት
¤ሱባኤ ሲቆጥሩላት
¤ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል::
††† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :-
¤በመጸነሱ ተጸንሳ
¤በመወለዱ ተወልዳ
¤በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ
¤በጥምቀቱ ተጠምቃ
¤በትምሕርቱ ጸንታ
¤በደሙ ተቀድሳ
¤በትንሣኤው ከብራ
¤በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ
¤በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች::
††† አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በመላው ዓለም ዞረው በብዙ ድካም የሠሯት ቤተ ክርስቲያን ለ200 ዓመታት እጅግ የበዙ መከራዋችን አሳልፋለች:: በ265 ዓ/ም የመጣባት መከራ ግን በዓለም ታሪክ እስካሁን አልታየም:: የወቅቱ ኃያላን ነገሥታት (ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስ) ዓለምን ለ2 ተካፍለው ክርስቲያኖችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ::
በመጀመሪያም በዓለም ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ካልሆነም እንዲዘጉ : በፈንታቸው ደግሞ አዽሎን: አርዳሚስ የተባሉ ጣዖቶች እንዲተኩ ትዕዛዝ ተሰጠ:: ለ40 ዓመታት ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ሚሊየኖች ተገደሉ: ታሰሩ: ተሰቃዩ: ተሰደዱ:: መጻሕፍት ተቃጠሉ: አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ወደሙ::
በአባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ ልንናገረው ከምንችለው በላይ ጭንቅና መከራ ደረሰ:: ነገር ግን ቅዱሳኑ ያን ሁሉ ችለው ጸኑ:: 47 ሚሊየን የሚያሕሉትን ደግሞ ሰይፍና እሳት በላቸው:: በዛ ዘመን አንድ ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት ከአሕጉር አሕጉር መሔድን ይጠይቅ ነበር::
ከዚሕ ሁሉ በኋላ ግን እግዚአብሔር "ግፍ ይበቃል" ሲል በ305 ዓ/ም ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: መክስምያኖስን በጦርነት ሲማርከው አውሬው ዲዮቅልጢያኖስ ግን አብዶ ሞተ:: ይህ ከተደረገ ከዓመታት በኋላ (በ313 ዓ/ም) ታላቁ ቆስጠንጢኖስ የዓለም መሪዎችን በዚሕች ቀን ጠርቶ አዋጁን በአዋጅ ሻረው:: "ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ:: በፈንታው ደግሞ ሁሉም ጣዖት ቤቶች ይዘጉ" አለ::
በሺሕ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን በወርቅ አስለበጠ:: በዚሕ ምክንያት ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን "ዕለተ ትፍሥሕት (የደስታ ቀን)" ተብላ ትከበራለች::
††† ቸሩ አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ይሠውርልን:: ከበረከቷም ያድለን:: ትውልዱ ደካሞች ነንና ከማንችለው ፈተናም ይጠብቀን::
††† ሰኔ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
2.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት (ከታላላቆቹ ሶፍያዎች አንዷ ናት)
4.ቅዱሳት ሰማዕታት ደባሞንና ብስጣሞን (የቅድስት ሶፍያ ልጆች)
5.ቅዱስ አውሎጊስ ሰማዕት
6.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
††† "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ:: ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ:: ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . .
ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ:: ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ::" †††
(መዝ. 121:1-9)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment