†✝† እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ድሜጥሮስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†
†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†
†✝† ቅዱስ ድሜጥሮስ ድንግል †✝†
††† ቅዱስ ድሜጥሮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ: በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ ደግ ሰው ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ያለቁበት በመሆኑ ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን እንዲያገባ ግድ አሉት::
ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ48 ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና ልብስ እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል::
ቅዱስ ሚካኤልም ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ ክንፉን ለርሱ : ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር:: ከ48 ዓመታት በሁዋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ የግብፅ 12ኛ ሊቀ ዻዻስ ሆኖ ተሹሞ: ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል::
ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን ሚስት አለው በሚል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከት በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ ትእዛዝ ሕዝቡን ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ ወይን ጋር እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::
ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና ተረድተው: "ማረን" ብለው በፍቅር የተለያዩት በዚሕ ዕለት ነው::
ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ ዘመናቸውን በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ ድሜጥሮስ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ (Origen) ና ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (Clement of Alexandria) የመሰሉ መናፍቃንንም አውግዟል::
ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን እየተሰበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም ይባርካቸው ነበር:: ቅዱሱ በ107 ዓመቱ ያረፈው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው::
††† አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ያሳድርብን:: ጸጋ በረከቱን ደግሞ ያትረፍርፍልን::
††† መጋቢት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት (ደንግልናው የተገለጠበት)
2.ቅድስት ልዕልተ ወይን
3.ቅዱስ መላዚ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት (ጠንቁዋዩን በለዓምን የገሰጸበትና አህያዋን እንድትናገር ያደረገበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
††† "ሥጋዊ ፈቃዳቸውን የሚሠሩ ሁሉ እነርሱ በላይኛው ዓለም የሞቱ ናቸው:: ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን ፈቃድ ድል ከነሳችሁት ለዘለዓለም በሕይትኖራላችሁ:: የእግዚአብሔር መንፈስ የሚወደውን ሥራ የሚሠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው::" †††
(ሮሜ. 8:13)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment