✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ የካቲት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+" ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ "+
+እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ ቢሉም)
+ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ዽዽስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::
+ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በሁዋላ ሙሉ የጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::
+ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::
+እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን (ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ 64 64 ጊዜ ያመሰግናት ነበር::
+በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 / 325 ዓ/ም 318ቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::
+ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይህማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቁዋንቁዋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል::
+በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጉዋል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በሁዋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውሃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::
+አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::
+ውዳሴዋን በ7 ቀናት ከደረሰላት በሁዋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምስጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምስጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ 14 ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::
+እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
+በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በ67 ዓመቱ በ365 / 373 ዓ/ም ዐርፎ ተቀብሯል::
+ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:-
1.ቅዱስ ኤፍሬም
2.ማሪ ኤፍሬም
3.አፈ በረከት ኤፍሬም
4.ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
6.አበ ምዕመናን ኤፍሬም
7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::
❖የካቲት ፫ ቀን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የፍልሠት በዓሉ ነው፡፡
✞ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
+" አባ ያዕቆብ ገዳማዊ "+
+ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት "ለስሒት መኑ ይሌብዋ- ስሕተትን ማን ያስተውላታል" (መዝ) ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ታላቅ ቅዱስ ሰው በኃጢአት ብዙ ተፈተነ:: ወደ በርሃ ወጥቶ: በምናኔ ጸንቶ: በጾምና በጸሎት ተግቶ ዘመናትን ስላሳለፈ ሰይጣንን አሳፈረው::
+ግን ደግሞ ክፉ ጠላት ባልጠረጠረው መንገድ መጥቶ መከራ ውስጥ ከተተው:: የአገረ ገዢው ልጅ ታማ "ፈውሳት" አሉት: ፈወሳት:: ወደ ቤቷ ስትመለስ ግን አመማት:: "ከአንተ ጋር ትቆይ" ብለው ትተዋት ቢሔዱ ከመለማመድ የተነሳ በዝሙት ወደቀ::
+እንዳይገለጥበት ስለ ፈራም ገደላት:: በሆነው ነገር ተስፋ ቆርጦ ወደ ዓለም ሲመለስ: ቸር ፈጣሪ የሚናዝዝ አባትን ልኮ ንስሃ ሰጠው:: ጉድጓድ ምሶ: ድንጋይ ተንተርሶ ለ30 ዓመታት አለቀሰ:: እግዚአብሔርም ምሮት: የቀደመ ጸጋውን ቢመልስለት: ዝናምን አዝንሞ ሕዝቡን ከእልቂት ታድጓል:: በዚህች ዕለት ዐርፎም ለርስቱ በቅቷል::
+" ታላቁ አባ ዕብሎይ "+
+ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት 'ርዕሰ ገዳማውያን' ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ ነው::
✞የካቲት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት-በዓለ ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ (ሕይወቱ መላዕክትን የመሰለ ግብፃዊ አባት)
3.አባ ያዕቆብ መስተጋድል
=>ወርኀዊ በዓላት
1,በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
2,ቅዱሳን እያቄም ወሐና
3,ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን
4,አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5,አቡነ ዜና ማርቆስ
6,አቡነ መድኃኒነ እግዚእ
7,ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሐይማኖት
++"+ ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል:: +"+ (ማቴ. 7:7)
++"+ የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 37:30)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment