Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ኀዳር ፳፰


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ሊቃኖስ ወአባ ሰረባሞን ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

" ኅዳር 28 "

+*" አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል "*+

=>ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ሊቃኖስ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

+ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው::

+አባ ሊቃኖስን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

+በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

+በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

+ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች::
አባ ሊቃኖስና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያሥራቸው
ቋንቋን መማር ነበር::

+ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ
ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ
መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ሊቃኖስ እንደ ገና አቀጣጠሉት::

+ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት::የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

+ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን
ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ሊቃኖስ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማኅበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

+የነ አባ ሊቃኖስ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ
መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::

*ዸንጠሌዎን በጾማዕት:
*ገሪማ በመደራ:
*አረጋዊ በዳሞ
*ጽሕማ በጸድያ
*አባ ይምዓታ በገርዓልታ
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::

+ልክ እንደ ባልንጀሮቻቸው 8ቱ ቅዱሳን አባ ሊቃኖስም ከጻድቅነታቸው ባሻገር ለሃገራችን ትልቅ ባለውለታ ናቸው::በነገራችን ላይ 'አባ ሊቃኖስ' የመጀመሪያ ስማቸው ሳይሆን
በትምሕርታቸው (በእውቀታቸው) የተደመመ የአክሱም ሕዝብ ያወጣላቸው ስም ነው::

+ሊቃኖስን 'ሊቁ አባት' ማለት ነው ብለው የተረጐሙልን አበው አሉና:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- 9ኙ ቅዱሳን
የማኅበር አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደየ ራሳቸው ገዳማት ሲሔዱ አባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ እዚያው
አክሱም አካባቢ በመቅረታቸው ይሏል::

+ምክንያቱም ሕዝቡና ንጉሡ 2ቱን አበው "አትራቁን" ብለው ለምነዋቸው ነበርና:: በዚህም የተነሳ አባ ዸንጠሌዎን ከአክሱም ከተማ በላይ ባለች ጾማዕት (እንዳባ ዸንጠሌዎን) በሚሏት ተራራ ላይ ሲያርፉ: አባ ሊቃኖስ ደግሞ ከዚያው
ከጾማዕት 1 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ደብረ ቆናጽል (የቀበሮዎችተራራ) ላይ ዐርፈዋል::

+በመካከላቸው ደግሞ የቅድስት ማርያም መግደላዊት ቤተ ክርስቲያን ይገኛል:: አባ ሊቃኖስ በአታቸውን ካደራጁና ገዳም ካነጹ በኋላ ደቀ መዛሙርትን አፈሩ: አስተማሩ::

+እጅግ ከበዛው ተጋድሏቸው ባልተናነሰ መንገድ ለ21 ዓመታት ያህል ከተራራው እየተነሱ ወንጌልን ሰብከዋል::
መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች መጻሕፍትንም ከሱርስት (የሶርያ ልሳን) እና ከጽርዕ (የግሪክ ልሳን) ተርጉመዋል::

+ሁልጊዜም ለአገልግሎት ሲወጡ በትረ ሙሴአቸውን አይለዩም ነበር:: ሲሰብኩም: ሲጸልዩም ተደግፈውባት
ነበር:: ታዲያ ከዘመን ብዛት የእጃቸው መዳፍ መነደሉን አበው:-"ወበእሒዘ በትር ዘተሰቁረ ዕዱ" ሲሉ ይናገራሉ::

+ዳግመኛ ማታ ማታ ለጸሎት እጆቻቸውን ሲያነሱ እንደ ፋና ቦግ ብለው ሲያበሩ ይታዩ ነበር:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ
ሥሙር በሆነ ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን
በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድም ሞገስን አግኝተዋል:: ዛሬም ድረስ የአክሱም
ሕዝብ ከልቡ ያከብራቸዋል::

+አንድ ወቅትም ሳይገባን (በቸርነቱ) ሒደን ገዳማቸውን ተመልከተናል:: አበው እንደሚሉት በደብረ ቆናጽል ላይ
ያለው ደን የብዙ ሥውራን መኖሪያ ነው:: ለ1,500 ዓመታት ተከብሮ ቢኖርም በ1928ቱ የጣልያን ወረራ ግን እንዳልነበረ ሆኖ ነበር::

+ዛሬም በቀድሞ ገጽታው አይደለም:: በገዳሙም ያገኘነው አንድ አባትን ነው::

+ዐይናችን ግን ብዙ ነገሮችን ተመልክቶ አድንቋል:: እንደ ሰማነውም ዛሬም መካነ ቅዱሳን በመሆኑ የጽዮን አገልጋዮችም ማረፊያ ነው:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ያረፉት ሕዳር 28 ቀን ነው::

+" ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት "+

+ቅዱሱ ሰው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ሲሆን የቅዱሳን ሐዋርያት ዘመድ ነው:: እርሱ ተወልዶ ያደገው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢየሩሳሌም ነው:: የዘር ሐረጉ ሲቆጠርም በቀጥታ ከሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስና ከስምዖን ቀለዮዻ
ይደርሳል::

+በልጅነቱ ያደገው በሥርዓተ ኦሪት ነው:: ወጣት በሆነ ጊዜ ግን ፈጣሪ በሰጠው ሕሊና ተመራምሮ በክርስትና ለመኖር ወሰነ:: የወቅቱን የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሒዶ "አጥምቀኝ" ቢለው "ልጄ! ደስ ይለኝ ነበር:: ግን ወገኖችህ አይሁድ
ይገድሉኛል" ሲል መለሰለት::

+አክሎም "ወደ ግብጽ ሒደህ ግን ብትመጠመቅ የተሻለ ነው" ስላለው ከኢየሩሳሌም ግብጽ ገባ:: ግብጽ ደርሶ:
ከቅዱስ ቴዎናስ (16ኛ ፓትርያርክ) ክርስትናን ተምሮ ተጠመቀ::ቀጥሎም ወደ ገዳም ገብቶ ከመጀመሪያዎቹ
መነኮሳት አንዱ ሆነ:: ምናኔን ከአባ እንጦንስ ተምሮ ስም አጠራሩ ከፍ አለ::

+በተጋድሎውና በንጽሕናው ስለ ወደዱትም የኒቅዮስ ዻዻስ አደረጉት:: በዘመነ ሲመቱም ጣዖት አምልኮን
ከአካባቢው አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በዲዮቅልጢያኖስ ተይዞ በዚህች ቀን
ተገድሏል:: ሲገደልም ልክ እንደ ቅድመ አያቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፊቱ ያበራ ነበር::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን መዓዛ ቅድስናቸውን ያሳድርብን::ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ ሊቃኖስ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው /አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ/
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

++"+ ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::አንደበቱም ፍርድን
ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ
ነው::በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:29)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!። 

  "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethe
llettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments