Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ታሕሳስ ፲፫


✝✞✝ እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን "አቡነ ዘርዓ ቡሩክ" : "አባ መቃርስ" እና "አባ አብራኮስ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

+*" አቡነ ዘርዓ ቡሩክ "*+

=>ሃገራችን ኢትዮዽያ:-
*ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት
*በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች
*የቅዱሳን መጠጊያ እና
*ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች::

+ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል:: በምሥራቅም: በምዕራብም: በሰሜንም: በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው:: ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው::

+በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው:: አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው:: ለመጥቀስ ያህል እንኩዋ:-

1.በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ 2ቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው: ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል:: (በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው)

2.ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል:: ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል::

3.መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል:: ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ5 ዓመት አቁመዋል::

4.ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት 12 ክንፍ (መንፈሳዊ ክንፍ) ተሰጥቷቸው ነበር:: ከዚህ በተረፈም በጾም: በጸሎት: በትርምትና በስብከተ ወንጌል ፍጹም ጽሙድ ነበሩ::

+ጻድቁ የተወለዱት በ16ኛው መቶ ክ/ዘ እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ: እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ:: ወላጆች በልጅ እጦት ተማለው ይህን የተቀደሰ ፍሬ አገኙ:: "ጸጋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋልና::

+ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው:: በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል:: ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጉዋቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል::

+ነገሩ እንዲህ ነው:: በ1598 ዓ/ም በኢትዮዽያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ዼጥሮስ (ፔድሮ) ፓኤዝ  ከሚባል ፈረንጅ መናፍቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ:: ካቶሊክ (ሮማዊ)ም ሆኑ::

+በሁዋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮዽያ ሕዝብ መናፍቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ:: ለጊዜው በቤተ መንግስቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ:: እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ::

+በተለይ በ1611 በተዋሕዶ አማኞችና በመናፍቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ዻዻሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ:: በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው: ሴቷ ከማዕድ ቤት: ካህኑ ከመቅደሱ: ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ::

+በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ:: በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ:: ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት::

+ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ:: በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ዼጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው:: ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ:: በጨለማ እስር ቤትም 5 ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር::

+እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም:: ከ5 ዓመት በሁዋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል:: ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል::

+እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል:: ሃይማኖት ተመልሷል:: ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል::

+ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል:: በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር 13 ቀን ዐርፈዋል::
<< ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ !! >>

+"+ አባ መቃርስ ገዳማዊ +"+

=>"መቃርስ" የሚለው ቃል በዮናኒ ልሳን "ብጹዕ" እንደ ማለት ሲሆን የመነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን በስሙ ተጠርተውበታል:: በነገረ ቅዱሳን ታዋቂ ከሆኑት አንዱና ተጠቃሹ ዛሬ የምናከብረው አባት ሲሆን ብዙ ጊዜ "ዘይሴሰይ ቆቅሃ - ቆቅን የሚበላው" እየተባለ ይጠራል::

+የዚህንም ምክንያቱን እንመለከታለን:: ቅዱስ መቃርስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው:: ከእሱ በፊት ታላቁ መቃርስ: መቃርስ ቀሲስና መቃርስ ዘቃው የተባሉ አባቶች ስለ ነበሩ እርሱን 4ኛው መቃርስ እያሉ መጥራት የተለመደ ነው::

+በወጣትነቱ ከዓለም ወጥቶ ገዳም ገባ:: ቀጥሎም መነኮሰ:: ግን ግን ወሬን: ሐሜትንና ትዕቢትን ፈጽሞ ይጠላ ነበርና: ከገዳሙ ወጥቶ ሰው ወደማይኖርበት በርሃ ሔደ::

+ግን በአካባቢው የሚበላ ነገር: ከዛፍ ፍሬ: ከሣር ዘርም እንኩዋ ምንም ነገርን ማግኘት አልቻለም:: ጾሞ በራበው ጊዜም "ፍጥረትን የምትመግብ ጌታ ሆይ! ራቴን አብላኝ?" ሲል ጸለየ::

+እግዚአብሔርም አንዲት ቆቅን አምጥቶለት በላ:: ከዚህ በሁዋላም ምግቡ ቆቅ ብቻ ሆነ:: ማታ ማታ 1 ቆቅ ይያዝለታል:: እርሱም አመስግኖ እየበላ ዘመናት አለፉ::

+እግዚአብሔር የዚህ ገዳማዊ ዜና እንዲገለጥ ስለ ፈለገ አንድ የቁስጥንጥንያ መነኮስ ከሃገሩ ተነስቶ ወደ በርሃ ወረደ:: መጠለያ በዓት ሲፈልግም አንድ አረጋዊ ባሕታዊ ቆቅ ሲያጠምድ ተመልክቶ ደነገጠ::

+"መነኮስ ሆኖ እንዴት ሥጋ ይበላል" ሲልም ተናደደ:: ነገሩን ለሊቀ ዻዻሳቱ ይነግር ዘንድም በመጣበት መንገድ እየቸኮለ ተመለሰ:: የሃገሩን ፓትርያርክም "አባታችን አንድ ባሕታዊ እምነታችን ሊያሰድብ እንዲህ አደረገኮ" ቢለው ነገሩ እርግጥ ይሆን ዘንድ ፓትርያርኩ አንድ ሰው ጨምሮ 2ቱን ላካቸው::

+በዚያች ቀንም ቅዱስ መቃርስ ለመጀመሪያ ጊዜ 3 ቆቆች ገቡለት:: "ጌታየ! 2ቱን ምን ላድርጋቸው?" ሲል መነኮሳቱ ወደ እርሱ ደረሱ:: ደስ ብሎት ፈጣሪን እያመሰገነ ሠርቶ አቀረበላቸው::

+እነርሱ ግን ቅዱሱን ናቁት:: "አንበላም" አሉት:: አባ መቃርስም የተጠበሱት ቆቆች እፍ እፍ እያለ ነፍስ ዘራባቸውና እንዲበሩ አደረገ:: በዚህ የደነገጡት መነኮሳቱ ሰግደውለት እየተሯሯጡ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ::

+ባሙበት አፋቸው "ታላቅ ሰው ተገኝቷል: በረከቱ አይለፋችሁ" ሲሉ ሰበኩ:: ይህ ሲሰማም ፓትርያርኩ ከነ ሕዝቡ: ንጉሡ ከነ ሠራዊቱ ሊባረኩ ወደ በርሃው ወረዱ:: ግን ቅዱስ መልአክ ተሸክሞት ወደ ብሔረ ሕያዋን ሲያርግ ደረሱ::

+እየጮሁ "አባ በረከትህን: የድህነት ቃልህን?" አሉት:: እርሱም "ይጹም አፉክሙ እምነገረ ውዴት ወሐሜት - አፋችሁ ከሐሜት: ከነገር ሥራት ይጹም:: ካህናት ትምሕርት: መነኮሳት ትሕርምትን አታብዙ:: ልቡናችሁ አይታበይ:: ሰላም ለእናንተ ይሁን!" ብሏቸው ከዐይናቸው ተሰወረ:: ወደ ብሔረ ሕያዋንም ገባ::

+"+ አባ አብራኮስ ገዳማዊ +"+

=>አባቶቻችን ይህንን ቅዱስ "ኃያል መነኮስ" ይሉታል:: በ20 ዓመቱ ወደ በርሃ ገብቶ ለ70 ዓመታት በበርሃ ሲጋደል 90 ዓመት ሞልቶታል:: ሰይጣንን መፈናፈኛ አሳጥቶ ከአካባቢው አርቆታል::+ሰይጣንም እርሱን መጣል ስላልቻለ ቢያንስ ከጾሙ: ጸሎቱና ስግደቱ ትንሽ ቢቀንስልኝ ብሎ አዲስ የፈተና ስልትን ፈጠረ:: ቀርቦም በገሃድ "አብራኮስ አንተ ደክመሃል:: ግንኮ ገና 50 ዓመት እድሜ አለህ" አለው::

+ቅዱሱ ግን ሰይጣንን "አሳዘንከኝ! እኔኮ ገና 100 ዓመት ያለኝ መስሎኝ ነው በጥቂቱ የምጋደለው:: እንዲያ ከሆነማ ከነበረኝ ጾም: ጸሎትና ስግደት በእጥፉ እጨምራለሁ" ቢለው ሰይጣን አፍሮ ተመልሷል:: ቅዱስ አብራኮስ ግን በዚያው ዘመን: በ90 ዓመቱ ዐርፏል::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ታሕሳስ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መቃርስ ገዳማዊ
2.አባ አብራኮስ ገዳማዊ
3.ብጽዕት ሐና (የእመቤታችን እናት)
4.አባ በጽንፍርዮስ ሰማዕት
5.አባ ሚካኤል ዘቀልሞን

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
4.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት
5.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
6."13ቱ" ግኁሳን አበው

=>+"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41)

    ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
        ✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
    ✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!። 

  "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn
Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments