✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱስ ፃና ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+"+ ቅዱስ ፃና +"+
=>በቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን አሉ:: ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ፃና:-
*በዘመነ ሰማዕታት የነበረ:
*ቅዱስ ኤስድሮስ የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው:
*ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ::
+በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር::
+በመከራ ዘመን (ዘመነ-ሰማዕታት) ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል:: አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::
+ሰማዕቱ ቅዱስ ፃና ባልንጀራው ኤስድሮስ ከተገደለ በሁዋላ ለ36 ቀናት በጨለማ እሥር ቤት ውስጥ ከብዙ ስቃይ ጋር ቆይቷል:: መከራን ቢያፀኑበትም በሃይማኖቱ ጽኑ ነበርና እርሱንም በዚሕች ቀን ገድለውታል::
+ደግ እናቱ በቦታው ነበረችና መላዕክት በክብር ነፍሱን ሲያሳርጉ ተመልክታለች::
=>ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን::
=>ሚያዝያ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ፃና ሰማዕት
2.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት
3.አባ ይድራ
4.የደብረ ሲና ቅዳሴ ቤት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
=>+"+ ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ: አሸንፋችሁአቸውማል:: በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና:: እነርሱ ከዓለም ናቸው:: ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ:: ዓለሙም ይሰማቸዋል:: እኛ ከእግዚአብሔር ነን:: እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል:: ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም:: +"+ (1ዮሐ. 4:4)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Comments
Post a Comment