✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ጥቅምት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
✞✞✞ እግዝእትነ ማርያም ✞✞✞
+እመቤታችን ድንግል ማርያም የወልደ እግዚአብሔር እናቱ ናትና ሁሉን ትችላለች:: እርሱን ከሃሊ (ሁሉን ቻይ)
ካልን እርሷን "ከሃሊት" ልንላት ይገባል:: ልክ ልጇ ሁሉን ማድረግ ሲችል በትእግስት ዝም እንደሚለው እመ
ብርሃንም ስንት ነገር እየተደረገ: በእርሷ ላይም አንዳንዶቹ ስንት ነገርን ሲናገሩ እንደማትሰማ ዝም ትላለች::
+እኛ ኃጥአን ንስሃ እስክንገባ ድረስም "ልጄ! የዛሬን ታገሣቸው?" እያለች ትለምንልናለች:: ቸሩ ልጇም ሊምረን እንጂ ሊያጠፋን አይሻምና "እሺ እናቴ!" እያለ ይኼው በዚህ ሁሉ ክፋታችን እስከ ዛሬ ድረስ አላጠፋንም::
*ቸር ነው
*መሐሪ ነው
*ይቅር ባይ ነው
*ታጋሽ ነው
*ርሕሩሕ ነው
*ቂምም የለውም:: በንስሃ ካልተመለስን ግን አንድ ቀን መፍረዱ አይቀርምና ወገኖቼ ንስሃ እንግባ: ወደ እርሱም እንቅረብ::
+ይህቺ ዕለት ለእመቤታችን እሥረኞችን የምትፈታባት ናት:: የሰው ልጅ በ3 ወገን እሥረኛ ሊሆን ይችላል:: በሥጋዊው:- አጥፍቶም ሆነ ሳያጠፋ ሊታሠር ይችላል:: በመንፈሳዊው ግን ሰው በኃጢአት ማሠሪያ የሚታሠረው በጥፋቱ ብቻ ነው::
+ሌላኛው ማሠሪያ ደግሞ ማዕሠረ ደዌ (በደዌ ዳኝነት) መታሠር ነው:: መታመም የኃጢአተኛነት መገለጫ አይደለም:: ምክንያቱም ከቅዱሳን ወገን ከ80 % (ፐርሰንቱ) በላይ ድውያን ነበሩና::
+ታዲያ በዚህች ዕለት እመ በርሃን 3ቱንም ማሠሪያዎች እንደምትፈታ እናምናለን:: በእሥር ቤትም: በኃጢአትም ሆነ በደዌ ማሠሪያ የታሠርን ሁላችን በዚሁ ዕለት እንድትፈታን የአምላክ እናትን እንለምናት::
+በ3ቱም ማሠሪያዎች የታሠሩ ወገኖቻችንንም እያሰብን "ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሐን-የእሥረኞች ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ" እያልን (መዝ. 78:11) ልንጸልይ ይገባል::
+እመ ብርሃንንም እንደ ሊቃውንቱ:-
"እማእሠረ ጌጋይ ፍትሕኒ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክ: እምነ ሙቃሔ ጽኑዕ ወእማዕሠር ድሩክ: ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላዕክ::" እንበላት::
+" ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ "+
+ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::
+በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ
የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ::
+ቅዱስ መጽሐፍ እንደነገረን ጌታችን በነአልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::
+ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል::(ዮሐ.11)
ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በኋላ ሊያስነሳው ይመጣል::
+ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
+'አዳም ወዴት ነህ' ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ 'አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት' አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
+ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ
ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)
+ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በኋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና): ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ74 ዓ/ም
አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::
+" ፍልሠት "+
+ይህቺ ዕለት ለቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ስትሆን ይህ የተደረገውም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ቅዱሱ
ያረፈው ቆዽሮስ ውስጥ ነው:: ግን ባልታወቀ ጊዜና ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል::
+አንድ ቀንም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲቆፍሩ አንድ አንድ ሳጥን አገኙ:: በላዩ ላይ ደግሞ "ይህ የጌታ ወዳጅ የአልዓዛር ሥጋ ነው" የሚል
ጽሑፍ አግኝተው ደስ ተሰኝተዋል:: በታላቅ ዝማሬና ፍስሐም ከኢየሩሳሌም ወደ ቁስጥንጥንያ አፍልሠውታል::
+የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::
+" አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም "+
+እኒህ ጻድቅ ሰው ግብጻዊ ሲሆኑ በሰፊው የሚታወቁት በኢትዮዽያና በኢየሩሳሌም ነበር:: ገና በወጣትነት
የጀመሩትን የተጋድሎ ሕይወት ገፍተው በበርሃ ሲኖሩ የወቅቱ የግብጽ ሲኖዶስ ከበርሃ ጠርቶ የኢየሩሳሌም ዻዻስ እንዳደረጋቸው ይነገራል::
+በቅድስት ሃገርም በንጽሕናና በመንኖ ጥሪት ወንጌልን እየሰበኩ ኑረዋል:: አባ ዮሐንስ የነበሩበት ዘመን 14ኛው
መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የወቅቱ የኢትዮዽያ ንጉሥ ደጉ አፄ ዳዊት ነበሩ::
+ንጉሡ የግብጽ ክርስቲያኖችን ደም ለመበቀል (በወቅቱ ከሊፋዎች ያሰቃዩዋቸው ነበር) እስከ ላይኛው ግብጽ ወርደዋል:: በሃገር ውስጥ ያሉ ተንባላት አባሪዎቻቸውንም ቀጥተዋል::
በዚህ የተደናገጠው የግብጹ ሡልጣን 'አስታርቁኝ' ብሎ ስለ ለመነ ለእርቅ የተመረጡ አባ ዮሐንስና አባ ሳዊሮስ ዘምሥር ናቸው::
+እነዚህ አባቶች በ1390ዎቹ አካባቢ ወደ ኢትዮዽያ ከመጡ በኋላ አልተመለሱም:: ምክንያቱም ደጉ አፄ ዳዊት እጅግ ስለ ወደዷቸው 'አትሔዱም' ብለው ስላስቀሯቸው ነው:: እንዲያውም ለግማደ መስቀሉ መምጣት ትልቁን አስተዋጽኦ ያደረጉት አባ ዮሐንስ ሳይሆኑ አይቀሩም:: ዛሬ የጻድቁ ዕረፍታቸው ነው::
+አምላከ ቅዱሳን ስለ ድንግል እናቱ ብሎ ከኃጢአት ሁሉ ማሠሪያ ይፍታን:: የወዳጆቹን በረከትም አያርቅብን::
=>ጥቅምት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ
3.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
4.ቅዱስ ኢዩኤል ነቢይ
5.ቅዱስ ማትያስ ረድእ
=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
+" ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት... ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም 'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው::" (ዮሐ. 11:40-44)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethellettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment