#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት #ቢታኒያ አድሮ በማግሥቱ ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ
<<ማር 11÷ 11-12
ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፡፡ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ፍሬ አላገኛባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት በለስ የተባለች ቤተ "እስራኤል" ናት ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት ከእስራኤል ፍቅርን ሃይማኖት ምግባርን ፈለጋ አላገኘም እስራኤልም <ሕዝብ እግዚአብሔር መባል እንጅ፡፡ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት በመረገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋብት፡፡
በለስ ኦሪት ናት ኦሪት በዚህ ዓለም ስፋነ ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያት ልሽር አልመጣሁም ልፈፅም እንጅ በማለት ፈጸማት ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሱ ድህነት አላደረገባትምና ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት ድህነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደ መድርቅ ፍጥና አለፋት፡፡
በለስ ኃጢአት ናት የበለስ ቅጠል ሰፊ እንድሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፋና አገኛት በለስ ሲበሉት ይጠፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል ኃጣአትም ሲስሩት ደስ ደስ ያሰኛል ኃላ ግን ያሳዝናል ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአት ጋር ዋለ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፡፡
በአንቺ ፍሬ አይገኛ የሚለውም በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑን ለማለት ነው፡፡ ስትረገም ፍጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኛትን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለፅ ነው፡፡
#አንጸሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው
ጌታችን በለስን ከረገማት በኃላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ /የንግድ ቤት/ ሆነ ቢያገኛው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እነንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አድርጋችኃት ብሎ የሚሸጡትን ሁሉ ገለበጠባቸው ገርፎም አስወጣቸው ይህም የሚያሳየው ማደርያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኛን ኃጢአታችን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━⊱✿⊰━━
Comments
Post a Comment