✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ስምዖን ዘአርማንያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት "*+
=>ቅዱስ ስምዖን የአርማንያ ሰው ቢሆንም ሰማዕትነትን
የተቀበለው በሃገረ ፋርስ (በአሁኗ ኢራን አካባቢ) ነው::
ፋርስ ከ1ኛው መቶ ክ/ዘ እስከ ተንባላት (መሐመዳውያን)
መነሳት (7ኛው መቶ ክ/ዘ) ድረስ ባለው ጊዜ ብዙ
ሰማዕታት ለክብር በቅተውባታል::
+ብዙዎቹ የዚያው (የፋርስ) ዜጐች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ
የተሰዉት ከሌላ ሃገር መጥተው ነው:: ፋርሳውያን
አብዝተው ፀሐይን ያመልኩ ነበርና ክርስቲያኖቹን
የሚያሰቃዩት ይህቺውን ፍጡር እያመለኩ እንዲንበረከኩ
ነበር::
+ቅዱስ ስምዖንም ከፋርስ ግዛቶች በአንዱ ኤዺስ
ቆዾስነትን (እረኝነትን) ተሹሞ ነበርና የመከራው ተሳታፊ
ሆኗል:: በጊዜው ክርስትና እንደ ዛሬው "ሠርግና ምላሽ"
አልነበረምና ቅዱስ ስምዖን (እረኛው) እና 150 የሚያህሉ
ልጆቹ (መንጋው) ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ሆነዋል::
+በእምነታቸው ጸንተው በመገኘታቸውም እንዲገደሉ
ተወስኖባቸው 151ዱም ተሰውተዋል::
=>አምላከ ሰማዕታት በጽናታቸው አጽንቶ ከበረከታቸው
ይክፈለን::
=>ሚያዝያ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት (አርማንያዊ)
2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (የስምዖን ማሕበር)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ:
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Comments
Post a Comment