❇️የ6ተኛ ቀን ስነፍጥረት❇️
ሚያዚያ 4
✞✞✞ እንኩዋን እግዚአብሔር
አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ተፈጥሮተ አዳም ወሔዋን "*+
=>ጌታችን እግዚአብሔር ስነ ፍጥረትን በዕለተ እሑድ :
መጋቢት 29 ቀን እንደ ጀመረ ቤተ ክርስቲያን
ታስተምራለች:: በዕለተ እሑድም ዓለምን ካለመኖር ወደ
መኖር አምጥቶ 8 ፍጥረታትን ፈጥሯል::
*ሰኞ 1:
*ማግሰኞ 3:
*ረቡዕ 3:
*ሐሙስ 3:
*ዓርብ 3 ፍጥረታትን ፈጥሯል::
+እነዚህን ቢደምሯቸው 21 ይሆናሉ:: የእግዚአብሔር
22ኛውና የመጨረሻው ፍጥረት የሰው ልጅ ነውና ከ4
ባሕርያተ ሥጋ 5ኛ ባሕርየ ነፍስን አዋሕዶ ፈጥሮታል::
+ከፍጥረታቱ አልቆ : በአርአያውና በአምሳሉ ከመፍጠሩ
ባለፈ በነፍስ ሕያው አድርጐ በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ
ንጉሥ : ነቢይና ካህንም ይሆን ዘንድ አድሎታል::
+ከዚያም ቅዱሳን መላእክት አዳም በተፈጠረ በ40:
ሔዋን በተፈጠረች በ80 ቀን የብርሃን ልብስ አልብሰው
"አዳምና ሔዋንን የፈጠረ እግዚአብሔር በባሕርዩ ቅዱስ ነው" እያሉ እየዘመሩ ወደ ገነት አስገብተዋቸዋል::
=>በጥንተ ተፈጥሮ: በሐዲስ ተፈጥሮ የፈጠረንና ያከበረን ዘለዓለም ሥላሴ ክብር ምስጋና ይድረሰው::
=>+"+ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ::
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው:: ወንድና ሴት አድርጐ
ፈጠራቸው . . . እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ::
እነሆም እጅግ መልካም ነበረ:: +"+ (ዘፍ. 1:26-31)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━⊱✿⊰━━
Comments
Post a Comment