✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡✝አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኩዋን ለጌታችን "ኢየሱስ ክርስቶስ" ዓመታዊ በዓልና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" ወርኀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ✝ቅዱሱ ቤተሰብ እና ጌታ✝ "*+
=>ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የዓለም ሁሉ ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ቀን ወደ ቢታንያ ሔዶ: እነ ቅዱስ አልዓዛርና ቤተሰቦቹ እንግድነት ተቀብለውታል::
+በዚያም ቅድስት ማርታ በጌታ ፊት ስታገለግል: ቅዱስ አልዓዛር ከጌታ ጐን ተቀምጦ: ቅድስት ማርያ በ300 ዲናር የገዛችውን ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: እግሩንም በጠጉሯ አበሰች:: (ዮሐ. 12:1)
+ለዛ የተባረከ ቤተሰብም ታላቅ በረከት ሆነ:: በርግጥም ድንቅ ነው:: ጌታን በቤት ማስተናገድ ፍፁም መታደል ነው::
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ይሁዳ በ300 ዲናሩ ሽቱ አመካኝቶ በጌታ ላይ አንጎራጎረ:: አይሁድ ደግሞ አልዓዛርን ይገድሉት ዘንድ ተማከሩ:: ምክንያቱም ጌታችን በርሱ ላይ የሠራትን ድንቅ እያዩ ከአይሁድ ወገን ብዙዎቹ ያምኑ ነበርና::
=>ቤተ አልዓዛርን የባረከ ጌታ በቸርነቱ የኛንም ይባርክርልን::
=>መጋቢት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሱ ቤተሰብ (አልዓዛር: ማርያና ማርታ)
2.አባታችን ላሜኅ (የማቱሳላ ልጅ-የጻድቁ ኖኅ አባት)
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
=>+"+ የወንድማማች መዋደድ ይኑር:: እንግዶችን መቀበል አትርሱ:: በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና:: ከእነርሱ ጋር እንደታሰረ ሆናችሁ እስሮችን አስቡ:: የተጨነቁትንም ራሳችሁ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ሆናችሁ አስቡ:: +"+ (ዕብ. 13:1)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━⊱✿⊰━━
Comments
Post a Comment