††† እንኳን ለጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት †††
††† አባ ሚካኤል በትውልዳቸው ግብጻዊ ሲሆኑ ገና በሕፃንነታቸው ገዳማዊ ሕይወትን መርጠው ለዓመታት በተጋድሎ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ ኑረዋል:: በዘመኑ ግብጽ ሊቀ ጳጳሷ አርፎባት ነበርና በሱባዔ እያሉ "አባ ሚካኤልን ሹሙት" የሚል ቃል ከሰማይ ሰምተው "እንሹምህ" አሉት:: "እንቢ" ቢላቸው ግድ ብለው አስረው ሹመውታል::
አባ ሚካኤል በመንበረ ማርቆስ ላይ እረኝነት (ጵጵስና) ተሹሞ ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን ተቀብሏል:: በወቅቱ የነበረው የግብጽ ከሊፋ (አባቶቻችን ክፉ ሰው ማለት ነው ይላሉ) አባ ሚካኤልን አሥሮ በሕዝቡ ፊት ይደበድባቸው ነበር::
ከመከራው ብዛት የተነሳ በርካቶቹ ተገደሉ: ከ20,000 በላይ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን ካዱ::
ይህንን የሰሙት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ በመንፈሳዊ ቅንዐት 100,000 ፈረሰኛ: 100,000 በበቅሎ: 100,000 ሠራዊት በግመል ጭነው ወደ ግብጽ ወርደው ከሊፋውን አስጨንቀው የግብጽን ክርስቲያኖች ከመከራ ታድገዋል::
አባ ሚካኤልም ከእሥር ከተፈቱ በኋላ የካዱ ምዕመናንን ለመመለስ ብዙ ደክመዋል:: ተሳክቶላቸውማል:: ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት ከዓመታት ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን አርፈዋል::
††† ፈጣሪ ከበረከታቸው አይንሳን::
††† መጋቢት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
7.አባ ዳንኤል ጻድቅ
††† "በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" †††
(፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━⊱✿⊰━━
Comments
Post a Comment