✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ሚያዝያ ፳፰ ❖
❖ ሚያዝያ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ሜልዮስ ሰማዕት +"+
=>ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርትያሳለፈ: በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው::
ይሕችን ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም
ለበርካታ ዓመታት ተጋድሏል::
+በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሳታል:: የአባ ሜልዮስ ጸጉሩ እስከ እግሩ: ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር::
+እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: 2ቱ ቅዱሳን አምላካቸውን
እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም ቅንነት አገልግለዋል::
+ከቆይታ በኋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት:: ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው ደበደቡት::
+ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም በሰይፍ አንገታቸውን መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ15 ቀናት ካሰቃዩት በኋላ በዚህች ቀን በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው ገድለውታል:: ጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጓል::
+ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ ወደነርሱ መልሶባቸው ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል::
❖ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ በረከትን ያካፍለን::
❖ሚያዝያ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሜልዮስ ዘደብረ ኮራሳን (ጻድቅና ሰማዕት)
2.አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ (ደቀ መዛሙርቱ)
3.ቅዱስ ብስጣውሮስ ሰማዕት (ተንባላት የገደሉት)
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ አምላካችን አማኑኤል
2፡ ቅዱሳን አብርሃም ፡ ይስሐቅ ፡ ወያዕቆብ
3፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
4፡ ቅዱሳን እንድራኒቆስ ወአትናስያ
5፡ ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
6፡ ቅዱሳን አባዲር ወኢራኢ
7፡ ቅድስት ሶስና
++"+ ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ:: እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው:: አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ:: እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን:: የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ::
+"+ (ራዕይ. 2:10)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment