Comments

3-comments

FOLLOW ME

LATEST

3-latest-65px

About

This just a demo text widget, you can use it to create an about text, for example.

Testimonials

3-tag:Testimonials-250px-testimonial

Popular Posts

Sections-BTLabels

Ads block

Banner 728x90px

About me

About Me


Aenean sollicitudin, lorem quis bibendum auctor, nisi elit consequat ipsum, nec sagittis sem nibh id elit. Duis sed odio sit amet nibh vulputate.

Section Background

Section Background

Follow Us Telegram & Facebook gage

Contact us-desc:Feel free to contact us at anytime about our service.

Name

Email *

Message *

SEARCH

በእንተ ስማ ለማርያም
Powered by Blogger.

Advertisement

3/recentposts

Comments

Ad Code

Responsive Advertisement

Facebook

Advertisement

Report Abuse

Featured Post

ሐምሌ ፳፯

††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...

Post Top Ad

Archive

Sections

ዝክረ ቅዱሳን መዝሙር ስነ–ፅሁፍ

Blog Archive

SEARCH

Search This Blog

Recent in Sports

በእንተ ስማ ለማርያም

4-tag:Campus-500px-mosaic

Header Ads

Subscribe Us

Random Posts

Recent Posts

Header Ads

Header Background

Header Background
Header Background Image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Section Background

Section Background
Background image. Ideal width 1600px with.

Search This Blog

Categories

A Team Of Awesome People

We are a creative web design agency who makes beautiful websites for thousands of peoples.

Labels

Labels

Follow Us

Sponsor

Ads

Popular Posts

Pages

Blogger templates

3/recentposts

Blogroll

3-comments

Pages - Menu

Pages - Menu

About

Blogger templates

About

Popular Posts

LATEST POSTS

SEARCH

Skip to main content

ግንቦት ፫

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ +"+

+ባለንበት ዘመን አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱሳኑ ስማቸው ከነሥራቸው መዘንጋቱ ነው:: ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ደማቸው እንዳልፈሰሰ: አጥንታቸውም እንዳልተከሰከሰ ይሔው አስታዋሽ አጥተው ስማቸውም ተዘንግቶ ይኖራል::

+አንዳንድ ንፉቃን ደግሞ ከዚሁ ብሶ ጭራሹኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስለ ክርስቶስ ትታ ስለ ቅዱሳኑ ብቻ ትሰብካለች ይሉናል::

+በእጅጉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ የቅዱሳን ሐዋርያት (የ120ው ቤተሰብ) መዘንጋት ነው:: ከ120ው ቤተሰብ የአብዛኞቹ ስም በመዘንጋቱ: ሊቃውንቱም ዝምታን በመምረጣቸው "ያሶን: አርስጦስ: አፍሮዲጡ: ቆሮስ . . . እያልን የ72ቱን አርድእት ስም ስንጠራ ግር የሚለው ዓይነት ትውልድ ተፈጥሯል::

+እስኪ እንዲያው ቢያንስ ሐዋርያትንና ዐበይት ቅዱሳንን እናስባቸው:: አስበናቸው የሚጨመረልን እንጂ የሚጨመርላቸው የለምና::

+ዛሬ የምናስበው ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችንን ከጥምቀቱ በኋላ ተከትሎ ለ3 ዓመታት ከእግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ተምሯል:: ከጌታችን ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

+ለብዙ ጊዜ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ተመላልሶ ሰብኳል:: በመከራውም ተካፍሎታል:: ታላላቆቹ ሐዋርያት ሰማዕትነትን ከተቀበሉ በኋላ ለመጣው አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ከጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል የሰማውን አስተላልፏል::

+ወንጌልን ስለ ሰበከላቸው አሕዛብ ብዙ ጊዜ አስረው ይደበድቡት: ያንገላቱት ነበር:: አንዳንድ ጊዜም እሳት እያነደዱ ያቃጥሉት ነበር:: ፈጣሪው ግን በተአምራት እያዳነው ከርሱ ጋር አልተለየም::

+ከከተማ ወጥቶ በዱርና በእስር ቤቶች ብዙ ነፍሳትን: ሽፍቶችንም ሳይቀር ወደ ክርስትና ማርኳል:: ቅዱስ ያሶን ለረዥም ዓመታት ሰብኮ በመልካም ሽምግልና አርፏል::

ንግሥት ወለተ ማርያም

+ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት ወለተ ማርያም ትታሰባለች::

+ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት:: በንግስትነት በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር::

+ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን ቤተሰብ ወደ መልካም ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች::

❖አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን::

ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ)
2.አባ ብሶይ ሰማዕት
3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ
4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት)

ወርኃዊ በዓላት
1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን
4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5፡ አባ ዜና ማርቆስ
6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ
7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት
8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ

++"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው
. . . እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም
ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ
ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17)

     ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
        ✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
    ✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
   
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ


ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!። 
  "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://
gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments