✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞
❖ የካቲት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+*" ማር ፊቅጦር "*+
=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ! ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው::
=>እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል:-
+ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው 20 ዓመት
ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ 3ኛ አድርጐ ሾመው::
+የድሮዋ አንጾኪያ (ሮም) እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ
ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት: ይወዱትም ነበር::
+እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል ነበር:: ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ እኩሉን
የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ እርሱ የንጉሡ 3ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ
የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::
+ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ47 ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ:: በመጋዝ ተተረተሩ:: ለአራዊት ተሰጡ:: በግፍም ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::
+በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ:: ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::
+ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ መኩዋንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ ሲል መናቅን መርጧልና::
+ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኩዋንንቱ እየተፈራረቁ አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል: ምላሱንም ቆርጠዋል:: ሚያዝያ 27 ቀን ግን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች::
❖እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው:- "እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ:
ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባዋለሁ::"
❖ይህች ቀን ማር ፊቅጦር የተወለደባት ናት፡፡ እናቱን ቅድስት ማርታ (ሶፍያንም) እናስባለን፡፡
❖ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን::
✞✞ ቅዱስ አውሳብዮስ ካልዕ (ጥዑመ ዜና) ✞✞
=> ቅዱስ አውሳብዮስ በወጣትነቱ ከተባረከች ሚስቱ ጋ በድንግልና የኖረ; በዘመኑ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ ይጸልይ;
4,000 አቡነ ዘበሰማያት በአንድ ቀን ያደርስ የነበረ; ስለ ሃይማኖትም በቀስት የተወጋ; በእሳት የቃጠለ; አካሉን
ቆራርጠው የጣሉትና እግዚአብሔር ከሞት ያስነሳው ጻድቅና ሰማዕት
ነው:: ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ ከነሥጋው ወደ ሰማይ ተነጥቆ ለ14 ዓመታት ቆይቷል:: ወደ ምድርም ተመልሶ ለ40 ዓመታት በሐዋርያነት ከ85,000 በላይ አሕዛብን ወደ ሃይማኖት መልሷል::
ጌታም በስምህ የተማጸነውን እስከ 7 ትውልድ እምርልሃለሁ ብሎታል::"
❖አባቶቻችን ደግሞ 'ስም አጠራሩ የከበረ ዜና ሕይወቱ ያማረ' ሲሉ ይጠሩታል::
❖ ከበረከቱ ያድለን::
✞ የካቲት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አውሳብዮስ ጻድቅ (ጥዑመ ዜና)
2.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት (ልደቱ)
3.ቅዱስ ሰርግዮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ መፁን ቀሲስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (የቅ/ፋሲለደስ ልጅ)
6.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
7.አባ ክፍላ
8.አባ ኅብስ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ : እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ :
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment