✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ የካቲት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+✝" በዓለ ስምዖን "✝+
=>ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ጌታ በተወለደ በ40 ቀኑ ራሱ የሠራውን ሕግ ይፈፅም ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል:: እንደ ሥርዓቱም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አገልጋዩዋ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ አቅርበዋል::
+ለ284 ዓመታት የአዳኙን (የመሢሁን) መምጣት ይጠብቅ የነበረው አረጋዊው ስምዖን በዚህች ዕለት ስላየውና ስለታቀፈው ዕለቱ በዓለ ስምዖን ይባላል:: (ሉቃ. 2:22) ከዘጠኙ የጌታ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው::
+ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ከዓለም ፍጥረት በ5,200 ዓመታት (ማለትም ከክርስቶስ ልደት 300 ዓመታት በፊት) በጥሊሞስ የሚሉት ንጉሥ በግሪክ ነገሠ::
+በጊዜውም በኃይለኝነቱ ሁሉን አስገብሮት ነበርና "ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጬ: እንደ ገል ቀጥቅጬ ገዛሁት:: ምን የቀረኝ ነገር አለ?" ሲል ተናገረ:: ባሮቹም "አንድ ነገር ቀርቶሃል:: በምድረ እሥራኤል ጥበብን የተሞሉ 46 መጻሕፍት አሉ:: እነርሱን አስተርጉም" አሉት::
+ያን ጊዜ እሥራኤላውያንን አስገብሯቸውነበርና 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ72 ምሑራን(ተርጉዋሚዎች)
ጋር እንዲያመጡለት አዛዦቹን ላከ:: እነርሱም 46ቱን መጻሕፍተ ብሉይ ኪዳን ከ72 ምሑራን ጋር አመጡለት::
+አይሁድ ክፋተኞች መሆናቸውን ሰምቷልና 36 ድንኩዋን አዘጋጅቶ: ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲሠሩ: ሲተረጉሙ እንዳይመካከሩ 36 ጠባቂዎችን ሾመባቸው:: ይህ ነገር ለጊዜው ከንጉሡ ቢመስልም ጥበቡ ግን ከእግዚአብሔር ነው::
+ምንያቱም በጊዜ ሒደት መጻሕፍተ ብሉያት በአደጋ እንደሚጠፉ ያውቃልና ሳይበረዙ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ለእኛ እንዲደርሱ ነው:: ስለዚህም ከክርስቶስ ልደት 284 ዓመት በፊት 46ቱም ሁሉም መጻሕፍት (ብሉያት) ከእብራይስጥ ወደ ጽርዕ ልሳን በ70ው ሊቃናት አማካኝነት ተተረጐሙ:: (በእርግጥ ከዚያ አስቀድሞ መጻሕፍት (ብሉያት) ወደ ሃገራችን መምጣቸውና ወደ ግዕዝ ልሳን መተርጐማቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው)
+ወደ ዋናው ጉዳያችን ስንመለስ ከ70ው ሊቃናት መካከል በእድሜው አረጋዊ የሆነ (እንደ ትውፊቱ ከሆነ 216 ዓመት የሆነው) ስምዖን የሚሉት ምሑረ ኦሪት ነበር:: በፈቃደ እግዚአብሔር ለእርሱ መጽሐፈ ትንቢተ ኢሳይያስ ደርሶት እየተረጐመ ምዕራፍ 7 ላይ ደረሰ::
+ቁጥር 7 ላይ ሲደርስ ግን "ናሁ ድንግል ትጸንስ: ወትወልድ ወልደ" የሚል አይቶ "አሁን እንኳን የአሕዛብ ንጉሥ የእሥራኤልስ ቢሆን ድንግል በድንግልና ጸንሳ ትወልዳለች ብለው እንዴት ያምነኛል!" ሲል አሰበ:: "በዚያውስ ላይ ኢሳይያስ በምናሴ የተገደለው ስለዚህ አይደል!" ብሎ ቃሉን ሊለውጠው ወሰነ::
+አመሻሽ ላይም 'ድንግል' የሚለውን 'ወለት-ሴት ልጅ' ብሎ ቀየረው:: እርሱ ሲያንቀላፋ ቅዱስ መልአክ ወርዶ 'ድንግል' ብሎ አስተካከለው:: ከእንቅልፉ ሲነቃ ግራ ተጋብቶ እንደ ገና ፍቆ ቀየረው::
+አሁንም መልአኩ 'ድንግል' ሲል ቀየረበት:: 3 ጊዜ እንዲህ ከሆነ በኋላ ግን መልአኩ ተገልጦ ገሰጸው:: በዚያውም ላይ "ይህችን ድንግልና መሲሑን ልጇን ሳታየውና ሳትታቀፈው ሞትን አታይም" ብሎት ተሰወረው:: አረጋዊ ስምዖን ከዚያች ዕለት በኋላ የመድኅን ክርስቶስን መምጣት ሲጠብቅ ለ284 ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሁኖ ኖረ:: አካሉም አለቀ::
+ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነበት በዚያ ሰሞን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ::
+ሕግን የሠራ ጌታ እርሱ 'ፈጻሜ ሕግ' ይባል ዘንድ የርግብ ግልገሎችን (ዋኖሶችን) ይዘው በተወለደ በ40 ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት:: በዚህች ቀንም ቅዱስ መልአክ መጥቶ ቅዱስ ስምዖንን ከአልጋው ቀሰቀሰው:: ተስፋ የሚያደርገው አዳኙ (መሲሑ) እንደ መጣም ነገረው::
+ይህን ጊዜ አረጋዊው አካሉ ታድሶ እንደ 30 ዓመት ወጣት እመር ብሎ ከአልጋው ተነሳ:: እንደ በቅሎ እየሠገረም ወደ መቅደስ ወጣ:: በዚያ መሲሑን (ፈጣሪውን) ሲመለከት እንደ እንቦሳ ዘለለ:: ቀረብ ብሎም ሕጻን ጌታን ከድንግል እናቱ እጅ ተቀበለው::
+ከደስታው ብዛት የተነሳም "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ: በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ሲል ጸለየ:: ትንቢትንም ተናገረ:: በዚያችው ዕለትም ዐርፎ ተቀበረ::
+"+ ሐና ነቢይት +"+
+ዳግመኛ በዚህች ቀን አረጋዊቷን ነቢይት ቅድስት ሐናን እናስባለን:: ይህች ቅድስት ትውልዷ ከነገደ አሴር ሲሆን አባቷ ፋኑኤል ይባላል:: በትውፊት ትምሕርት ሐና የተዳረችው በልጅነቷ (በ12 /15/ ዓመቷ) ነው:: ለ7 ዓመታት ከልጅነት ባሏ ጋር ኖራ ዕድሜዋ 19 (22) ሲደርስ ሞተባት::
+እንደ እሥራኤል ልማድ ሌላ እንድታገባ ብትጠየቅም 'እንቢ' ብላ መበለት ሆነች:: ራሷንም ለእግዚአብሔር አሳልፋ ሰጠች:: በቤተ መቅደስም ለ84 ዓመታት ለፈጣሪዋ ተገዛች:: ፈጽማ ትጸልይና ትጾም ነበርና በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ውጪውን አልተመለከተችም::
+ለእርሷ 103 (106) ዓመት ሲሆን መድኃኒታችን ተወለደ:: በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ተመልክታም ጌታን ባረከች:: ደስ እያላትም ትንቢትን ተናገረች:: ወደ ቤቷ ገብታም ነፍሷን ሰጠች:: (ሉቃ. 2:36-38)
❖ቸሩ መድኃኒታችን ተርፎ ከሚቀረው ዘመን ዕድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍሥሐ አይንሳን:: ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
✞የካቲት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ስምዖን አረጋዊ
2.ቅድስት ሐና ነቢይት (የፋኑኤል ልጅ)
3.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ እግዝእት
4.አባ ኤልያስ ገዳማዊ (በትህትና ያጌጠ ቅዱስ ሰው)
❖አረጋዊ ስምዖንን ከድካም አልጋ ያነሳ አምላከ ቅዱሳን
እኛንም ድካመ ነፍስን ከሚያመጣ የበደል ምኝታ በቸርነቱ
ያንሳን::
++"+ እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕጻኑን ጌታ ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው:: እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ:- 'ጌታ ሆይ! አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ:: ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና:: ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን: ለሕዝብሕም ለእስራኤል ክብር ነው::' ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር::
+"+ (ሉቃ. 2:27)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together.https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment