በእንተ ስማ ለማርያም:
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞
✞✞✞ እንኩዋን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "*+
=>ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው
የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ
ውስጥ ያዙት::
¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ
ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
+ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
+በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ
6,666 ገረፉት::
¤ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::
¤6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው
ሰቀሉት::
+7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
¤ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን
ተናገረ::
¤ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::
+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ
ፈታ::
¤11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና
ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::
በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ::
ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::
+ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27
ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት
አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::
+ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::
+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::
+"+ ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ +"+
=>በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው:: "ታላቁ
መቃርዮስ": "መቃርስ እስክንድርያዊ": "መቃርስ
ባሕታዊ"ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: ይህኛው
ቅዱስ ደግሞ "መቃርስ ኤዺስ ቆዾስ: መቃርስ ብጹዓዊ: መቃርስ ዘሃገረ ቃው" ይባላል:: ሁሉም መጠሪያዎቹ ናቸው::
+ቅዱሱ የ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ሲሆን የቅዱስ
ቄርሎስና የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ተከታይ ነው:: ከሕይወቱ
ማማርና ከቅድስናው መሥመር የተነሳ አበው
አመስግነውት አይይጠግቡም:: ልበ አምላክ ቅዱስ
ዳዊት "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል" እንዳለው:: (መዝ. 91)
+ዳግመኛ "ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ
ሙሐዘ ማይ" (መዝ. 1:3) እንዳለው ቅዱስ መቃርስ
እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን አፍርቷል:: ከሁሉ አስቀድሞ
በበርሃ ኗሪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ስለ ጌታ ፍቅር እንባው
እንደ ዥረት እየፈሰሰ:: ራሱን በብረት ዘንግ ይመታ ነበር::
+"ቃው" በምትባል ሃገር ዻዻስ ሆኖ በተሾመ ጊዜም
ተጋድሎውን አልቀነሰም:: ዻዻስ ቢሆንም የሚለብሰው
የበርሃዋን ደበሎ ነው:: ከብቅዓቱ የተነሳ የሕዝቡ
ኃጢአት በግንባራቸው ላይ ተጽፎ እየታየው ስለ ወገኖቹ
ያለቅስ ነበረ:: በቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሞ አንጀቱ ቅጥል እስኪል ድረስም ያለቅስ ነበር::
+ሁልጊዜ ሲቀድስ ጌታችንን ከመላእክቱ ጋር ያየው
ነበር:: አንድ ቀንም ጌታ ቅዱስ መቃርስን "ዻዻሱ ሆይ
ሕዝቡን ገስጻቸው:: ብትገስጻቸውና ባይሰሙህ እዳው
በእነርሱ ላይ ነው" አለው:: ቅዱስ መቃርስም ሕዝቡ
ከኃጢአታቸው ይመለሱ ዘንድ ይመክራቸው:
ይለምንላቸውም ነበር::
+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ አብዳን) 636 ዻዻሳት ንጉሡን ፈርተው ሃይማኖታቸውን ሲክዱ ቅዱሳኑ ዲዮስቆሮስና መቃርስ "ተዋሐዶን አንክድም" በማለታቸው ዘበቱባቸው:: ብዙ አሰቃይተውም ወደ ጋግራ ደሴት አሳደዷቸው::
+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ውስጥ ሲሞት ቅዱስ
መቃርስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ሕዝቡን ሲመክር
ያዙት:: ከመሬት ላይ ጥለውም እየደጋገሙ ኩላሊቱን
ረገጡት:: ከመከራው ብዛትም በዚህች ቀን ነፍሱን
አሳልፎ ሰጠ:: ቅዱሱ ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ብዙ
ተአምራትን ሠርቷል::
+አበውም ስለ ቅዱስ መቃርስ ብሎ ጌታ እንዲምራቸው
እንዲህ ይጸልዩ ነበር:-
"ሰላም ሰላም ለፈያታዊ ዘቀደሶ::
ሃገረ ጽጌ የአኀዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ::
ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ::
በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ::
ወበበትረ መስቀል ዘይዘብጥ ርዕሶ::" (አርኬ ዘጥቅምት 27)
+*" አቡነ መብዓ ጽዮን "*+
=>ሃገራችን ኢትዮዽያ እጅግ በርካታ ቅዱሳንን ስታፈራ
አንዳንዶቹ ደግሞ የተለዩ ናቸው:: ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮን በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን በሽዋ (ሻሞ) አካባቢ የተነሱ ጻድቅ ናቸው:: ገና ከልጅነታቸው የእመቤታችንና የጌታችን ፍቅር የሞላባቸው ነበሩ::
+በ3 ዓመታቸው ከእንግዳ የወሰዷት ስዕለ አድኅኖ
ተለይታቸው አታውቅም ነበር:: በወጣትነታቸው ጊዜም
ብሉያት ሐዲሳትን: ቅኔንም ጨምሮ ተምረው:
ከቤተሰባቸው አስፈቅደው በምናኔ ገዳም ገቡ::
ከዚያ በሁዋላ ያለውን ገድላቸውን ማን ችሎ
ይዘረዝረዋል!
+በተለይ ዐርብ ዐርብ የጌታን 13 ሕማማት ለማዘከር
ሲቀበሉት የኖሩት መከራ እጅግ ብዙ ነው:: ድንጋይ
ተሸክመው እንባና ላበታቸው እየተንጠፈጠፈ ይሰግዳሉ:: በድንጋይ ደረትና ጀርባቸውን ይደቃሉ:: ራሳቸውን ይገርፋሉ:: በዋንጫ ሐሞት (ኮሶ) ሞልተው ይጠጣሉ::
+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ወር በገባ በ27 ስለ መድኃኔ
ዓለም ጠላ ጠምቀው: ንፍሮ ነክረው ወደ ገበያ ይወጡና ይዘክሩ ነበር:: ከዝክሩ የነካ ሁሉ ይፈወስ ነበር:: ከእንባ ብዛት ዓይናቸው ቢጠፋ ድንግል ማርያም መጥታ ብርሃናዊ ዓይንን ሰጠቻቸው:: ስለዚህም "ተክለ ማርያም (በትረ ማርያም)" ይባላሉ::
+ጌታችንም ስለ ፍቅራቸው በአምሳለ ሕጻን
ይገለጽላቸው: እርሳቸውም አቅፈው ይስሙት ነበር::
ጻድቁ ተናግረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ ተጋድለው ጌታ በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡበት ስልጣንን ሰጣቸው:: አባታችን ቅዱሱና ጻድቁ መብዓ ጽዮን ከብዙ ትሩፋት በሁዋላ ዐርፈዋል::

+"+ አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ +"+
=>ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም
ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ
ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ
ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::
+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም
"ክርስቶስ አልተወለደም:: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ
ነው::" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ
ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር
ተገናኙ::
+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ::
አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው
(ሲያጠምቁዋቸው) "ጽጌ ድንግል" አሏቸው::
ሲመነኩሱም "ጽጌ ብርሃን" ተብለዋል:: ቀጥለውም
በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ
ምሥጢር ተገለጠላቸው::+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም
ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርገው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: በዚህች ቀንም ዐርፈዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ:
በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን::
ከመስቀሉና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
=>ጥቅምት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት
1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ
3.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
4.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
3.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
5.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
=>+"+ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ:: ሕማማችንንም
ተሸክሟል:: እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ
ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው:: እርሱ ግን ስለ
መተላለፋችን ቈሰለ:: ስለ በደላችንም ደቀቀ::
የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ:: በእርሱም
ቁስል እኛ ተፈወስን:: +"+ (ኢሳ. 53:4)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethellettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment