✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖✝ኅዳር 15✝ ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ ❇️ጾመ ነቢያት❇️ +"+
=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::
+"7ቱ" አጽዋማት:-
1.ዓቢይ ጾም
2.ጾመ ፍልሠታ
3.ጾመ ሐዋርያት
4.ጾመ ነቢያት
5.ጾመ ድኅነት
6.ጾመ ነነዌ እና
7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::
+በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለውና ይቆየን:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል::
+ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን::
+ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት: ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2) አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ. 13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን::
+ጾመ ነቢያት ማለት ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው::
በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስና
ቅዱስ ዳንኤል በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን
ናቸው:: (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3)
+ቅዱስ ዳዊት "ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ" (መዝ.
68:10, 108:24) ብሎ ዘወትር ሰውነቱን በምን
ለእግዚአብሔር ያስገዛ እንደ ነበር ጠቅሷል:: ቅዱሳን
ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ
መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም
አብቅቶታል::
+በየዘመኑ ጻድቃነ ብሊት በጾማቸው ከመዓት ርቀዋል::
ጸጋ: ክብርና ሞገስንም አግኝተዋል:: ይህ ጾም ኅዳር 15
ቀን ጀምሮ ታሕሳስ 29 ቀን የሚጠናቀቅ ሲሆን በ4
ዓመት አንዴ 1 ቀን ወደ ሁዋላ ያሰግራል::
+ጾሙም የተለያዩ መጠሪያዎች ሲኖሩት እነዚህ
ይጠቀሳሉ:-
1.ጾመ ነቢያት
2.ጾመ ማርያም (ጌታን ጸንሳ ሳለ የአባቶቿን ጾም
ጾማለችና)
3.ጾመ ሐዋርያት (ሐዋርያትም በረከተ ነቢያትን ሲሹ
ይጾሙት ነበርና)
4.ጾመ ጌና ("ጌና - ልደተ እግዚእ ስቡሕ" ማለት ነው)
5.ጾመ ስብከት (ስብከተ ነቢያት ስለሚታሰብበት)
6.ኅዳር ጾም (በወሩ ምክንያት)
7.ጾመ ፊልዾስ (አርድእተ ፊልዾስ ሐዋርያ ለጉዳይ ስለ ጾሙት)
=>አምላከ አበው ነቢያት በጾሙ ከሚገኘው ጸጋ በረከት አይለየን::
=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር:: በፍጹም ልባችሁ
በጾምም: በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም
የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ኢዩ. 2:12). ዸነ
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!።
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Togethellettps://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment