+"የመስቀል ወፍ"+
ይህች ወፍ በአገራችን በኢትዮጵያ "የመስቀል ወፍ" በመባል ትታወቃለች፡፡
ምክንያቱም ለተወሰኑ ወራት ያህል በሌላ ሥፍራ ተሰውራ ቆይታ የመስቀል በዓል (መሥከረም 17) ሲያቃርብ ብቅ ብላ ስለ ምትታይ ነው፡፡
.
እንግዲህ ከዚች ወፍ የዘንድሮ 2015 ዓ.ም የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ትልቅ ትምህርትን እንማራለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
መችም እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ሕዝቡን ያስተምራል፡፡ ኢዮ.33፡14
.
ዛሬስ ልዑል እግዚአብሔር ይህችን ወፍ ምክንያት አድርጎ ቢያስተምረን ማን ይከለክለዋል?
ይህች ወፍ የመስቀሉ ፍቅር ከገባቸው ከኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ጋር የመስቀሉን በዓል በዝማሬና በምሥጋና ለማሳለፍ ለበዓሉ አከባበር የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቃ ከበዓሉ ቀደም ብላ በየ አከባቢያችን መገለጧ የሚገርም ትርዒት ነው፡፡
ደግሞም ይህች ወፍ ለመስቀሉ ትልቅ ፍቅር ያላት ነው የምትመስለው፡፡
መናፍቃን ግን የዚህችን ወፍ ያህል እንኳ ዕውቀት አጥተው ከዕውቀት ነፃ በሆነ አመለካከት መስቀሉን እየተቃወሙ ሆዳቸውን አምላካቸው አድርገው ክብራቸውን በነውራቸው ሽጠው የመስቀሉ ጠላቶች ሆነው መመላለሳቸው የሚያሳዝን ነው፡፡ ፊል.3፡18
.
በእርግጥም የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት መናፍቃን ሞኝነት፥ አላዋቂነት፥ መሀይምነት፥ ድንቁርና... ቢሆንም ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው።
1ቆሮ.1:18
.
ምናልባት የመስቀሉ ፍቅር ያልገባችሁ ሰዎች!
እስኪ ወፊቱን ጠይቋት!
ለምን ይሆን በሰመቀል በመስቀል በዓል ላይ የምትመላለሰው?
ለምንስ ይሆን ትኩረቷን በመስቀሉ ላይ ያደረገችው?
ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?
1ቆሮ.11:14
.
ይህች ወፍ የሙጥኝ ብላ ትኩረቷን በመስቀሉ በዓል ላይ በማድረጓ ትምክህቷም ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ትምክህት ነው የሚመስለው፡፡ ገላ.6፡14
.
እንግዲህ ይህች ወፍ የመስቀሉን ነገር የዘነጉ ሰዎች እንዲያስቡበት ቀደም ብላ መጥታ ከእግዚአብሔር በተሰጣት ልዩ ዜማ የበዓሉን መድረስ ታበሥራለች፡፡
.
በቃ ምን አለፋችሁ!
ወፊቷ አስተውሎ ለተመለከታት ሰው ሁሉ ስለ መስቀሉ ፍቅር በጥበብ የምትሰብክ ልዩ ሰባኪት ናት፡፡
ስለዚህ ልብ ብላችሁ ተመልከቷት ግብዣዬ ነው፡፡
.
አድራሻችሁ ከመስቀሉ ሥር የሆናችሁ ሁሉ መጪው የመስቀል በዓል የሠላምና የፍቅር በዓል ይሁንላችሁ!
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment